(ኢሳት ዜና–ሕዳር 27/2010) የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ነባርና ታሪካዊ አካባቢዎችን ማፍረስ ጀመረ። ገዳም ሰፈርና ጌጃ ሰፈርን ጨምሮ አምስት ነባር ሰፈሮች ሙሉ ለሙሉ ይፈርሳሉ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2010 ከያዘው ከ40 ቢሊየን ብር አመታዊ በጀት ውስጥ 30 ቢሊየን ብሩን ከማዘጋጃ ቤትና ግብር ነክ ገቢዎችን ከሕብረተሰቡ በቀጥታ የሚሰበስበው መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ ገቢ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻውን የያዘው ነባር መሬቶችን በማስለቀቅ መሬቱን በመሸጥ የሚያገኘው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሕወሃት የተቋማትን ኮምፒዩተሮች ይሰልላል
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 27/2010) የሕወሃት የስለላ ተቋማት አንድ በእስራኤል የሚገኝ ድርጅት የሚያቀርበውን የስለላ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክን፣አንድ የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪንና የአንድ ጠበቃን ኮምፒዩተሮች ሲሰልል እንደነበር ሲትዝን ላብ የተባለው ተቋም አጋለጠ። በአሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያውያን ነጻ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ፣በግለሰቦችና ሌሎች ድርጅቶች ላይም የስለላ ተግባር መፈጸሙ ተጋልጧል። በሲትዝን ላብ የሚገኝ አንድ ግለሰብም የጥቃቱ ሰለባ መሆኑ ታውቋል። ሲትዝን ላብ እንደ ሕወሃት ያሉ አምባገነን ...
Read More »እስረኞች ከፍተኛ ማሰቃየት እየተፈጸመባቸው ነው
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 26/2010) በፖለቲካ ምክንያት ታስረው በወህኒ ቤት የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ ማሰቃየት እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገለጸ። ከጊዜያዊ ህመም እስከ ዘላቂ የአካል ጉዳት የደረሰ ቅጣት እንደሚፈጸምባቸውም እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች አረጋግጠዋል። በኢትዮጵያ እስር ቤቶች የሚፈጸሙና አሰቃቂ የሚባሉት ድርጊቶች ችሎት ፊት ሲቀርቡ ምናልባትም የህግ ባለሙያዎች መቀለጃ ወይንም የበለጠ ቅጣትን ማክበጃ ተደርገው ይወሰዳሉ። እንዲህ አይነቱ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚፈጸመው ደግሞ ምንም አይነት ወንጀል በሌለባቸው፣ወንጀል ሰርተው ...
Read More »አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ ተቃጠለ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 27/2010) በሰሜን ጎንደር አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ ተቃጠለ። በጭልጋ ወረዳ ነጋዴ ባህር አካባቢ ኳቤር ሎምዬ ቀበሌ ነዳጅ የጫነ ቦቴ መኪና ዛሬ ጠዋት የተቃጠለ ሲሆን፣ አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ለጥቃቱ ሃልፊነቱን ወስዷል። ነዳጁ ለአጋዚ ጦር የታሰበ በመሆኑ ርምጃውን መውሰዱን ንቅናቄው አስታውቋል። የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ነዳጅ የጫነ ቦቴ መቃጠሉን አረጋግጠው ቦቴው የጋየው ከዘራፊዎች ጋር በተደረገ ...
Read More »በ8 ሀገራት ላይ የተጣለው የጉዞ እገዳ ሕግ ጸደቀ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 26/2010) የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር የቀረበውንና በ8 ሀገራት ላይ የተጣለውን የጉዞ እገዳ ሕግ አጸደቀ። ውሳኔው ግን ይግባኝ ሊጠየቅበት እንደሚችል ሲታወቅ በሁለት ግዛቶች የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ውሳኔውን ለመቀልበስ ክርክር በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ባለፈው መስከረም ለሶስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ የቀረበውን የጉዞ እገዳ ሕግ ሙሉ ለሙሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሲያጸድቅ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ...
