(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 27/2010) በእንግሊዝ ሃይሎች ከኢትዮጵያ ተዘርፈው የተወሰዱ ቅርሶች በአደራ መልክ ሊመለሱ መሆኑ ተነገረ። አንድ ክፍለ ዘመን ሙሉ በእንግሊዝ ተዘርፈው የቆዩት የኢትዮጵያ ቅርሶች በእዳ መልክ ለተወሰነ ጊዜ ተመላሽ እንደሚደረጉ ታውቋል። በእንግሊዝ ሙዚየም የሚገኙ እነዚሁ ቅርሶች በአጼ ቴድሮስ ጊዜ ከመቅደላ የተዘረፉ መሆናቸውም ተነግሯል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1868 እንግሊዞች በአጼ ቴድሮስ የታሰሩ ዜጎቻቸውን ለማስለቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ሲዘምቱ የተመዘበሩ ቅርሶች በርካታ ናቸው። አጼ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሜጄር ጄኔራል ገብሬ አድሃና በአብዬ ግዛት ተሾሙ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 27/2010) ሜጄር ጄኔራል ገብሬ አድሃና በአብዬ ግዛት የሰላም አስከባሪው አዛዥ ሆነው በተባበሩት መንግስታት መሾማቸው ተገለጸ። የሕወሃቱ ታጋይ ጄኔራል ገብሬ አድሃና የሚተኩት ሌላውን የሕወሃት ታጋይ ሜጄር ጄኔራል ተስፋዬ ግደይን እንደሆነም ለመረዳት ተችሏል። የዚህ ተልዕኮ ምክትል አዛዥ ሆነው ተሹመው በመስራት ላይ የሚገኙትም ሌላዋ የሕወሃት ታጋይ ብርጋዴር ጄኔራል ዘውዱ ኪሮስ ናቸው ። ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በሚወዛገቡበት አቢዬ ግዛት ከተሰማራው 4ሺ ያህል ...
Read More »ሕዝቡ የጀመረውን እምቢተኝነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 27/2010)የኢትዮጵያ ሕዝብ የጀመረውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት አጠናክሮ እንዲቀጥል አለምአቀፍ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረ ሃይል ጥሪ አቀረበ። በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም የጀመሩትን የዲፕሎማሲ እና የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ትግሉን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቋል። አለም አቀፉ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረሃይል ባወጣው መግለጫ እንዳለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተስፋና በስጋት ጊዜ ላይ ይገኛል። በኢሕአዴግ ውስጥ የለውጥ አቀንቃኝነት ዝንባሌ ያላቸው ፖለቲከኞች ወደ ፊት አመራርነት መምጣታቸው እንደ ተስፋ ይታያል ነው ...
Read More »በአማራ ክልል የጦር መሳሪያ ለማስፈታት የተደረገው ዘመቻ ውጤታማ አይደለም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 27/2010)በአማራ ክልል የጦር መሳሪያ ለማስፈታት የተደረገው ዘመቻ ውጤታማ አለመሆኑን ተከትሎ ለሚሊሺያ ሰራዊት አባላት ጥሪ መደረጉ ተሰማ። ወደየቤተሰቦቻቸው የተበተኑት የሚሊሺያ አባላቱ በኮማንድ ፖስቱ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ መሳሪያ ወደ ማስፈታት ዘመቻ እንዲገቡ መታቀዱን የኢሳት ምንጮች ካደረሱን መረጃ ለማወቅ ተችሏል። የህወሀት አገዛዝ የአማራ ተወላጆችን በጦር መሳሪያ ማስፈታት ዘመቻ እርስ በእርስ ለማጋጨት ያቀደው ሴራ በመሆኑ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል። የህዝባዊ ወያኔ ...
Read More »የሶማሊው ፕሬዚዳንት አንቀጽ 39ን ተግባራዊ አደርገዋለሁ እያሉ በመዛት ላይ ናቸው
የሶማሊው ፕሬዚዳንት አንቀጽ 39ን ተግባራዊ አደርገዋለሁ እያሉ በመዛት ላይ ናቸው (ኢሳት ዜና መጋቢት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ደስተኛ ያልሆኑት የህወሃቱ ቀኝ እጅ አቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር የህገ መንግስቱን አንቀጽ 39ን በመጥቀስ የመገንጠል ጥያቄ አቀርባለሁ በማለት እየዛቱ ነው። አዲስ አበባ ውስጥ የነበሩ የክልሉ አገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም ፖለቲከኞች ወደ ጅጅጋ የተጠሩ ሲሆን፣ የልዩ ሃይል አዛዦች፣ የልዩ ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 11 ታዋቂ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ተፈቱ
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 11 ታዋቂ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ተፈቱ (ኢሳት ዜና መጋቢት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) መጋቢት 16 ቀን 2010 ዓም ታስረው የነበሩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ አዲሱ ጌታሁን፣ ጦማሪ ዘላለም ወርቅአገኘሁ፣ ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን፣ ጋዜጠኛ በፈቃዱ ሃይሉ፣ ወ/ት ወይንሸት ሞላ፣ ስንታየሁ ቸኮልና ተፈራ ተስፋዬ ዛሬ ተለቀዋል። ትናንት በመታወቂ ዋስ እንደሚፈቱ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ ዛሬ ...
