(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010) የሩዋንዳ መንግስት በሀገሪቱ ሺሻ እንዳይሸጥ እገዳ ጣለ። የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው እገዳው የተጣለው የአለም አቀፉን የጤና ድርጅት ምክር በመከተል ነው። ሩዋንዳ ሺሻን በማገድ በአፍሪካ ሁለተኛ ሀገር ሆናለች። ባለፈው አመት ሀምሌ ታንዛኒያ ሺሻን ማገዷ ይታወቃል። አለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO ሺሻ ለጤና እጅግ አደገኛና ጠንካራ ሱስ የሚያሲዝ ነው በሚል ሀገራት እገዳና ቁጥጥር እንዲያደርጉ በመወትወት ላይ ይገኛል። ሩዋንዳ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የቀድሞ መንግስት ባለስልጣን የዕድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010) በቀይ ሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በኔዘርላንድ ፍርድ ቤት የቀረቡት የቀድሞ መንግስት ባለስልጣን የዕድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው። በደርግ ዘመነ መንግስት በጎጃም ክፍለ ሃገር የደርግ ተጠሪ በነበሩበት ወቅት ለ75 ሰዎች መገደልና ለ200 ሰዎች መሰቃየት ተጠያቂ የተባሉት አቶ እሸቱ አለሙ ዘ ሔግ ኔዘርላንድ ውሳኔው የተላለፈባቸው ትላንት ሀሙስ መሆኑም ታውቋል። የ63 አመት እድሜ ያላቸው አቶ እሸቱ አለሙ በኔዘርላንድ ጥገኝነት አግኝተው መኖር የጀመሩት ...
Read More »ዳኛው ዘርአይ ወልደሰንበት ከችሎት እንዲነሱ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆነ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010) የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት የግራ ዳኛው ዘርአይ ወልደሰንበት ከችሎት እንዲነሱላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አደረገው። ተከሳሾቹ ዳኛው እኛ አማራ ስለሆንን ፍትሃዊ ዳኝነት እንገኛለን ብለን አናምን የሚል ቅሬታ አንስተዋል። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ዳኛው አማራ በዘሩ የማይኮራ፣በጎጥ የሚጠራ ህዝብ ነው ያሉት ሀሳብ ከተከሳሾቹ ጉዳዩ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ሲል ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት አስተባባሪ ...
Read More »ትምህርት ለማስጀመር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010) በኢትዮጵያ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስጀመር አገዛዙ በሀገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ተነገረ። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የዘር ልዩነት ያመጣውን አገዛዝ በመቃወም ድምጻቸውን በማሰማታቸው በአጋዚ ሃይሎች በመደብደባቸው ግቢውን እየጣሉ ወደ ቤታቸው አምርተዋል። በአማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርስቲዎች የተጎዱ ተማሪዎች ቁጥራቸው በርካታ ነው ተብሏል። በኢትዮጵያ ካሉ ከ30 በላይ ዩኒቨርስቲዎች ከ15 በላይ በሚሆኑት የመማር ማስተማር ሂደቱ ተቋርጧል። በተለይም ...
Read More »ተማሪዎች አደባባይ በመውጣት ሀዘናቸውን ገለጹ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010) የጨለንቆውን ጭፍጨፋ በማውገዝ የኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚማሩ ተማሪዎች አደባባይ በመውጣት ሀዘናቸውን ገለጹ። በተለይ በወለጋ ነቀምት ጥቁር ልብስ የለበሱት ተማሪዎች በሰልፍ ወጥተው ግድያውን በማውገዝ ላለቁት ወገኖች ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ከአንድ ቤተሰብ 5 ሰዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 18 ሰዎች የተገደሉበት የባለፈው ሰኞ የጨለንቆው ጭፍጨፋ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ግድያውን በማውገዝ በሂደቱ ተሳታፊ የሆኑትን ...
