.የኢሳት አማርኛ ዜና

የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ መምህራን በወታደሩ ላይ የሰላ ትችት ሲያሰሙ አረፈዱ

የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ መምህራን በወታደሩ ላይ የሰላ ትችት ሲያሰሙ አረፈዱ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ዛሬ በቅጽል ስማቸው ጄኔራል ሾማ እየተባሉ በሚጠሩ ወታደራዊ አዛዥ እና በፕ/ር ጨመዳ ፊኒኒሳ በተመራው የመመህራንና የሰራተኞች ስብሰባ ፣ ሰራተኞቹ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ትችት ሲሰነዝሩ ውለዋል። ከጠዋት 2 ሰአት እስከ 6 ሰዓት በቆዬው ስብሰባ ተሰብሳቢዎቹ በስሜት ይናገሩ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። አንድ መምህር፣ “ክቡር ጄኔራል፣ ...

Read More »

የድል ሚድድ ደጋፊ ናቸው የተባሉ የኢትዮ-ሶማሊ ተወላጆች ቤተሰቦች አሁንም እየታሰሩ ነው

የድል ሚድድ ደጋፊ ናቸው የተባሉ የኢትዮ-ሶማሊ ተወላጆች ቤተሰቦች አሁንም እየታሰሩ ነው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) የሶማሊውን ክልል መሪ የአቶ አብዲ ኢሌን አገዛዝ ለመቃወምና በክልሉ ሰላምና ፍትህ እንዲሰፍን ለመታገል በውጭ የሚገኙ የሶማሊ ኢትዮጵያውያን ያቋቋሙትን ድል ሚድድ የተባለው ንቅናቄን ተከትሎ የንቅናቄው አባላትና አመራር ናቸው የተባሉ ቤተሰቦች እየተያዙ መታሰራቸው ቀጥሎአል። በቅርቡ በክልሉ ዱል ሚድድ የሚል እና ህዝቡ ለመብቱ እንዲነሳ የሚጠይቅ ...

Read More »

ከ150 ያላነሱ በአብዛኛው የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው የጉምሩክ ሰራተኞች ከስራ ተቀነሱ

ከ150 ያላነሱ በአብዛኛው የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው የጉምሩክ ሰራተኞች ከስራ ተቀነሱ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ከተቀነሱት ውስጥ 98 በመቶ የሚሆኑት የህወሃት ወታደሮች የነበሩ ናቸው። ብዙዎቹ የትምህርት ማስረጃቸው ብቁ አይደለም በሚል እንደተባረሩ ኢሳት ከደረሰው ደብዳቤ ለማወቅ ችለናል። ኢሳት ትናንት ባቀረበው ዘገባ በሶማሊ ክልል 38 የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው እና ከመከላከያ ወደ ጉምሩክ ተዛውረው ለ8 ዓመታት ሲሰሩ የነበሩ ሰራተኞች መቀነሳቸውን ጠቅሶ ...

Read More »

እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ከ16 ሚሊየን በላይ ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 14/2010)በኢትዮጵያ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ አስቸኳይ እርዳታዎች የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ከ16 ሚሊየን በላይ መድረሱን ለኢሳት የደረሰው የመንግስት ሰነድ አመለከተ። እስከ ታህሳስ 2011 ድረስ ይህ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ከተባሉት ውስጥ ከ6 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ዜጎች ናቸው ። ከሶማሌ ክልል ነዋሪዎች 80 በመቶው አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልጉ ናቸው ።          የኢትዮጵያ መንግስትና ከ80 በላይ እርዳታ ሰጪ ሃገራትና ተቋማት ...

Read More »

በሶማሊያ በደረሰ የቦንብ ጥቃት 14 ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 14/2010)በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በአንድ ሆቴል ላይ በደረሰ የቦንብ ጥቃት 14 ሰዎች ሞቱ። በመኪና ለይ ተጠምዶ ነበር በተባለው በዚህ የቦምብ ጥቃት በመዝናናት የነበሩ 6 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ሌሎች ተጨማሪ 8 ሰዎችም በአደጋው ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነም የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር ይችላል።  ለተፈጸመው የቦምብ ጥቃትም አልሻባብ ሀላፊነት መውሰዱን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል። ባለመረጋጋት ውስጥ በቆየችው ሶማሊያ በተለይ ...

