ህዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሚዛን ተፈሪ 90 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውና ልዩ ስሟ <<ዲማ>> ተብሎ በሚጠራው ቦታ በሱርማ እና በዲዙ ብሔረሰብ መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸው ተሰማ። ጉዳዩን አስመልክተው ለኢሳት ቃለ-ምልልስ የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት፤ግጭቱ ከተከሰተ አንድ ወር ያስቆጠረ ቢሆንም፤ እስካሁን ሊበርድ አልቻለም። የፌዴራል የመከላከያ ሠራዊት ወደ ስፋራው ቢላክም ግጭቱን ብስለት በተሞላበት መንገድ ከማረጋጋት ...
Read More »Author Archives: Central
የሱዳን አማፅያን ጥቃት ሊፈጽምባቸው የሄደን የመንግስት የጦር አውሮፕላን መተው መጣላቸውን ገለፁ
ህዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሱዳን ህዝቦች የነፃነት ንቅናቄ እንዳለው፤ አማጽያኑ የመንግስትን አንቶኖቭ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን በደቡብ ኮርዶፋ ግዛት ጃው በተባለ አካባቢ ከአፈር ጋር ቀላቅለውታል። ጉዳዩን አስመልክቶ የአልበሽር አስተዳደር እስካሁን የሰጠው አስተያዬት የለም። በ አማጽያኑ እና በመንግስት ሠራዊት መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ ከደቡባዊ ኮርዶቻና ከጥቁር አባይ ግዛቶች ብቻ በ አስር ሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቀያቸውን ጥለው መሰደዳቸውን ቢቢሲ ...
Read More »በላፍቶ ክፍለ ከተማ ከ17 ሺ በላይ አባወራዎች ሜዳ ላይ ተበተኑ ሁለት ህጻናትም በፖሊስ ዱላ ተገደሉ
ጥቅምት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ላፍቶ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ቤታቸው የፈረሰባቸው ከ17 ሺ በላይ በላይ አባዎራዎች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። የአትዮጵያን ሰንደቃላማና የአቶ መለስ ዜናዊ ፎ ከ400 በላይ ነዋሪዎች ዛሬ በአንድ ላይ በመሆን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ሲያመሩ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ወደ አዲስ አበባ መስተዳደር እንዲሄዱ አዞዋቸዋል። አዲስ አበባ መስተዳድርም ሶስት ሰዎች ተወክለው ...
Read More »እነ አቶ አንዱለም አራጌ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ጥቅምት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብርተንነት ወንጀል ተከከሰው ብግፍ እስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ሌላው የአመራር አባል አቶ ናትናኤል መኮንን እንዲሁም የመኢዴፓ የአመራር አባል የሆነው አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ የይግባኝ አቡቱታቸውን ለማቅርብ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ዳኞቹ ለህዳር 13 ቀን 2005 ዓም ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱን አሰናብተዋል። የፍርድ ሂደቱን በተመለከተ ችሎቱን የተከታተሉትን አንድነት ...
Read More »መንግስት 6 የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ሊያዞር ነው
ጥቅምት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብሉምበርግ እንደዘገበው ወደ ግል ከሚዞሩት ድርጅቶች መካከል 600 ሄክታር የሚሸፍነው በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው አርባ ጉጉ የቡና ተክል ይገኝበታል። መንግስት ከስድስቱ የልማት ድርጀቶች 1 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱም ታውቋል። የኢትዮጵያ መንግስት የ5 አመቱን እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል በማዞር የገንዘብ እጥረቱን ለመቅረፍ እየሞከረ ነው። መንግስት አምና የሜታ ፣ የሀረርና በደሌ ቢራ ...
