.የኢሳት አማርኛ ዜና

ወጣት ሰይፉ ዓለሙ በማእከላዊ እስር ቤት አካላዊና በማንነቱ ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እንደተፈጸሙበት ለፍርድ ቤት ተናገረ

ወጣት ሰይፉ ዓለሙ በማእከላዊ እስር ቤት አካላዊና በማንነቱ ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እንደተፈጸሙበት ለፍርድ ቤት ተናገረ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በሽብር ክስ የተከሰሰው ወጣት ሰይፉ ዓለሙ በማእከላዊ እስር ቤት ቆይታው ወቅት በምርመራ ሥም የተፈጸመበትን ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች አስመልክቶ ለ19ኛው ወንጀል ችሎት በአካል ቀርቦ አሰምቷል። ተከሳሹ ወጣት ሰይፉ ዓለሙ በማዕከላዊ እስር ቤት ቆይታው የደረሱበትን በደሎች አስመልክቶ ለችሎቱ ሲናገር ”በድብደባ ...

Read More »

በራሷ ችግር የተተበተበችው ኢትዮጵያ እኛን ለማደራደር ብቁ አይደለችም ስትል ደቡብ ሱዳን ገለጸች።

በራሷ ችግር የተተበተበችው ኢትዮጵያ እኛን ለማደራደር ብቁ አይደለችም ስትል ደቡብ ሱዳን ገለጸች። (ኢሳት ዜና ማጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ/ም) ደቡብ ሱዳን ይህን ያለችው፣ የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት በምህጻረ ቃሉ ኢጋድ፣ በደቡብ ሱዳን የእርስበርስ ግጭት ዙሪያ ለመምከር በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ ስብሰባ እንደሚቀመጥ ይፋ መሆኑን ተከትሎ ነው። ኢትዮጵያ በራሷ የውስጥ ችግር እየታመሰች ባለችበት ሁኔታ፣ ለሯሷ መፍትሄ በመፈለግ ፋንታ ለደቡብ ...

Read More »

ግሎባል አሊያንስ ከሞያሌ ለተፈናቀሉ ወገኖች 10 ሺ ዶላር ሰጠ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2010)በውጭ ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያቋቋሙት ግሎባል አሊያንስ /ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት /ከሞያሌ ተፈናቅለው ኬንያ ለገቡ ኢትዮጵያውያን የ10 ሺ ዶላር እርዳታ ሰጠ። በአሜሪካ ቀይመስቀል በኩል ወደ ኬንያ ለስደተኞች የሚላከውን ገንዘብ ትላንት ለአሜሪካ ቀይ መስቀል ያበረከቱት የትብብሩ ሰብሳቢ አቶ ታማኝ በየነና ሌሎች የትብብሩ አመራሮች መሆናቸውን መረዳት ተችሏል። መጋቢት 1 ቀን 2010 በመከላከያ ሰራዊት አባላት በሞያሌ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ...

Read More »

በባሌ ዞን ሕጻናትን ጨምሮ 5 የአንድ ቤተሰብ አባላት ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2010) በሶማሌ ክልል የልዩ ሐይል አባላት በኦሮሚያ ባሌ ዞን ሕጻናትን ጨምሮ 5 የአንድ ቤተሰብ አባላትን መገደላቸው ተነገረ። በሌላ ዜና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ በኦሮሚያ ክልል በሶስት አቅጣጫ ገብቷል በሚል በክልሉ አሰሳ እና እስራት መጠናከሩን ምንጮች  ለኢሳት ገለጸዋል። ለኢሳት በደረሰው መረጃ በነገሌ ቦረና ዞን ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው አሰሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከሞያሌ በ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የመከላከያ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ዞን በሮቢት ከተማ አካባቢ በሚካሄደው ውጊያ ነዋሪዎች መጎዳታቸው እንዲሁም የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ታወቀ

በሰሜን ጎንደር ዞን በሮቢት ከተማ አካባቢ በሚካሄደው ውጊያ ነዋሪዎች መጎዳታቸው እንዲሁም የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ታወቀ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ/ም) ዛሬ፣ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓም ከጎንደር ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ሮቢት ከተማ አካባቢ በሚገኙ የገጠር የቀበሌዎች፣ አገዛዙ በከባድ የጦር መሳሪያዎች የታጀበ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አሰማርቶ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ከወታደሮች በኩልም 7 ተገድለው ...

