.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሲያትል እና አካባቢዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የህወሀትን የዘረኝነት አሠራርን አጥብቀው ተቃወሙ

ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሲያትል እና አካባቢዋ የሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች ህወሀትን አጥብቀው የተቃወሙት፤ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ነገ እሁድ  ኦገስት 19 ቀን  በ3515 ሳውዝ አላስካ በሚገኝ የስብሰባ አዳራሽ  በሚካሄድ እና  ከ2 ሰ ዓት እስከ 6 ሰዓት በሚቆይ የመንግስት ስብሰባ ላይ የትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዲገኙ ተለይቶ ጥሪ በመደረጉ ነው። በበርሀ ስማቸው ተወልደ አጋመ ተብለው በሚጠሩት በአምባሳደር ተወልደ ገብሩ ...

Read More »

የብጹፅ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዜና ረፍት የመላው ኢትዮጵያውያን መነጋገሪያ ሆኗል

ነሀሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘጋቢዎቻችን እንደገለጡት የአቡነ ጳውሎስን ድንገተኛ ዜና እረፍት ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው ። አንዳንድ ሰዎች አቡኑ በዋልድባ እና በሌሎች ገዳማት ላይ ለፈጸሙት በደል እግዚአብሄርን አሳዝነዋል የሚል አስተያየት ሲሰጡ ሌሎች ወገኖች ደግሞ የሞታቸው መንስኤ ከአቶ መለስ ዜናዊ ደህንነትጋር የተያያዘ ነው ይላሉ። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አባት አቡነ ጳውሎስ ለሞት የሚያበቃ በሽታ እንዳልነበረባቸው መስክረው፣ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መረጋጋት የሚያስፈልጋት ጊዜ ላይ ናት ሲል ታዋቂው ጸሀፊ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገለጠ

ነሀሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሀይማኖታዊ ጽሁፎቹ የሚታወቀው  ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከኢሳት  ጋር ባደረገው ቃለምልልስ የአቡነ ጳውሎስ ድንገተኛ እረፍት እንዳስደነገጠው ገልጧል:: በአቡነ ጳውሎስ የ20 አመታት አስተዳዳር የተሰሩ  መልካም ስራዎች የመኖራቸውን ያክል ባይሰሩ ይሻል ነበር የሚያስብሉ ጉዳዮች እንደነበሩም ዲያቆን ዳንኤል ይናገራል:: ወቅቱ የመረጋጋት ፣ እርስ በርስ የምንተጋገዝበት እና ለወደፊቱ መልካም የሆኑ ስራዎችን ስርተን ለማለፍ የምንችልበት መሆኑን ሁለም ሰው ...

Read More »

አንዋር መስጊድ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ድርቅ ተመታ

ነሀሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 7 ወራት ከ50 ሺ ህዝብ በላይ ሲያስተናግድ የከረመው አንዋር መስኪድ በዛሬው የጁመአ ጸሎት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ100ዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ብቻ አስተናግዷል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ወደ አንዋር መስጊድ እንዳይሰባሰብ ተተኪ አመራሩ ውስጥ ለውስጥ ባሰራጨው መመሪያ መሰረት ፣ ህዝቡ ወደ መስጊዱ የሚያደርገውን ጉዞ እንደገታ ታውቋል። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተል አንድ ስሙ እንዳይገለጥ የፈለገ ሰው ለኢሳት ...

Read More »

ክቡር ገና የሚረገጥ ህዝብ ድንገት ይነሳል አሉ

“አንድ ህዝብ ዝም ብሎ ተኝቶ ሲረገጥ አይውልም፤ ድንገት ይነሳል፤ መተንፈሻ ያጣ ህዝብ ሌላ መንገድ በመፈለግ ለመተንፈስ ይሞክራል” ሲሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ክቡር ገና ተናገሩ። አንድነት “በዴሞክራሲአዊ ስርአት ግንባታ የሲቪክ ማህበራት ሚና” በሚል ርእስ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተናጋሪ እንግዳ ሆነው የቀረቡት፤ ዶ/ር ክቡር ገና ከፍኖት ነጻነት አዘጋጆች ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፤ “ፖለቲካ ችግርን በውይይት መፍቻ መንገድ ሆኖ ሳለ” በኛ ...

