(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 9/2010) ጣሊያን 450 ስደተኞች በሲሲሊ እንዲያርፉ ፈቀደች። ጣሊያን ውሳኔውን ያሳለፈችው ፈረንሳይ፣ፖርቹጋል፣ማልታ፣ጀርመንና ስፔን እያንዳንዳቸው 50 ስደተኞችን እንወስዳለን ማለታቸውን ተከትሎ ነው። በሲሲሊ ደሴት በፖዛሎ የወደብ ዳርቻ እንዲያርፉ የተደረጉት 57 ሕጻናትና ሴቶች ብቻ መሆናቸው ታውቋል። በደሴቷ እንዲያርፉ የተደረጉት ስደተኞቹ በሁለት ጀልባዎች ተጭነው ሲጓዙ የነበሩና በነፍስ አድን ሰራተኞች ከሜዲትራኒያን ባህል ላይ ሕይወታቸው የተረፈ መሆኑንም ዘገባው አመልክቷል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ አዲሱ የጣሊያን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ወሰኑ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 9/2010) በኤርትራ ትጥቅ ትግል ሲያካሂዱ የነበሩ ሁለት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ መወሰናቸውን አስታወቁ። የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ/አዲሃን/ እና የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ትህዴን/ባወጡት መግለጫ በኤርትራ ሲያካሂዱ የነበረውን የትጥቅ ትግል በማቆም በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ወስነዋል። ለሁለቱም ድርጅቶች እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ምክንያት የሆናቸው በኢትዮጵያ እየተካሄ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ ተስፋ የሚሰጥ በመሆኑ ነው ብለዋል።
Read More »የፌደራል የጸጥታ አካላት ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጥሩ ትዕዛዝ ተላለፈ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 9/2010) በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ የፌደራል የጸጥታ አካላት በአፋጣኝ ገብተው ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጥሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ትዕዛዝ ሰጡ። ሁለቱም ክልሎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ መሰረት የጸጥታ አካላት እንዲገቡም ስምምነታቸውን መግለጻቸው ተመልክቷል። ለመቶሺዎች መፈናቀል፣ ለብዙዎች ሞትና አካል መጉዳል ምክንያት የሆነው ግጭት ከአመት በላይ ዘላቂ መፍትሔ ሳያገኝ ቆይቷል። ይህንን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታት የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊቱ የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት ...
Read More »ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ወደ አስመራ ተመለሱ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 9/2010)ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ በኢትዮጵያ ያደረጉትን የሶስት ቀናት ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ወደ አስመራ ተመለሱ። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ የአዲስ አበባውን የኤርትራ ኤምባሲ በይፋ እንደገና መክፈታቸውም ታውቋል። በአዲስ አበባና በሃዋሳ ጎዳናዎች ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸውና በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው ስነስርአት ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ወደ አስመራ ሲመለሱ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል። ቅዳሜ ማለዳ ከ20 አመታት በኋላ አዲስ አበባ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ...
Read More »በግብጽ 37 ግለሰቦች ላይ የእስር ቅጣት ማስተላለፉ ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 5/2010) የግብጽ ፍርድ ቤት በሰው አካል ንግድ ላይ ተሰማርተው ተገኝተዋል ባላቸው 37 ግለሰቦች ላይ የእስር ቅጣት ማስተላለፉ ተሰማ። በሃገሪቱ የሚታተም አንድ ጋዜጣ ለንባብ እንዳበቃው የካይሮ ፍርድ ቤት በወንጀሉ ተሳትፈዋል ባላቸው ግለሰቦች ላይ ከ 7- 15 አመት ቅጣት ማስተላለፉን አስነብቧል። ከተከሳሾቹ መካከል በህገወጥ የአካል ዝውውሩ ላይ የጤና ባለሙያዎችም እንደሚገኙበት ታውቋል። እንደ ጋዜጣው ዘገባ ከሆነም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ...
