.የኢሳት አማርኛ ዜና

ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በቅርቡ የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ ይደረጋል አሉ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010) ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በቅርቡ የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ እንደሚደረግ ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ የሚደረገው ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ነው ብለዋል። መንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንደገጠመውም ፕሬዝዳንቱ በይፋ ተናግረዋል። እንደ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ገለጻ በኢትዮጵያ ላለፉት 3 አመታት በነበረው የውጭ ምርቶች መላክ መዳከምና ከዚህ ጋር ...

Read More »

በሲዳማ ዞን ጭኮ ወረዳ መምህራን ለአባይ ግድብ አናዋጣም በማለታቸው ደሞዛቸው ታገደ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010) በሲዳማ ዞን ጭኮ ወረዳ መምህራን ለአባይ ግድብ አናዋጣም በማለታቸው ደሞዛቸው መታገዱ ተሰማ። የአባይ ዋንጫ በዙር ጭኮ ወረዳ መግባቱን ተከትሎ እያንዳንዱ የመንግስት ሰራተኛ ከደመወዙ ከ300 ብር ጀምሮ እንዲያዋጣ መመሪያ ተወስኖበታል። የሴክተር መስሪያ ቤቶች ያለፈቃዳቸው እንደተስማሙ ተደርጎ የተቆረጠባቸው ሲሆን መምህራን ተቃውሞ በማንሳታቸው የመስከረም ወር ደሞዝ ሳይከፈላቸው አራት ቀናት መቆጠሩን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። መምህራኑ ደሞዛችን ካልተከፈለን አንሰራም በማለት ዛሬ ስራ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሶማሌ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤትና የቢሮ ሃላፊው በቅርቡ የሰጧቸው መግለጫዎች አፍራሽና ሕዝብን ጥርጣሬ ውስጥ የሚከቱ ናቸው ተባለ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010) የፌደራል መንግስት የኢትዮጵያ ሶማሌ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤትና የቢሮ ሃላፊው በቅርቡ የሰጧቸው መግለጫዎች አፍራሽና ሕዝብን ጥርጣሬ ውስጥ የሚከቱ ናቸው በሚል ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠነቀቀ። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የሶማሌ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት በኦሮሚያ ጥቃት ላይ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር የተደረገ የጋራ መግለጫ በሚል ያወጣው መግለጫ የፌደራሉ መንግስት ያስቀመጠውን አቅጣጫ የሚቃረን ነው። እናም የሚመለከተው አካል ይህንኑ ...

Read More »

አቶ አባዱላ ገመዳ መኖሪያቸውን እንዲለቁ መገደዳቸው ተሰማ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010) የአፈጉባኤነት ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለመተው መልቀቂያ ያቀረቡት አቶ አባዱላ ገመዳ መኖሪያቸውን እንዲለቁ መገደዳቸውን ምንጮች ገለጹ። ዛሬ በፓርላማ በመደበኛ ስራቸው ላይ የታዩት አቶ አባዱላ ገመዳ ሃላፊነታቸውን ለመልቀቅ መወሰናቸውንም ትላንት አረጋግጠዋል። ላለፉት አስር አመታት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤነት የቆዩት አቶ አባዱላ ገመዳ ከኦሮሚያና ከሶማሌው አዋሳኝ ድንበር ግጭት ጋር በተያያዘ የጸጥታ ሃይሉ ሚና እንዳላስደሰታቸውና ስልጣን ለመልቀቅም ምክንያት እንደሆናቸው አዲስ ስታንዳርድ ...

Read More »

ታዋቂው የባህል ሙዚቃ አቀንቃኝ ድምጻዊ ሀብተሚካኤል ደምሴ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010)ታዋቂው የባህል ሙዚቃ አቀንቃኝ ድምጻዊ ሀብተሚካኤል ደምሴ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ድምጻዊ ሀብተሚካኤል ደምሴ ከዚህ አለም በሞት የተለየው በደረሰበት የመኪና አደጋ ነው። ሀብተሚካኤል ደምሴ በአዲስ አበባ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አካባቢ ከሚያሽከረክረው መኪናው ወርዶ መንገድ በማቋረጥ ላይ ሳለ በአንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገጭቶ ሕይወቱ አልፏል። አደጋው የደረሰበት ዛሬ ሰኞ ከረፋዱ 4 ሰአት አካባቢ ነው። ከዚህ አለም ...

