በዶሃ በተካሄደው የሩጫ ውድድር ኮከብ የሌለው ባንዲራ የያዙ ኢትዮጵያውያን ማስጠንቀቂያ ደረሳቸው

በዶሃ በተካሄደው የሩጫ ውድድር ኮከብ የሌለው ባንዲራ የያዙ ኢትዮጵያውያን ማስጠንቀቂያ ደረሳቸው
(ኢሳት ዜና ግንቦት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) በካታር ዶሃ በተደረገው የዲያመንድ ሊግ የሩጫ ውድድር ኮከብ የሌለበትን ባንዲራ የያዙ ኢትዮጵያውያን ከአገዛዙ ደጋፊዎችና የደህንነት ሰዎች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተው ነበር::
ኢትዮጵያውያኑ ወያኔን የሚቃወሙ መፈክሮችንም አሰምተዋል:: በተቃውሞው የተበሳጨው አገዛዙ ዶሃ ቀመር በሚገኘው ኢምባሲው አማካኝነት መግለጫ አውጥቷል ::
በመግለጫውም በኩዋታር ውስጥ በሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ውስጥ ኮከብ የሌለውን ባንዲራ ይዞ በሚገኝ ኢትዮጵያዊ ላይ በኳታር እና በኢትዮጵያ ህግ መሰረት እንጠይቃለን ብሏል፣ ህገመንግስቱን ለማስከበር ከኳታር መንግስት ጋር ተባብረን እንሰራለን ሲል አስጠንቅቋል:: ኢምባሲው በሰው አገር እንዲህ አይነት መግለጫ ማውጣቱን ኢትዮጵያኖች አሳፋሪ ብለ ውታል::
በአሜሪካ፣አውሮፓና ሌሎችም አገራት ተመሳሳይ ባንዲራዎች ሲያዙ ለምን ዝምታን መረጠ ሲሉም ጠይቀዋል ::