.የኢሳት አማርኛ ዜና

ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ቧንቧ መስመር ለመዘርጋት ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ተፈራረመች

የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጅቡቲ ወደብ በኩል ነዳጅ ለዉጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችላትን የቧንቧ መስመር በኢትዮጵያ ለመዘርጋት ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟ ተዘግቧል። የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ለአሶስየትድ ፕሬስ የዜና አገልግሎት እንደገለፁት የቧንቧ መስመሩ ባለቤት ደቡብ ሱዳን እንደምትሆንና መስመሩ በኢትዮጵያ በኩል ወደ ጅቡቲ የሚተላለፍበት ተጨማሪ እንደሚሆን ተናግረዋል። የሁለቱ መንግስታት ባለስልጣኖች በወሩ መጀመሪያ ላይ በአዲስ አበባ ላይ የመግባቢያ ...

Read More »

አልሸባብ አልቃይዳን በይፋ መቀላቀሉ ተገለፀ

የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአልቃይዳዉ መሪ በእስልምና ተከታዮች ፎረም ላይ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰዉ አልሸባብ በፀረ ፅዮናዊነት የሚደረገዉን የጅሃድ ዘመቻ በመቀላቀል የአልቃይዳ አባል መሆኑ እሳቸዉንና እምነት ያላቸዉን እንደሚያስደስት፤ በተቃራኒዉ እምነት የሌላቸዉን ሊያስደነግጥ እንደሚችል ተናግረዋል። የአልቃይዳዉ መሪ በተጨማሪ በሶማሊያ የሚገኙ የእስልምና ተከታዮች ዉሸትን የሚሰብኩትንና ንፁህ በሆነዉ የእስላም ምድር ላይ ይህን መአት ያመጡትን ደካማ የሶማሊያ መሪዎች እንዳይቀበሏቸዉ ጥሪ አድርገዋል። ...

Read More »

የአፍሪቃ ቀንድ አሁንም ለረሃብና ለምግብ እጥረት የተጋለጠ እንደሆነ ጥናቶች አረጋገጡ

የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአፍሪቃ ቀንድ ቁጥሩ 13 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ የምግብ እጥረት እንዳለበትና በመቶ ሺዎች የሚገመቱ ለረሃብ ይጋለጣሉ የሚል ስጋት እንዳለ ኦክስፋምና የእንግሊዝ ህፃናት አድን ድርጅት ያወጡት ሪፖርት ገልጿል። ከ50 እስከ 100 ሺህ ሰዎች እንደሞቱበት በሚነገረዉ በአፍሪቃ ቀንድ ተከስቶ የነበረዉ የረሃብ አደጋ በክፍለ ዘመኑ ከታዩት ሁሉ በአይነቱ ልዩ የሆነ የአስቸኳይ ጊዜ ክስተት እንደነበር ሪፖርቱ ጠቅሷል። ድርቅ ባሰከተለዉ ...

Read More »

አንድ የአሜሪካ ተቋም ከአምልኮ ጋር በተያያዘ በሳውዲ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን እንዲፈቱ ጠየቀ

የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአሜሪካ አለማቀፍ የሀይማኖት ነጻነት አስጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ የሳውዲ አረቢያ መንግስት እስረኞችን ያሰረበትን ትክክለኛ ምክንያት ይፋ እስካላደረገ ድረስ፣ መልቀቅ አለበት ብሎአል። እስረኞቹ በእስር ቤት ውስጥ እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን፣  የእስልምና ሀይማኖትን እንዲቀበሉ እየተገደዱ መሆኑን ድርጅቱ አክሎ ገልጧል። 35 የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን የታሰሩት ሴቶችና ወንዶች በአንድ ላይ በመሆን አምልከዋል በሚል ምክንያት ነው። ሳውዲአረቢያ የቤተሰብ አባል ያልሆኑ ሴቶችና ...

Read More »

የሰበታ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሽመልስ ሀሰኖ በ10 አመት እና በ40 ሺ ብር ተቀጡ

የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሙስና ጋር በተያያዘ በእስር ላይ በሚገኙት በርካታ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መስጠቱን ዘጋቢአችን ገልጧል። ከአቶ አባዱላ ገመደ እና ከወ/ሮ  አዜብ መስፍን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ሲነገርላቸው በቆዩት በከንቲባ ሽመልስ ላይ የ10 አመት ፍርድ ሲያስተላልፍ፣ ከእርሳቸው ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቸው ግበረ አበሮች ላይ ደግሞ ከ8 አመት እስከ 9 ወር በሚደርስ እስር እንዲቀጡ ወስኗል ...

