ጥር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቡና ላኪዎች ባለባቸዉ የዉስጥ ችግር ምክንያት መንግሰት በዘንድሮዉ አመት ከያዘዉ 270ሺህ ቶን አመታዊ እቅድ ዉስጥ 25 በመቶ ያህሉን እንኳ እስካለፈዉ 2ኛዉ ሩብ አመት መጨረሻ ድረስ ለዉጭ ገበያ ማቅረብ እንዳልቻለ አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘገበ። ይኸዉ ሁኔታ ያስደነገጣቸዉ የንግድ ሚኒስትሩ ከበደ ካሳና በሚኒስትር ማእረግ ያሉት ያእቆብ ያላ ባለፈዉ ሳምንት ዉስጥ ከኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር መሪዎች ጋር ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያ በሶማሊያ በአልሸባብ ላይ አዲስ የዉጊያ ቀጠና መክፈቷ ታወቀ
ጥር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግሰት ወታደሮች የአልሸባብ ተዋጊዎች ጠንካራ ምሽግ ወደ ሆነዉ ቁልፍ አካባቢ በመግባት አዲስ የዉጊያ ቀጣና በመክፈት ላይ እንዳሉ የአይን ምስክሮች ገልፀዋል። ዶሎዉ በተባለዉ የድንበር ከተማ በኩል ወደ ሶማሊያ የገባዉ የኢትዮጵያ ጦር በደቡብ ምእራብ ጌዶ ክልል ወደ ሚገኘዉ ለክ ከተማ እንዲሁም ባይ እና ባኩል ወደ ተባሉት በአልሸባብ ቁጥጥር ስር ወደሚገኙት አካባቢዎች እንዳመራ ታዉቋል። በኢትዮጵያ ፤ ...
Read More »የአቶ መለስ ዜናዊ አያት የባሻ አስረስ ተሰማ ፎቶ ግራፍ በፌስ ቡክ እየተሰራጨ ነው
ጥር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ይህ በፌስ ቡክ፦”shocking photo ”(አስደንጋጭ ፎቶ” ) በሚል ርዕስ ስር የተለቀቀው የአቶ መለስ ዜናዊ አያት የባሻ አስረስ ፎቶ፤ ባሻ አስረስ ከጣሊያን ቅኝ ገዥዎች ሹመት በተቀበሉበት ቀን የተነሱት ነው ። በፎቶው ላይ የአቶ መለስ አያት ባሻ አስረስ ተሰማ፤ ሹመት በሰጧቸው የጣሊያን የጦር አዛዥ ጎን ቆመውና በተከታዮቻቸው ታጅበው ይታያሉ። አቶ ገብረመድህን አርአያን ጨምሮ የአቶ መለስ ዜናዊን ...
Read More »የሱዳን የጦር መኮንኖች ለፕሬዝዳንት አልበሽርና ለመከላከያ ሚኒስትራቸዉ ማስጠንቀቂያ ሰጡ
ጥር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ደቡብ ሱዳንን ለመዉጋት ከሚያደርጉት ችኮላ እንዲቆጠቡና ሌሎችም ወታደራዊና ፖለቲካዊ ማሻሻያዎችን እንዲያደርጉ ለአልበሽርና ለመከላከያ ሚነስትራቸዉ ፣ ለአብዱል ረህማን መሃመድ ሁሴን ማስጠንቀቂያዉን የሰጡት ፣ ቁጥራቸዉ 700 የሚሆኑ የሱዳን የጦር ሃይል መኮንኖች እንደሆኑ ሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ዘግቧል። ከደቡብ ሱዳን ጋር ባለ ችግር ምክንያት ወደ ጦርነት ሊገቡ እንደሚችሉ ፕሬዝዳንቱና የመከላከያ ሚኒስትሩ ለጦር መኮንኖቹ ገለፃ ባደረጉበት ወቅት ፣ መኮንኖቹ ...
Read More »ሰሞኑን የምግብና ሌሎች የምግብ ነክ እቃዎች ዋጋ ማሻቀቡን ዘጋቢዎቻችን ገለጡ
ጥር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደገለጡት በጥር ወር ጤፍ በተለምዶ የሚቀንስ ቢሆንም፣ በዚህ አመት ግን ይህ አልሆነም። ሰሞኑን በምግብ እህል ላይ ከ50 ብር ያላነሰ ጭማሪ ታይቷል። የጤፍ ዋጋ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተማዎችም ከ950 ጀምሮ በመሸጥ ላይ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ደግሞ ከ1 ሺ 100 ብር ጀምሮ እየተሸጠ ነው። ወትሮውኑ በቆሎ እስከ 400 ብር በመሸጥ ላይ ...