Read More »የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የሽግግር ሰነድ አቀረበ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010) የአውሮፓ ፓርላማ በጠራውና ኢትዮጵያን በተመለከተው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የሽግግር ሰነድ ማቅረቡ ተገለጸ። የሽግግር ሰነዱ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት አገዛዝ ከወደቀ በኋላ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሽግግር ስርዓት የሚያሳይ መሆኑ ተመልክቷል። በስብሰባው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራሮች ለኢሳት እንደገለጹት የአውሮፓ ፓርላማ የኢትዮጵያ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑን በመረዳት ከዚህ ቀደም ይከተለው የነበረውን አካሄድ በመተው የለውጥ ሃይሎች ...
Read More »የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ከነውዝግቡ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010) የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ መቀጠሉ ታወቀ። የደህንነቱ ዋና ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንዲፈርስ ጠይቀዋል። ብአዴንና ኦህዴድ ራሳችሁን አጥሩ በሚል በሕወሃት የቀረበው ሃሳብም ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። ይህ ከፍተኛ ውዝግብ ያስከተለው ስብሰባ ሸምጋዮች እንዲገቡበት የቀረበው ሃሳብም ውድቅ ተደርጓል። ስብሰባው ረዥም ጊዜያትን እንደሚወስድም ተገምቷል። ሆኖም ስብሰባው ሳያልቅ የማረጋጊያ መግለጫ በቀጣዮቹ ቀናት ይወጣል ተብሎም ...
Read More »በመላው የኦሮሚያ አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 5/2010) የጨለንቆውን ጭፍጨፋ በመቃወም በመላው የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። ተቃውሞው አዲስ አባባ ዙሪያ መድረሱንም ለማወቅ ተችሏል። በወለጋ ጊምቢና ነጆ፣ በጂማ በአጋሮና በአብዛኛው የምስራቅ ሀረርጌ ከተሞች ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል። በሞያሌ በአጋዚና በህዝቡ መሃል ግጭት ተፈጥሯል። በአምቦ የተገደሉ የአጋዚ ወታደሮች ቁጥር መጨመሩም እየተነገረ ነው። ዛሬ በኦሮሚያ ክልል የተካሄዱትን ተቃውሞች በተመለከተ የተዘጋጀውን ዝርዝር ዜና ብሩታዊት ግርማይ ታቀርበዋለች ባለፈው ሰኞ ...
Read More »ህዝባዊው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 5/2010) በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። በአይከል ከተማ ህዝቡ አደባባይ በመውጣት የህወሃትን አገዛዝ ማውገዙ ታውቋል። በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው በመውጣት ላይ ናቸው። ህወሀት ከስልጣን እንዲወርድ ተማሪዎቹ ጠይቀዋል። በጎንደር ዩኒቨርስቲ ዛሬም ትምህርት አልተጀመረም። አንድ የመንግስት ተሸከርካሪ ዩኒቨርስቲው ደጃፍ ላይ ወድሟል። በወልዲያ ከ70በመቶ በላይ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወተዋል። በኡርጌሳ ወሎ ህዝቡ ከአጋዚ ሰራዊት ጋር እንደተፋጠጠ መሆኑ ታውቋል። ...
Read More »ዚምባቡዌ መንግስቱ ሃይለማርያምን አሳልፌ አልሰጥም አለች
(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 5/2010) ዚምባቡዌ የቀድሞ የኢትዮጵያን ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሐይለማርያምን አሳልፋ እንደማትሰጥ አስታወቀች። የዚምባቡዌ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባለፈው ወር ሮበርት ሙጋቤ ከስልጣን ከተነሱ በኋላ ሀገሪቱ መንግስቱ ሃይለማርያምን ወደ ሀገራቸው እንድትሰድ በመጎትጎት ላይ ናቸው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም አጋርና ወዳጅ የሆኑት ሮበርት ሙጋቤ አሁን በስልጣን ላይ ባይሆኑም ዚምባቡዌ ኮለኔል መንግስቱን አሳልፋ እንደማትሰጥ አንድ የሀገሪቱ ባለስልጣን ማረጋገጫ ሰጥተዋል። የዚምባቡዌ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሙጋቤ ...
Read More »