Read More »የኢሳት 7ኛ አመት በቦስተንና ሂውስተን ተከበረ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 26/2010) የኢሳት 7ኛ አመት በቦስተንና ሂውስተን ከተማ በድምቀት ተከበረ። የበአሉ ተሳታፊዎች ኢሳት የሚያደርገው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያለማቋረጥ ድጋፋችንን እናደርጋለን ሲሉ ቃል ገብተዋል። ባለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 2/2017 በሰሜን አሜሪካ ማሳቹሴትስ ግዛት ቦስተን ከተማና ቴክሳስ ግዛት ሂውስተን ከተማ የኢሳት 7ኛ አመት በርካታ የኢሳት ደጋፊዎች በተገኙበት ተከብሯል። ለኢሳት ማጠናከሪያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በእለቱ ተካሂዷል። በቴክሳስ ሂውስተን በተካሄደው ዝግጅት ላይ ላለፉት ...
Read More »የአጫሉ ሁንዴሳ የሙዚቃ ኮንሰርት ተሰረዘ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 26/2010) ታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ አጫሉ ሁንዴሳ በጊዮን ሆቴል ያዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት ተሰረዘ። የአዲስ አበባ አስተዳደር ለጉዳዩ በሰጠው ምላሽ የሙዚቃ ኮንሰርቱ የተሰረዘው በጸጥታ ችግር ምክንያት መሆኑን አመልክቷል። ታዋቂው ድምጻዊ አጫሉ ሁንዴሳ በግዮን ሆቴል ሊያካሂድ የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት መሰረዝ በርካታ ኢትዮጵያንን ያስቆጣ ሆኗል። የመንግስታትን ርምጃ በመቃወም በማህበራዊ ድረገጾች ከፍተኛ ትችቶች እየቀረቡ መሆናቸው ታውቋል። በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ በሆኑ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ...
Read More »በዶክተር መረራ ጉዲና ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ተሰጠ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 26/2010) የፌደራሉ አቃቢ ህግ በዶክተር መረራ ጉዲና ላይ ተጨማሪ ምስክሮችን ማቅረብ ባለመቻሉና በቀረቡት ማስረጃዎች ውሳኔ እንዲሰጠው በመጠየቁ ችሎቱ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጠ። በዶክተር መረራ ጉዲና ላይ የቀረቡት ምስክሮች ከቤታቸው ጽሁፎች ሲወሰዱ ማየታቸውን ከመግለጽ ውጪ ስለጽሁፎቹ ይዘትም ሆነ በሌላ ጉዳይ ላይ የሰጡት ምስክርነት አለመኖሩ ተገልጿል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ዶክተር መረራ ጉዲና በብይን በነጻ የመፈታታቸው ጉዳይ የሰፋ መሆኑን አንድ የህግ ...
Read More »በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች ተቃውሞ ተካሄደ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 26/2010) በበርካታ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ዛሬ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ። በአጋሮ ተማሪዎች አደባባይ ወተው የህወሀትን መንግስት አውግዘዋል። በባሌ ሮቤ መምህራን ተቃውሞ አሰምተዋል። በቦረና ዞን የሰላማዊ ሰው ግድያ እንዲቆም በመጠየቅ ሰልፍ ተደርጓል። በሀረር እስር ቤት በተነሳ ቃጠሎ በርካታ እስረኞች መጎዳታቸው ታውቋል። በሌላ በኩል በደቡብ ኦሞ በሙርሲ ታጣቂዎች 13 ሰዎች መገደላቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። በኦሮሚያ ክልል ዛሬም የህዝብ ንቅናቄ በበርካታ ...
Read More »ዜግነታቸው ለጊዜው ያልታወቀ ጎብኚ ተገደሉ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) በኢትዮጵያ አፋር ክልል ማንነታቸውና ዜግነታቸው ለጊዜው ያልታወቀ ጎብኚ ተገደሉ። ጎብኚውን ሲያዘዋውር የነበርው ሹፌርም መገደሉ ታውቋል። የኢሳት ምንጮች ከስፍራው እንደገለጹት ዛሬ በአፋር ክልል ኤርታሌ በተባለው ወረዳ የተገደሉት ጎብኚ ወደ ኤርታሌ እሳተ ጎመራ በመጓዝ ላይ ነበሩ። ወደ አካባቢው ሰርገው የገቡት ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች ከጎብኚው አጃቢዎችና ከአካባቢው ሃይሎች ጋር መጋጨታቸውም ታውቋል። ጎብኚው የተገደሉት በተኩስ ልውውጥ ይሁን አልያም ሆን ተብሎ ግን ...
Read More »