Read More »

ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ለደረሰው የሰውና የንብረት ውድመት ከፍተኛ አመራሩ ተጠያቂ ነው አለ

ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ለደረሰው የሰውና የንብረት ውድመት ከፍተኛ አመራሩ ተጠያቂ ነው አለ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮጵያ ለደረሰው የዜጎች እልቂት፣ የሚሊዮኖች መፈናቀልና ከፍተኛ ንብረት ውድመት የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ሃላፊነቱን ይወስዳል ሲል ፓርቲው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ድርጅቱ ሰሞኑን በሰጣቸው ተከታታይ መግለጫዎች፣ በኢትዮጵያ ለሚታዬው የጸጥታ መደፍረስ የቀለም አብዮት እንዲካሄድ የሚፈልጉ የምዕራብ አገራትንና ኤርትራን ተጠያቂ አድርጎ ነበር። ዛሬ ባወጣው መግለጫ ደግሞ ...

Read More »

በምስራቅ ሃረርጌ ነዋሪዎች በወታደራዊ አገዛዙ መማረራቸውን ገለጹ

በምስራቅ ሃረርጌ ነዋሪዎች በወታደራዊ አገዛዙ መማረራቸውን ገለጹ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በተለይ በኮምቦልቻ ከተማ ካለፈው እሁድ ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው ፍተሻ ፣ ነዋሪዎች ጥንድ ጥንድ ሆነው መጓዝ እንደማይችሉና ህጉን ጥሰው ቢገኙ ሊመቱ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። ሃዘን ቤት ተቀምጦ ማውራት፣ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በሁዋላ መዘዋወር እንዲሁም የተለያዩ የውጭ ጣቢያዎችን ማዬት እንደማይቻል እንደተነገራቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል። ካለፈው ...

Read More »

የግብጽና ሱዳን መሪዎች ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የጋራ ስምምነት ላይ ደረሱ

የግብጽና ሱዳን መሪዎች ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የጋራ ስምምነት ላይ ደረሱ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ/ም) የሱዳኑ መሪ ኦማር አልበሽር በግብጽ የአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። የፕሬዚዳንቱን ጉብኝት ተከትሎ ሁለቱ አገራት በ2015 እ.ኤ.አ. የተፈረመውን የአባይ ግድብ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ኢጅብት ቱዴይ ዘግቧል። የግብጹ ፕሬዚዳንት አልሲሲና የሱዳኑ አቻቸው ኦማር አልበሽር ከመገናኘታቸው በፊት የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮችና ...

Read More »

ኒኮላስ ሳርኮዚ በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2018) የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ዛሬ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ወደ ወህኒ ለመጋዝ ምክንያት የሆነባቸው ከቀድሞው የሊቢያ ፕሬዝዳንት ሙአመር ጋዳፊ መንግስት ለምርጫ ዘመቻ በሚሊየን ዮሮ የሚቆጠር ገንዘብ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ተቀብለዋል በሚል ነው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2007 ለተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊየን ዩሮ ተቀብለዋል በሚል የተወነጀሉት ሳርኮዚ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2013 ጀምሮ ምርመራ ሲካሄድባቸው ...

Read More »

አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመርን ማስቀጠል አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2010) አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመርን ማጠናከርና ማስቀጠል አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን የኢሕአዴግ ስራአስፈጻሚ ገለጸ። የኢህአዴግ ስራአስፈጻሚ ለ8 ቀናት ያካሄደውን የስራ አስፈጻሚ ግምገማ አጠናቆ የድርጅቱን አጠቃላይ የምክርቤት ስብሰባ ጀምሯል። ስራአስፈጻሚው ስብሰባውን ሲያጠናቀቅ ባወጣው መግለጫ እንዳለው ታዲያ በአመራሩ መካከል የነበረው የአመለካከት ልዩነት ወደ ተሻለ አንድነት እንዲመጣ አቅጣጫ ተቀምጧል። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመርን በሚያጠናከር መልኩ በአመራሩ መካከል የአመለካከት ...

Read More »