Read More »

የሸካ ጥቅጥቅ ደን በእሳት ቃጠሎ እየወደመ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 14/2010) በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የባህልና የሳይንስ ተቋም ዩኔስኮ የተመዘገበው የሸካ ጥቅጥቅ ደን በእሳት ቃጠሎ እየወደመ መሆኑ ተገለጸ። እስካሁን 250 ሄክታር የሚሆነው የደኑ ይዞታ በእሳት የወደመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የአገዛዙ የመገናኛ ብዙሃን ደኑ በሰደድ እሳት መያያዙን ቢገልጹም የተፈጥሮ ሀብት ባለሙያዎች ግን የአካባቢው የአየር ንብረት ሰደድ እሳትን የሚፈጥር አይደለም ሲሉ ይከራከራሉ። የአከባቢው ህዝብ እሳቱን ለማጥፋት የሚችል ባለመሆኑ መንግስት በአስቸኳይ ደኑን ...

Read More »

አበበ ካሴ ከፍተኛ ስቃይ እየተፈጸመበት ነው

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 14/2010)በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ተከሶ በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኘው አበበ ካሴ ከፍተኛ ስቃይ እየተፈጸመበት መሆኑን ገለጸ።   ከ2006 ጀምሮ 7 አመት ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው አበበ ካሴ በተፈጸመበት ኢሰብአዊ ድርጊት ሽንቱን መቆጣጠር እንደማይችል ገልጿል። ከወልቃይት ማንነት ጋር በተያያዘ በእስር ቤቱ ሃላፊዎች አሁንም ድብደባ እየደረሰበት ነውም ተብሏል። አበበ ካሴ በአርበኞች ግንቦት ሰባት ስም ከተወነጀለበት ክስ ሌላ በአማራ ክልል ፍርድቤትም ...

Read More »

የወጪ ንግድ ገቢ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር በታች መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2010) በግማሽ አመት የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር በታች መሆኑ ተገለጸ። ምርት በመላክ የውጭ ምንዛሪ ከተገኘባቸው የአለማችን ሃገራት መካከል ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችው ሶማሊያ በሁለተኛ ደረጃ ተመዝግባለች። የመጀመሪያ ግማሽ አመት ሪፖርቱን ያመጣው የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ከወጪ ንግድ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ 1 ነጥብ 35 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር መሆኑን ይፋ አድርጓል። በሌላ በኩል በተጠቀሰው የበጀት ...

Read More »

የአማራ ክልል የሕዝብ ቁጥር እድገት እጅግ አዝጋሚ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 14/2010) የአማራ ክልል የሕዝብ ቁጥር እድገት እጅግ አዝጋሚ መሆኑን በኢትዮጵያው አገዛዝና በአለም አቀፍ ለጋሾች የቀረበ አንድ ሰነድ አመለከተ። በዚህ ሰነድ መሰረት በመጪው የሕዝብ ቆጠራ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተጨማሪ 3 ሚሊየን የአማራ ህዝብ ሊጠፋ እንደሚችል ተገምቷል። በሰነዱ እንደተመለከተው ለምግብ እጥረት የተጋለጡትን ለመለየት በተካሄደ የሕዝብ ቁጥር ትንበያ ጥናት የአማራ ክልል ነዋሪዎች 20 ነጥብ 5 ሚሊየን ብቻ ናቸው። የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ ...

Read More »

የስደተኞች ቁጥር ባለፈው ዓመት ብቻ ከ5ሺህ በላይ ነበር ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2010)ወደ አውሮፓ ሳይሻገሩ ባህር ላይ የሰመጡ ስደተኞች ቁጥር ባለፈው ዓመት ብቻ ከ5ሺህ በላይ እንደነበር ተዘገበ። ከወራት በፊት አንድ የጀርመን ጋዜጣ ባውጣው ዘገባ ከ33ሺህ የሚበልጡ ሟቾችን ዝርዝር ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ዴር ታግ ኢስፒግል የተባለው የጀርመን ጋዜጣ በቅርቡ ይፋ እንዳደረገው መረጃ ከሆነ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1993 ወዲህ ባለው ጊዜ ብቻ 33ሺ 293 ስደተኞች ወደ አውሮፓ ሊሻገሩ ሲሉ ባህር ውስጥ ሰምጠው ...

Read More »