Read More »የምርጫ ቦርድ፤ የአዋጁን መመዘኛ አሟልተው በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለት ብቻ ናቸው አለ
ጥር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ፤ የአዋጁን መመዘኛ አሟልተው በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለት ብቻ ናቸው። እነሱም ኢህአዴግና የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ብቻ ናቸው” ሲል ሌሎቹን ፓርቲዎች አስጠነቀቀ። የኢህአዴግ ታማኝ ተቃዋሚዎችን ብቻ ያካተተ የውይይት የክርክር መድረክ መዘጋጀቱ፤ተቃውሞ አስነሳ። “በምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ዓ.ም መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ፣ የማደራጀት፣ የመከታተል፣ የመቆጣጠርና የመደገፍ ኃላፊነት አለኝ”ያለው ምርጫ ቦርድ፤ ብዙዎቹ ...
Read More »ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሶስተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ገለጠ
ጥር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ንቅናቄው ለኢሳት በላከው መግለጫ ፤ በኢትዮጵያ፣ እንዲሁም በውጭ አገራት ውስጥ በአፍሪቃ፣ በአውስትራሊያ፣ በሩቅና መካከለኛው ምሥራቅ፣ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ አባሎቹ ከጥር 12 ቀን እስከ 19 ድረስ ባደረጉት ሶስተኛ ጠቅላላ ጉባኤ የንቅናቀያቸውን ሪፖርቶች አዳምጠው በጥንካሬዎችና ድክመቶች ላይ ግልጽና ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጧል። ግንቦት 7 ለኢትዮጵያዊያን ተስፋን የፈነጠቀ፤ በወያኔ ላይ ደግሞ ስጋትን ያሰፈነ ድርጅት መሆን ...
Read More »ኒኮላስ ዲ ክርስቶፍ መለስ ዜናዊ በወሰደው የጭካኔ እርምጃ የዓለምን የመገናኛ ብዙሀን ትኩረት የበለጠ ከመሳብ ውጭ ጸጥ ሊያሰኝ አይችልም አለ
ጥር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው የዘ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ አምደኛ የሆነው ኒኮላስ ዲ ክርስቶፍ መለስ ዜናዊ በስዊድን፣ አሜሪካና ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ላይ በወሰደው የጭካኔ እርምጃ የአለምን የመገናኛ ብዙሀን ትኩረት የበለጠ ከመሳብ ውጭ ጸጥ ሊያሰኝ አይችልም ብሎአል። ኒኮላስ ዲ ክርስቶፍ እንደጻፈው አስቀያሚ በሆነው የኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ ቅማል፣ ቁንጫና አይጥ በሞላበት እስር ቤት ውስጥ ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብየ እና ጋዜጠኛ ጆን ...
Read More »የፌደራል ፖሊስ አባላት ስራቸውን በገፍ መልቀቅ ያሳሰበው መንግስት ጥለው የሚጠፉ ፖሊሶችን ማሰር ጀመረ
ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከታማኝ የፌደራል ፖሊስ ምንጮች ባገኘነው መረጃ በመላ አገሪቱ የሚገኙ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ስራቸውን እየለቀቁ ነው። ባለፈው ወር ብቻ ከ100 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት ስራ መልቀቃቸው ያስደነገጠው መንግስት፣ ያለፈቃድ ጥለው የሚጠፉትን እያደነ በማሰር ላይ ነው። ምንም እንኳ በትክክል የታሰሩ ፖሊሶችን ቁጥር ማግኘት ባይቻልም፣ በእየ ክፍለሀገሩና በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ውስጥ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች ታስረው ...
Read More »የሶማሊንና የኦሮሚያን የክልል መንግስታት እያወዛገበ ያለው የሞያሌን ከተማ እና አካባቢውን አስተዳደር በፌደራል መንግስቱ ስር ለማስገባት እንቅስቃሴ ተጀመረ
ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሶማሊንና የኦሮሚያን የክልል መንግስታት እያወዛገበ ያለውና በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት በርካታ ዜጎች ለሞትና ለስደት የሚዳረጉበትን የሞያሌን ከተማ እና አካባቢውን አስተዳደር በፌደራል መንግስቱ ስር ለማስገባት እንቅስቃሴ ተጀመረ:: የኢሳት የሞያሌ ምንጮች እንደገለጡት ከወራት በፊት በሶማሊና በኦሮሚያ ብሄሮች መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ በከተማዋ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መጠን የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው ተሰማርቷል። በአሁኑ ጊዜም በቦረና እና በገሪ ጎሳዎች መካከል ...
Read More »