Read More »ኦነግ የዶ/ር አብይን መመረጥ ወያኔ በኦሮሞ ላይ የሚደርሰውን ጭቆና ለማስፋፋት የወጠነው ማባበያ ነው አለ ከኢህአዴግ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑንም ገልጿል
ኦነግ የዶ/ር አብይን መመረጥ ወያኔ በኦሮሞ ላይ የሚደርሰውን ጭቆና ለማስፋፋት የወጠነው ማባበያ ነው አለ ከኢህአዴግ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑንም ገልጿል (ኢሳት ዜና መጋቢት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) ኦነግ በመግለጫው በ27 ዓመታት ኢህአዴግ ስርዓት አገዛዝ ዘመን ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ ችግር አለመፈታቱንና ወደ ባሰ ሁኔታ መሸጋገሩን ገልጾ፣ የወያኔ ስርዓት አስተማማኝ መፍትሄ ለማግኘት ከመስራት ይልቅ በማባበያና እውን በማይሆን ተስፋ ዓላመውን ማሳከቱን መርጧል ብሎአል። ...
Read More »የሰሜን ጎንደር የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ የዘር ፍሬያቸውን በመመታታቸው ለህመም እንደተዳረጉ ተናገሩ
የሰሜን ጎንደር የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ የዘር ፍሬያቸውን በመመታታቸው ለህመም እንደተዳረጉ ተናገሩ (ኢሳት ዜና መጋቢት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) አቶ ሙላት ፍሰሃ እንደተናገሩት በጎንደር የተካሄደውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ተይዘው ከታሰሩ በሁዋላ በማዕከላዊ እስር ቤት ሌሊት ሌሊት እየተጠሩ መደብደባቸውን ተናገሩ። “ቴዲ ከሚባል ሽፍታ ጋር ተገናኝተሃል፣ ከአርበኞች ግንቦት7 አመራሮች ጋር በመገናኘት በጎንደር ማረሚያ ቤት ላይ ጥቃት ልትፈጽም ነበር” ...
Read More »ሰዊዘርላንድ 300 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ መወሰኗን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኮነነ
ሰዊዘርላንድ 300 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ መወሰኗን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኮነነ (ኢሳት ዜና መጋቢት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) የስዊዘርላንድ መንግስት ጥገኝነት የጠየቁ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከኢትዮጵያ የደኅንነት ባለስልጣናት ጋር ስምምነት በማድረግ ወደ ትውልድ አገራቸው ለመመለስ ውሳኔ አሳልፏል። ውሳኔውን ተከትሎ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ድርጊቱን በመኮነን መግለጫ አውጥተዋል። ስደተኞቹ ካለምንም ሕጋዊ የጉዞ ሰነድ ወደ ስዊዘርላንድ የገቡ ቢሆንም፣ ...
Read More »የዩቱብ ህንጻ ላይ አንድ ሴት በከፈተችው ድንገተኛ ተኩስ 3 ሰዎች ቆሰሉ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 26/2010)በአሜሪካ ሳንፍራንሲስኮ በሚገኘው የ ዩቱብ ህንጻ ላይ አንድ ሴት በከፈተችው ድንገተኛ ተኩስ 3 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተሰማ። የ 39 አመቷ ናሲም አህዳም በፈጸመችው በዚህ ጥቃት ሶስት ሰዎችን ካቆሰለች በኋላ ራሷን ማጥፋቷንም ቢቢዚ በዘገባው አመልክቷል። እንደዘገባው ከሆነ ናሲም አህዳም ጥቃት ለማድረሷ ምክንያት ተደርጎ ለጊዜው የተቀመጠው በቅርብ ለራሷ የዩቲዩብ ማህበራዊ ድረገጽ የሰራችው ቪዲዮ መዘጋቱንና በዚህም ምክንያት ማግኘት ያለባትን ገንዘብ በማጣቷ ...
Read More »