Read More »ጄኔራልነት አብርሃ ወልደማርያም በጡረታ መሰናበታቸው ተረጋገጠ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) በቅርቡ የሙሉ ጄኔራልነት ማዕረግ ከተሰጣቸው የጦር አዛዦች አንዱ አብርሃ ወልደማርያም በጡረታ መሰናበታቸው ተረጋገጠ። ኢሳት ባገኘው መረጃ መሰረት ጄኔራል አብርሃ ወልደማርያም ከሰኞ ሰኔ 25/2010 ጀምሮ ከሰራዊቱ በጡረታ ተሰናብተዋል። ጄኔራል አብርሃ ወልደማርያም ለረጅም አመታት የምስራቅ እዝ አዛዥ ሆነው በሶማሌ ክልል ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ሲያደርጉ መቆየታቸውም ይነገራል። ጄኔራሉ በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ በከፍተኛ የኮንትሮባንድ ንግድ የከበሩና እጅግ የተንደላቀቀ ዘመናዊ ...
Read More »የጎዛምን ሆቴል ባለቤት ለሕዝብና ለሃገር እጨነቃለሁ አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) በደብረማርቆስ አቶ በረከት ስምኦን ታይተዋል በሚል ጉዳት የደረሰበት የጎዛምን ሆቴል ባለቤት ከንብረታቸው ይልቅ ለሕዝብና ለሃገር እንደሚጨነቁ ገለጹ። የሆቴሉ ባለቤት ዶክተር ምንውየለት ሞሴ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት ሆቴሉን በትውልድ አካባቢውያቸው የገነቡት ሕዝቡ እንዲጠቀምና ሀገርን ለማሳደግ ነው። ከ40 አመታት በላይ በውጭ ሀገር የኖሩትና በተለያዩ የስራ ሃላፊነት ላይ የቆዩት ዶክተር ምንውየለት ሞሴ ሕዝቡ በኢትዮጵያ ፍትህ እስኪሰፍንና እኩልነት እስኪረጋገጥ ...
Read More »አምባሳደሮች ተሾሙ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማና አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ጨምሮ 8 ባለስልጣናት በአምባሳደርነት ተሾሙ። የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ስምንቱ ተሿሚዎች በየትኛው ሃገር እንደሚወከሉ ዝርዝሩ ባይገለጽም ሹመቱን ግን ዛሬ ማግኘታቸው ታውቋል። የደኢሕዴን ሊቀመንበርነታቸውን በቅርቡ የለቀቁትና የግብርና ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ፣አቶ አለማየሁ ተገኑ፣አቶ እሸቱ ደሴ፣አቶ አዛናው ታደሰ ከተሿሚዎቹ ዝርዝር ውስጥ ...
Read More »በቂሊንጦ እስር ቤት የእሳት ቃጠሎ ደረሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) በቂሊንጦ እስር ቤት የእሳት ቃጠሎ መድረሱ ተነገረ። በእስር ቤቱ የእንፈታ ጥያቄ ያቀረቡ ዜጎች ላይ አስለቃሽ ጋዝ ሲተኮስ እንደነበርና የቦምብ ፍንዳታም መሰማቱ ተነግሯል። እስረኞቹን ለመጠየቅ የመጡ ሰዎች በፖሊስ እንደተደበደቡ ለማወቅ ተችሏል። በቂሊንጦ እስር ቤት እስረኞች የእንፈታ ጥያቄ አቅርበው ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል። እስረኞቹ የኦነግና የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት በሚል ታስረው ከነበሩት መካከል መሆናቸውም ታውቋል። ድሃ በመሆናችንና ታዋቂ ባለመሆናችን ከእስር ...
Read More »ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ነገ ወደ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ነገ አዲስ አበባ እንደሚገቡ መንግስት ይፋ አደረገ። የአዲስ አበባና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ለኤርትራው መሪ አቀባበል እንዲያደርጉላቸውም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል። የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ከቅዳሜ ሐምሌ 7/2008 ጀምሮ እስከ ሰኞ ሐምሌ 9/2010 ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ቆይታ እንደሚያደርጉም ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦርነት ከፈነዳበት ግዜ ጀምሮ እንዲሁም ...
Read More »