(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2010) በኢራቅ በአይሲስ ተይዛ የነበረችውን ሞሱል ለማስለቀቅ በተደረገ ፍልሚያ እስከ 11 ሺ የሚደርሱ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የአሶሼትድ ፕሬስ የምርመራ ሪፖርት ይፋ አደረገ። ይህ አሃዝ ከዚህ በፊት ሲነገር ከነበረው በ10 እጥፍ እንደሚልቅም ታውቋል። በአሜሪካ የሚመራው ጥምር ጦር በኢራቅ ወታደራዊ ሃይል በአይሲስ ተይዛ የነበረችውን ሞሱልን ለማስለቀቅ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተደረገ ጥቃት ከ9ሺ እስከ 11ሺ ንጹሃን ሰዎች ማለቃቸውን የአሶሼትድ ፕሬስ የምርመራ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ማይክ ኮፍማን የራሱን ህዝብ የሚያሸብር መንግስት የኛ አጋር አይሆንም አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2010) የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ማይክ ኮፍማን የራሱን ህዝብ የሚያሸብር መንግስት የአሜሪካ አጋር መሆን አይገባውም ሲሉ ተናገሩ። ኮፍማን ይህንን ያሉት በአሜሪካ የኮሎራዶ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ዴንቨር ባለፈው ቅዳሜ ኤች አር 128 በመባል የሚታወቀውን ረቂቅ ህግ አስመልክቶ በተዘጋጀው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ነበር። ኢትዮጵያና አሜሪካ በጋራ የሚያደርጉት የጸረ ሽብር እንቅስቃሴ አደጋ ላይ ይወድቃል በሚል ማስፈራሪያ ህጉ እንዲጨናገፍ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ...
Read More »የሱዳን ጦር የሀገራችንን ድንበር መጣሱ አለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታሕሳስ 11/2010) የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የሱዳን ጦር የሀገራችንን ድንበር በመጣስ በቅርቡ የፈጸመው ወረራ አለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር ነው ሲል ለፕሬዝዳንት አልበሽር በጻፈው ደብዳቤ አሳሰበ። የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣም ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ለሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ይህን መሰል ደብዳቤ ሲጽፍ የመጀመሪያው አይደለም። የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ተላልፎ ተሰቷል ከተባለበት ጊዜ አንስቶ ጉዳዩ ያሳሰበው ...
Read More »የትግራይ ተወላጆች ማህበር የሀዘን መግለጫ አወጣ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/ 2010) ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በርካታ ዜጎች ሲገደሉ ድምጹን ያላሰማውና በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የትግራይ ተወላጆች ማህበር በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለተገደሉ ዜጎች የሀዘን መግለጫ ማውጣቱ ተሰማ። በርካታ ኢትዮጵያውያን በመከላከያ ሰራዊት፣ በፊደራል ፖሊስና በልዩ ሃይል ፓሊስ ሲገደሉ ድምጹን ያላሰማው ማህበር አሁን ላይ አለሁ ማለቱ በብዙዎች ዘንድ እንዲተች አድርጎታል። በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የትግራይ ተወላጆች ማህበር በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ...
Read More »ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2010) በሐገር ቤት የሚንቀሳቀሱ ሁለት ፓርቲዎችና በውጭ ሀገር የሚገኙ የተቃዋሚዎች ስብሰባ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ገለጹ። ሰማያዊ ፓርቲ እንዲሁም መኢአድና ሸንጎ በዋሽንግተን ዲሲ በሳምንቱ መጨረሻ ባካሄዱት ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል። ሁለቱ የሀገር ቤት ድርጅቶችና ሸንጎ በሚል አጭር መጠሪያ የሚታወቀው በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ስብሰባ በጋራ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በአደረጃጀት፣በፋይናንስ፣በአቅም ግንባታ፣አለም አቀፍ የፋይናንስ ድጋፍ ...