Read More »ፓትሪያርክ መርቆሬዎስ ከነሙሉ ስልጣናቸው ወደመንበራቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ
በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ ለኢሳት እንደተናገሩት፤ ቅዱስ ፓትሪያርኩ ከነሙሉ ስልጣናቸው ወደመንበረ-ፓትሪያርኩ ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ቅዱስ ፓትሪያርኩ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የሚገልጽ ደብዳቤ ለአቃቤ መንበረ ፓትሪያርኩ፤ ለአቡነ ናትናኤል መጻፋቸውንና ደብዳቤውም በሲኖዶሱ ጉባኤ ላይ መነበቡን በተለይ ለኢሳት ገልጸዋል። በሀገር ቤትና በስደት በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ስምምነት ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት እንዲሳካ ለማድረግ በውጭ ...
Read More »ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረቡ
ጥቅምት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ 25 የፖለቲካ ፓርቲዎች 18 ጥያቄዎች የያዘ ደብዳቤ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ማስገባታቸውን አስታወቁ። የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ ሊያካሂድ ባሰበውና የጊዜ ሰሌዳ ባወጣለት የወራዳና የአንዳንድ ዞኖች የሞማያ ምርጫ ነጻና ፍትሀዊ እንዲሆን እሁድ እለት ተሰብስበው ውሳኔ ያስተላለፉት 25 የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በእለቱ ያቆቆሞቸው ሰባት አባላት ያሎቸው አስተባባሪ ኮሚቴ ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 18 ...
Read More »ሟቹ ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ ትግራይን የኢንዲስትሪ ማእከል ለማድረግ ጽሁፍ አዘጋጅተው ነበር ተባለ
ጥቅምት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትግራይን የኢንደስትሪ ማእከል ለማድረግ አቶ መለስ ያወጡትን ስትራቴጂ ለመተግበር ርብርብ በማድረግ ላይ መሆኑን ወ/ሮ አዜብ መስፍን ገለፁ። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤትና የ ኤፈርት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የ ኤፈርት ኩባንያዎች እየተጠናከሩ መምጣታቸውንም ገልፀዋል ። ከኤፈርት ኩባንያዎች አንዱ ሉሆነው ዋልታኢንፎርሜሽን ማዕከል ወ/ሮ አዜብ መስፍን በሰጡት ቃለ ምልልስ ያቶ ...
Read More »የአባይ ግድብ አሁን ባለው ሁኔታ በ20 አመታት አይጠናቀቅም ሲሉ ሰራተኞች ገለጡ ሰራተኞቹ ተገደው ወደ ስራቸው እንዲመለሱም ተደርጓል
ጥቅምት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ትናንት በሰበር ዜና እንዳቀረበው ሰራተኞቹ ተቃውሞውን ያነሱት ከስራው መጓተት፣ ከክፍያ ፣ ከስራ ከባቢ ከመጠለያና ተዛማች ችግሮች ጋር በተያያዘ ነው። ሳሊኒ ከግብጽ መንግስት ጋር የተመሳጠረ በሚመስል ሁኔታ ስራው እንዳይሰራ እያጓተተው ነው፣ ሰራተኛው አለስራ ጊዜውን እያባካነ ነው፣ የሚከፈለን ክፍያ ከስራው ጋር የተመጣጠጠነ አይደለም፣ የምግብ፣ የመጠለያና ሌሎችም ችግሮች አሉብን በማለት የስራ ማቆም አድማ ያደረጉት ...
Read More »በደጋን ወረዳ የተያዙ ሙስሊም እስረኞች በሰለጠኑ ውሾች ሳይቀር እንዲነከሱ እየተደረገ መሆኑን የአይን እማኞች ተናገሩ
ጥቅምት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ በደጋንና በገርባን የተነሳውን የሙስሊሞች ተቃውሞ ተከትሎ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት መገደላቸውን፣ ግጭቱን አስነስተዋል የተባሉ 2 ሰዎች በፌደራል ፖሊሶች እንዲረሸኑ፣ ሌሎች ሁለቱ ደግሞ በግጭቱ ላይ በፌደራል ፖሊሶች ጥይት እንዲገደሉ መደረጉን ፣ ይህን ተከትሎም የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው በስፋት በመስፈር አካባቢውን የጦር ቀጣና እንዳስመሰሉትና እስካሁን ድረስ ከ200 በላይ ወጣቶችን፣ አዛውንቶችንና ሴቶችን ሳይቀር ይዘው ማሰራቸውን ...
Read More »