(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 3/2010) በሶማሌ ክልል ተቃውሞው በመቀጠል በበርካታ ከተሞች ህዝባዊ ንቅናቄዎች ሲካሄዱ መዋላቸው ተገለጸ። በጅጅጋ የሚገኘው የክልሉ ጤና ኮሌጅ ተማሪዎችም ተቃውሞ መጀመራቸው ታውቋል። በቀብሪዳሃር፣ ድሬዳዋ፣ አዲጋላ፣ ቢኬ፣ ኤረርና ሌሎች ከተሞችም በተቃውሞ ውስጥ መዋላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በቀብሪዳሃር አንዲት ወጣት በልዩ ሃይሉ መገደሏን ተከትሎም የሕዝብ ቁጣ ተቀስቅሷል። በሌላ በኩል በአፋር ክልል የህዝባዊ ተቃውሞ ጥሪ ወረቀት መበተኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ህዝቡ ለፍትህና ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አቶ አባይ ጸሃዬን ጨምሮ አራት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተባረሩ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 3/2010)አቶ አባይ ጸሃዬን ጨምሮ አራት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተባረሩ። ለኢሳት በደረሰው የስንብት ደብዳቤ ላይ እንደተመለከተው አቶ አባይ ጸሀይን ጨምሮ አራቱ ባለስልጣናት ከስልጣናቸው የተነሱት ሚያዚያ 11 እና 12/ 2010 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጻፉት ደብዳቤ ነው። በሁለት ተከታታይ ቀናት የስንበት ደብዳቤ የደረሳቸው ባለስልጣናት ከአቶ አባይ ጸሐዬ በተጨማሪ ጠቅላይ ዐቃቢ ህጉ አቶ ጌታቸው አምባዬ፣ የመለስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ቴድሮስ ሐጎስ፣ ...
Read More »በጂግጂጋ ተማሪዎች ተቃውሞ አደረጉ
በጂግጂጋ ተማሪዎች ተቃውሞ አደረጉ (ኢሳት ዜና ግንቦት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) በሶማሊ ልዩ ሃይል በከፍተኛ ጥበቃ ስር በምትገኘው ጅግጅጋ የመጀመሪያውን ተቃውሞ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች አካሂደዋል:: ተማሪዎቹ ከቀኑ 10 ሰአት ላይ በጀመሩት ተቃውሞ ፣ የክልሉ ፕሬዚዳን አቶ አብዲሌ ከስልጣን እንዲወርድ ጠይቀዋል:: ተማሪዎቹ አብዲሌን የሚያወግዙ መፈክሮችን ሲያሰሙ፣ የልዩ ሃይል አባላት በፍጥነት በመግባት ተማሪዎች ተቃውሞውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል::
Read More »አምስት የህወሃት ሰላዮች ተገደሉ
አምስት የህወሃት ሰላዮች ተገደሉ (ኢሳት ዜና ግንቦት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በሶማሊላንድ እና አካባቢው በልዩ የስለላ ስራ ሰልጥነው መርጃዎችን ሲያቀብሉ የነበሩ 5 ሰላዮች መገደላቸውን ከደህነነት ምንጮች ለማወቅ ተችሏል:: የሰላዮቹ ጠርናፊ የነበረው አማኑኤል ኪሮስ የተባለው ሰው ድሬደዋ ውስጥ በምስራቅ እዝ አዛዥ ጄኔራል ማሾ መኖሪያ ሰፈር አካባቢ የተገደለ ሲሆን ፣ 11 ወታደሮችም ለጥየቃ በሚል ተይዘው ታስረዋል:: ግድያውን ማን እንደፈጸመው ...
Read More »ዶክተር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የ62 ተካሳሾች ክስ ተነሳ ክሳቸው ከተነሳላቸው መካከል 16 ተከሳሾች ወደ ዝዋይ ተወሰዱ::
ዶክተር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የ62 ተካሳሾች ክስ ተነሳ ክሳቸው ከተነሳላቸው መካከል 16 ተከሳሾች ወደ ዝዋይ ተወሰዱ:: (ኢሳት ዜና ግንቦት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሳምንት እንዲከላከሉ የተወሰነባቸው እነ ዶክተር ፍቅሩ ፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ማስረሻ ሰጠኝና ሌሎችም እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ይፈታሉ:: ይሁን እንጅ ዛሬ 16 እስረኞች በከባድ ጥበቃ ውስጥ ሆነው ወደ ዝዋይ ተወስደዋል፣ከተወሰዱት መካከል አግባውሰጠኝ ፣ፍቅረማርያምና ማስረሻ በካቴና መታሰራቸውታውቋል:: እስረኞቹ ሰሞኑን ...