Read More »ተቃውሞው ዛሬም ቀጥሎ መዋሉ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2010) በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ዛሬ ተቃውሞ መካሄዱ ተገለጸ። በዱከም የቻይና የኢንዱስትሪ ዞን መመስረትን በመቃወም ሰልፍ ተካሄዷል። መቱ ለሶስተኛ ቀን ተቃውሞ ተደርጎባታል። በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ዛሬ ግጭት መፈጠሩም ታውቋል። በድሬዳው ዩኒቨርስቲ ዛሬ ግጭት መፈጠሩን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ባለፈው ሰኞ በርካታ ተማሪዎች የተጎዱበት ግጭት ከተከሰተ በኋላ ዩኒቨርስቲው በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ቢሆንም ዛሬም በተማሪዎች ተቃውሞ ተቀስቅሷል። በኢሉባቡር መቱ ለ3ኛ ቀን ...
Read More »ዶክተር ታደሰ ብሩ ነጻ ተባሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) በ8 ጉዳዮች በሽብር ወንጀል በእንግሊዝ መንግስት የተከሰሱት ታዋቂው ምሁርና ፖለቲከኛ ዶክተር ታደሰ ብሩ በተከሰሱባቸው ሁሉም ጉዳዮች ነጻ ተባሉ። ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የሀገሪቱ ፍርድ ቤት በሕዝብ በተመረጠ ዳኝነት/ጁሪ/ ዶክተር ታደሰ ብሩን በሙሉ ድምጽ ነጻ ናቸው ብሏል። ዶክተር ታደሰ ብሩ ሂደቱን ሲከታተሉና ሲጨነቁ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ምስጋና አቅርበዋል። ዶክተር ታደሰ ብሩ የተከሰሱት የሽብር ወንጀሎች ለምርምርና ለነጻነት ትግል የተጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክስ መጻሕፍትን ...
Read More »የሶማሌ ክልል ተወላጆች ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) ከ5ሺህ በላይ የሶማሌ ክልል ተወላጆች በምዕራብ ሀረርጌ ዞን በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ያለውሃና ምግብ በመቆየታቸው ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸው ተገለጸ። ሰሞኑን ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ የስልክም ሆነ የትራንስፖርት ግንኙነት ተቋርጧል። አስቸኳይ ድጋፍ ካልደረሰላቸው ዕልቂት ሊከሰት እንደሚችል በማስጠንቀቅ የሶማሌ ተወላጆች የአክቲቪስቶች መረብ መግለጫ አውጥቷል። በአራት ቀበሌዎች ተጠልለው የሚገኙ የሶማሌ ተወላጆችን ለመደገፍ የኦሮሞ ሽማግሌዎችና ወጣቶች ጥረት እያደረጉ መሆኑም ተገልጿል። በአካባቢው ሌላ ...
Read More »ሳውዳረቢያ የተተኮሰባትን ባሊስቲክ ሚሳኤል አመከነች
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) ሳውዳረቢያ ከሃውቲ አማጽያን የተተኮሰባትን ባሊስቲክ ሚሳኤል ሪያድ አቅራቢያ ማምከኗን አስታወቀች። የሃውቲው አል ማሲራህ ቴሌቪዥን እንዳለው በአማጽያኑ የተተኮሰው ሚሳኤል በአል-ያማማ ቤተመንግስት በስብሰባ ላይ የነበሩ የሳውዲ መሪዎችን ኢላማ ያደረገ ነበር። ሳውዳረቢያና አሜሪካ ኢራን የሃውቲ አማጽያንን ሚሳኤል ታስታጥቃለች ሲሉ ይከሳሉ። ኢራን ግን ክሱን ታስተባብላለች። ባለፈው ወርም ተመሳሳይ ሚሳኤል የሪያድን አይሮፕላን ማረፊያ ሊመታ ጥቂት ሲቀረው ነበር ተጠልፎ የወደቀው። የሃውቲ አማጽያን ላለፉት ...
Read More »በሃይማኖት አባቶች ስም እንቅስቃሴ ተጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የመከላከያ ሰራዊት ጣልቃ እንዲገባ በሃይማኖት አባቶች ስም እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑ ታወቀ። የኢሳት ምንጮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት የመከላከያ ሰራዊት ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያለ ክልሉ ፈቃድ እንዲገባ የሃይማኖት አባቶች ጥሪ እንዲያደርጉ ታዘዋል። የሃይማኖት አባቶች በቀጣዮቹ ቀናት በዚህ ዙሪያ የጋራ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። በፌደራልና በአርብቶ አደሮች ሚኒስቴር በኩል ለቀረበው ጥያቄ የሕወሃትና ...
Read More »