Read More »

የአሜሪካን ድምጽ ሬድዮ ፕሮግራም በመታወክ ላይ ነው

በኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚደረግ አፈና መቀጠሉን ከአዲስ አበባ የመጣው ዜና ያስረዳል። በዚህም መሰረት የአሜሪካን ድምጽ ሬድዮ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች በአጭር ሞገድ እንዲሁም በሳተላይት የሚያስተላልፍው ፕሮግራም በመታወክ ላይ ይገኛል። የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከህዝብ ዕይታ መሰወርን ተከትሎ የኤርትራ ቴሌቭዥን የሣተላይት ስርጭት መመታቱ ሲታወስ፤ በሐገሪቱ በሥርጭት ግንባር ቀደም የሆነው ፍትህ ጋዜጣ ሥለ አቶ መለስ ሁኔታ ዘገባ ይዞ በመውጣቱ በፍርድ ቤት ውሳኔ መቃጠሉ ...

Read More »

ሙስሊሞች ተቃውሞ ለመግለጽ መስኪድ ሳይሄዱ ቀሩ

(Aug. 17) በአዲስ አበባ የሙስሊሞች ተቃውሞ በዛሬው እለትም የቀጥለ ሲሆን፤ አንዋር መስጊድ በተቃውሞ ጭር ብሎ እንደዋለ ከአዲስ አበባ ለለማወቅ ችለናል። የአዲስ አበባ ምንጮቻች እንደገለጹልን፤ በዚህ አርብ ደህንነቶች ቀንደኛ ያሉዋቸውን የሙስሊሙን አስተባባሪዎች ለመያዝ ዝግጅት ላይ እንደሆኑ መረጃ በመውጣቱ የተነሳ፤ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ወደአንዋር መስጅድ ሳይሄድ እንደዋለና አንዋር በተቃውሞ ጭር ብሎ እንደዋለ ምንጮቻችን ጠቅሰዋል። በደሴም በትናንትናው እለት ከተደረገው በመንግስት የተቀነባበረ ሰልፍ በሁዋላ ውጥረቱ ...

Read More »

ዲፕሎማቶች እየኮበለሉ ነው ተባለ

(Aug. 17) ከአቶ መለስ ዜናዊ መሰወር ጋር ተያይዞ በውጭ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ወደአገር ቤት ቢጠሩም፤ ብዙዎቹ በነበሩበት አገር ወይንም ወደሌላ ሶስተኛ አገር በመኮብለል ጥገኝነት እየጠየቁ እንደሆነ የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በህንድ የወ/ሮ ገነት ዘውዴ ምክትል ሆነው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ደረጀ አስፋው ጄቶ ወደአሜሪካን እንደከዱና በአሜሪካን ጥገኝነት እንደጠየቁ ታማኝ ምንጮች ነግረውናል። በሌላ ዜናም በካርቱም ዲፕሎማት ሆነው ሲሰሩ የቆዩትና ከዚህ ቀደም በጃፓንና በዱባይ ለረጂም ...

Read More »

በዳላስ የተገደሉት ኢትዮጵያዊያን ተጠርጣሪ ገዳይ ታወቀ

በዳላስ የተገደሉት ሁለት ኢትዮጵያዊያን ተጠርጣሪ ገዳይ መታወቁን የዳላስ ፖሊስ አስታወቀ። ምክንያት ንቀውኛል በማለት። ተጠርጣሪው አብይ በለጠ ግርማ የተባለ ኢትዮጵያዊ ሲሆን፤ ተጠርጣሪው ሟቾቹን የደስታ ምግብ ቤት ባለቤቶች፤ አቶ ያየህ ይራድ ለማንና ወ/ሮ ኔነሽ ደስታን በተገደሉ እለት፤ ከምግብ ቤታቸው ጀምሮ ሲከተላቸው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ሁለቱ የደስታ ምግብ ቤታ ባለቤቶች፤ ባለፈው ረቡእ እኩለ ሌሊት ላይ ከስራ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ በራቸው ላይ በጥይት ተመተው ...

Read More »

የአቡነ ጳውሎስ ቀብር ነሀሴ 17 ቀን እንደሚካሄድ ታውቋል

(Aug. 17) በትናንትናው እለት ከዚህ አለም በሞት የተለዩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ ቀብር በመጪው ሀሙስ ነሀሴ 17 ቀን እንደሚካሄድ ተነገረ። ከስፍራው ባገኘነው መረጃ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ከየአገረስብከቶቻቸው ወደአዲስ አበባ እየገቡ እንደሆነም ታውቋል። በኢትዮጵያ የሚገኘው የአገር ቤቱ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ እንደተቀመጠ የታወቀ ሲሆን፤ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራአስኪያጅ የሆኑት፤ ብጹእ አቡነ ፊልጶስ በጊዜያዊነት የሲኖዶሱ ሰብሳቢ እንደሆኑ ታውቋል። በትናንትናው እለት ...

Read More »