የዩቱብ ህንጻ ላይ አንድ ሴት በከፈተችው ድንገተኛ ተኩስ 3 ሰዎች ቆሰሉ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 26/2010)በአሜሪካ ሳንፍራንሲስኮ በሚገኘው የ ዩቱብ ህንጻ ላይ አንድ ሴት በከፈተችው ድንገተኛ ተኩስ 3 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተሰማ።

የ 39 አመቷ ናሲም አህዳም በፈጸመችው በዚህ ጥቃት ሶስት ሰዎችን ካቆሰለች በኋላ ራሷን ማጥፋቷንም ቢቢዚ በዘገባው አመልክቷል።

እንደዘገባው ከሆነ ናሲም አህዳም ጥቃት ለማድረሷ ምክንያት ተደርጎ ለጊዜው የተቀመጠው በቅርብ ለራሷ የዩቲዩብ ማህበራዊ ድረገጽ የሰራችው ቪዲዮ መዘጋቱንና በዚህም ምክንያት ማግኘት ያለባትን ገንዘብ በማጣቷ ነው ተብሏል።

ጥቃቱን ከመፈጸሟ በፊትም በንዴት የተሞላ መልኦክቷን በማህበራዊ ድረገጾች ማስተላለፏም ታውቋል።

የናሲም አህዳምን ጥቃት በተመለከተም ተጨማሪ ምርመራዎች እየተደረጉ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።