Read More »

መለስ በመድረክ ውስጥ ያልታሰሩ የሽብርተኛ ድርጅቶች አባላት አሉ ብለው የተናገሩትን የመድረኩ መሪ አጣጣሉት

የካቲት 1 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ 99 ነጥብ ስድስት በመቶ በራሳቸው የፓርቲ አባላት በተያዘው ፓርላማ ፊት ቀርበው ባደረጉት ንግግር በመድረክ ውስጥ ለፍርድ ቤት በቂ የሆነ ማስረጃ ያላገኘንባቸው የአሸባሪ ድርጅቶች አባላት አሉ በማለት መናገራቸው ይታወቃል። የመድረኩ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ሞጋ ፍሪሳ በበኩላቸው አቶ መለስ ዜናዊ በሰው ህሊና ውስጥ ያለውን ነገር እንዴት እንደሚያውቁ አላውቅም ሲሉ መልሰዋል:: አቶ መለስ ዜናዊ ...

Read More »

የጋምቤላውን ከፍተኛ ባለስልጣን አስገድለዋል የተባሉ ተያዙ፤ ሶስት ባለስልጣናትን ለመግደል እቅድ ነበራቸው

የካቲት 1 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጋምቤላውን ከፍተኛ ባለስልጣን አስገድለዋል የተባሉ አንዳንድ ባለስልጣናት መያዛቸው ተሰማ፣ ሶስት ባለስልጣናትን ለመግደል እቅድ ነበራቸው ተብሎአል የኢሳት የጋምቤላ ወኪል እንደገለጠው በቅርቡ በክልሉ የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ በስውር የደህንነት አባል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን አቶ ጌታቸው አንኮሬን ያስገደሉት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው። ግለሰቡ የከምባታ ተወላጅ ሆነው የህወሀት ሰላይ በመሆን የክልሉ ነዋሪዎችን ሲያሰቃዩ፣ እርስ በርስ ለመከፋፈል ሲሞክሩ መቆየታቸውን መረጃዎች ...

Read More »

ዜጎች ሀሳባቸውን በመግለጣቸው አሸባሪ እየተባሉ በመታሰር ላይ ናቸው ሲሉ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ ተናገሩ

ጥር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-99 በመቶ የአንድ ፓርቲ ሰዎች በታጨቁበት ፓርላማ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ዛሬ የአቶ መለስ ዜናዊን የስድስት ወራት ሪፖርት ካደመጡ በሁዋላ በርካታ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ማቅረባቸውን ዘጋቢያችን ገልጧል። ዜጎች ሀሳባቸውን በገለጡ አሸባሪ ይባላሉ በዚህም የተነሳ የፖለቲካ መህዳሩ እየጠበበ መምጣቱን አቶ ግርማ ተናግረዋል። አቶ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ የሽብርተኝነት ህግ በዓለም ላይ ምርጥ ከተባሉት ...

Read More »

የ አንድነት ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር የፃፉት ደብዳቤ ይፋ ሆነ

ጥር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብርተኝነት ተከሰው የ 17 ዓመት እስራት የተፈረደባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ዘሪሁን ገብረ-እግዚአብሔር የፃፉት ደብዳቤ ይፋ ሆነ። አቶ ዘሪሁን ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት በወረዱበት ቀን ለፍኖተ-ነፃነት አንድ ደብዳቤ ጽፈው እንደነበር ያወሳው የጋዜጣው ዝግጅት ክፍል፤ ጉዳያቸው ገና በፍርድ ቤት እየታየ ስለነበር በወቅቱ ደብዳቤውን ሊያወጣው እንዳልቻለ በመጥቀስ፤በትናንትናው ዕትሙ ይፋ አድርጎታል። አቶ ...

Read More »

ካናዳ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለሚፈጽመው የግዳጅ ሰፈራ እርዳታ በመስጠቷ ተቃውሞ ቀረበባት

ጥር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ሂዩማን ራይትስ ዎች ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት፤ብዙዎችን ለችግርና ለመከራ ህይወት ለዳረገውና ኢትዮጵያ እየፈፀመች ላለው የግዳጅ ሰፈራ የገንዘብ እርዳታ አድርጋለች ያላትን ካናዳን መውቀሱ ይታወሳል። የሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ይፋ መሆን ፤ግብር ከፋዩን የካናዳ ህዝብ እያነጋገረ እንደሆነ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት፤ የአገሪቱ ታላቁ ራዲዮ የሆነው “ራዲዮ ካናዳ ኢንተርናሽናል” በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ ይሰጡ ዘንድ፤ የድርጅቱን አንድ መርማሪ በመጋበዝ ...

Read More »