Read More »መሬታቸው ከጥቅም ውጭ የሆኑ አርሶ አደሮች ጩኸታችንን የሚሰማን አጣን አሉ
መሬታቸው ከጥቅም ውጭ የሆኑ አርሶ አደሮች ጩኸታችንን የሚሰማን አጣን አሉ (ኢሳት ዜና ግንቦት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) በደቡብ ክልል፥ በጋሞ ጋፋ ዞን፥ የደምባ ጎፋ ወረዳ የጉራዴ ቀበሌ አርሶ አርሶ አደሮች ከኦቶሎ ሳውላ የመንገድ ሥራ ተቋራጭ በመንገድ ሥራው ምክንያት በእርሻቸው ላይ ጎርፍ በመለቀቁ ማሳቸው በደለል፥ አሸዋና ጠጠር ተሞልቷል :: እርሻችንን ማረስ አንችልም፥ ማሳችን ከጥቅም ውጭ ሆኗል የሚሉት አርሶ አደሮች፣ በተደጋጋሚ ለወረዳው ...
Read More »አይ ኤም ኤፍ ኢትዮጵያን የእዳ ጫና ከበዛባቸው አገራት ተርታ መደባት
አይ ኤም ኤፍ ኢትዮጵያን የእዳ ጫና ከበዛባቸው አገራት ተርታ መደባት (ኢሳት ዜና ግንቦት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) የአላማቀፉ የገንዘብ ድርጅት እንደሚለው ለአመታት መካከለኛ የእዳ ጫና ካለባቸው አገራት ስትመደብ የቆየችው ኢትዮጵያ ፣በዚህ አመት ከፍተኛ የውጭ እዳ ካለባቸው አገራት መካከል ተመድባለች:: እንደ ኢትዮጵያ አደጋ ውስጥ የገባችው ሌላዋ አገር ዛምቢያ ናት:: ኢትዮጵያ በተለይ ከግል ባንኮች የምትበደረው ገንዘብ እየጨመረ መምጣት አሳሳቢ መሆኑን ድርጅቱ ጠቅሷል:: ...
Read More »በዶሃ በተካሄደው የሩጫ ውድድር ኮከብ የሌለው ባንዲራ የያዙ ኢትዮጵያውያን ማስጠንቀቂያ ደረሳቸው
በዶሃ በተካሄደው የሩጫ ውድድር ኮከብ የሌለው ባንዲራ የያዙ ኢትዮጵያውያን ማስጠንቀቂያ ደረሳቸው (ኢሳት ዜና ግንቦት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) በካታር ዶሃ በተደረገው የዲያመንድ ሊግ የሩጫ ውድድር ኮከብ የሌለበትን ባንዲራ የያዙ ኢትዮጵያውያን ከአገዛዙ ደጋፊዎችና የደህንነት ሰዎች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተው ነበር:: ኢትዮጵያውያኑ ወያኔን የሚቃወሙ መፈክሮችንም አሰምተዋል:: በተቃውሞው የተበሳጨው አገዛዙ ዶሃ ቀመር በሚገኘው ኢምባሲው አማካኝነት መግለጫ አውጥቷል :: በመግለጫውም በኩዋታር ውስጥ በሚደረግ ማንኛውም ...
Read More »ትናንት ሀሙስ እስራኤል በፈጸመችው ግዙፍ ጥቃት የተቆጣችው ኢራን ፣“ሶሪያ ራሷን የመከላከል መብት አላት” ስትል አስታወቀች።
ትናንት ሀሙስ እስራኤል በፈጸመችው ግዙፍ ጥቃት የተቆጣችው ኢራን ፣“ሶሪያ ራሷን የመከላከል መብት አላት” ስትል አስታወቀች። (ኢሳት ዜና ግንቦት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) እስራኤል በትናንቱ ጥቃት ሶሪያ ውስጥ ያሉ የኢራን ወታደራዊ ቤዞችን እንዳውደመች ነው የገለጸችው። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ባወጣው መግለጫ የእስራኤል ድርጊት የሶሪያን ሉዓላዊነት የጣሰ ነው በማለት የእስራኤልን ድርጉት አውግዟል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ፣ ጥቃቱ ላለፉት አስር ዓመታት እስራኤል ሶሪያ ...
Read More »የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር በእድሜ ረጅሙ መሪ ሆኑ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 2/2010) በጡረታ ተገለው የነበሩት የቀድሞ የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር በድጋሚ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ። ከ15 አመት በኋላ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱ መንበር የተመለሱት ሞሃታሂር ሞሃመድ የአለም የመጀመሪያው የእድሜ ባለጸጋው የሃገር መሪ ሆነዋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2003 በጡረታ የተገለሉትና የ92 አመት የእድሜ ባለጸጋው ሞሃታሂር የፓርላማውን 113 መቀመጫ በማግኘት ማሸነፋቸው ደግሞ ሌላ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል። ከ2 አስርት አመታት በኋላ ማሌዢያ የቀድሞ ...
Read More »