Read More »

በኢትዮጵያ የብሔር ተኮር ፖለቲካ ፈተና እየገጠመው ነው ተባለ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 26/2010)በኢትዮጵያ ባለፉት 26 አመታት የተተገበረው የብሔር ተኮር ፖለቲካ ፈተና እየገጠመው መሆኑን ታዋቂው የአለም አቀፍ መጽሔት ዘ ኢኮኖሚስት ዘገበ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የብሔር ግጭት የዳሰሰው ዘኢኮኖሚስት የክልል መንግስታት በፌደራል መንግስት ቁጥጥር የሚደረግባቸው ቢሆንም ከእጅ እያመለጡ ናቸው ብሏል። እናም የሕዝቡን አንድነት በማዳከም የጎሳ ፖለቲካን ሲያራምድ የቆየው የኢትዮጵያው አገዛዝ የማይወጣው ችግር ውስጥ እያስገባው መሆኑን ዘ ኢኮኖሚስት በሀተታው ዘርዝሯል። ...

Read More »

አንድ ጄኔራል የህወሃት አገዛዝን ከድተው በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቁ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 26/2010) በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በወታደራዊ ደህንነት ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩ አንድ ጄኔራል ስርአቱን ከድተው በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቁ። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ስርአቱን ከድተው በአሜሪካ የቀሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ጥሩነህ የተባሉ ከፍተኛ መኮንን ናቸው። ከወር በፊት በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ አዘጋጅነት በዋሽንግተን በተካሄደ ጸረ አይ ሲስ አለም አቀፍ ዘመቻ ላይ ከተገኙ የኢትዮጵያ ልኡካን አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ጥሩነህ ...

Read More »

የኒዩክለር ጦር መሳሪያን ለማስወገድ አለም አቀፍ ዘመቻ የተባለው ድርጅት የ2017 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸነፈ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 26/2010) የኒዩክለር ጦር መሳሪያን ለማስወገድ አለም አቀፍ ዘመቻ የተባለ ድርጅት የዘንድሮውን የ2017 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸነፈ። በምህጻረ ቃል ኢካን ተብሎ የሚታወቀው አለም አቀፍ ተቋም የዘንድሮው የሰላም ኖቤል አሸናፊ የሆነው የኒዩክለር አደጋ ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ ለአለም አደጋ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ነው። እናም ተቋሙ የጸረ ኒዩክለር ስምምነት እንዲኖር ላደረገው ጥረት ሽልማቱን ማግኘቱ ታውቋል። የኖቤል ሽልማቱን ያገኘው ተቋም በአውስትራሊያ ተመስርቶ በአሁኑ ...

Read More »

የአባይ ግድብ ግንባታ ጉዳይ ላይ የተደረገው ስምምነት ችግር እየገጠመው መሆኑን ግብጽ አስታወቀች

(ኢሳት ዜና–መስከረም 26/2010) ኢትዮጵያ በጀመረችው የአባይ ግድብ ግንባታ ጉዳይ ላይ የተደረገው ስምምነት ችግር እየገጠመው መሆኑን ግብጽ አስታወቀች። ግብጽ እንደምትለው የአባይ ግድብን በተመለከተ ከሱዳንና ከኢትዮጵያ ጋር የተካሄደው የሶስትዮሽ ስምምነት በአንዳንድ ምክንያቶች እየተስተጓጎለ ይገኛል። ጉዳዩን ይፋ ያደረጉት የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አጋጠሙ ስላሏቸው ችግሮች ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል። የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹኩሪ የሶስትዮሽ ስምምነቱን አደጋ ላይ የሚጥል እንቅፋት ማጋጠሙን ...

Read More »

በአሶሳ ዩኒቨርስቲ የተጠራው አጠቃላይ ስብሰባ በተቃውሞ ተቋረጠ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 25/2010)በአሶሳ ዩኒቨርስቲ የተጠራው አጠቃላይ ስብሰባ በተቃውሞ መቋረጡ ተሰማ። በዩኒቨርስቲው የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ከተማሪዎች ጋር ለመወያየት የተጠራው ስብሰባ ወደተቃውሞ መድረክ በመለወጡ መቀጠል ሳይችል ቀርቷል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ተማሪዎቹ ያነሷቸው ጥያቄዎች የፖለቲካና የአካዳሚክ ነጻነቶችን የተመለከቱ በመሆናቸውና ከሰብሳቢዎቹ አቅም በላይ በመሆኑ ስብሰባው ሊቋረጥ ችሏል። የአንድ ለአምስት አደረጃጀትን የተቃወሙት ተማሪዎቹ የትምህርት ጥራትንም አንስተው የኢትዮጵያ የወደፊት ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። የስብሰባው ዓላማ በሀገር ...

Read More »