ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጡረተኞቹ የጎባና የአካባቢው ጡረተኞች ማኀበር በሚል ተደራጅተው በ1991 ዓ.ም፣ 200 ሄክታር መሬት ተረክበው ሲሰሩ እንደነበር በመሃል 75 ነጥብ 25 ሄክታር መሬት መነጠቃቸውን በአሁን ወቅት ደግሞ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው እያለሙ ያሉትን መሬት ሙሉ በሙሉ መነጠቃቸውን ገልጸዋል፡፡ መሬቱ ለ25 ዓመታት ተዋውለን የተረከብነው ነው ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ በ30 ሄክታር መሬት ላይ ከ75 ሺ ብር በላይ ለትራክተር ...
Read More »Author Archives: Central
ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ተፈናቃዮች አለመረጋጋታቸውን ተናገሩ
ግንቦት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሚያዝያ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተፈናቀሉ በኋላ በድርድር ወደ ተፈናቀሉበት ቤንሻንጉል ጉሙዝ እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ተወላጆች ዳግም የመፈናቀል ስጋት አንዣቦብናል አሉ፡፡ የት ተወልድን እንዳደግን፣ የቀድሞ ሠፈራችንና ቀበሌያችንን በመመዝገብ ሂደት ላይ ያለው የዞኑ አስተዳድር ሚስጥራዊና ድብቅ የማፈናቀል ዘመቻውን ሊቀጥል እንደሚችል በተወሰነ መልኩ መገንዘብ ችለናል ያሉት ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ አንድ የሴባ ቀበሌ ኗሪ በሁኔታው ሁሉም ...
Read More »በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ከአንድ መቶ በላይ ተማሪዎች ተይዘው ታሰሩ
ግንቦት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሶስት ቀናት በፊት የተነሳው የተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ ቀጥሎ የፌደራል ፖሊሶች አድማውን መርተዋል ብለው የጠረጠሩዋቸውን ከ100 በላይ ተማሪዎች ወስደው በጋሞጎፋ ዞን ፖሊስ መመሪያ ግቢ ውስጥ ማጎራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። የተለያዩ የትምህርትና አስተዳዳራዊ በደሎችን ያነሱት ተማሪዎች ትናንት ቀኑን ሙሉ በፖሊሶች ተከበው መዋላቸውን መዘገባችን ይታወሳል። በዛሬው እለትም ተማሪዎቹ ትምህርት ያልጀመሩ ሲሆን፣ የታሰሩ ጓደኞቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ...
Read More »የአብያታ ሐይቅ ህልውና ላይ አደጋ ተጋርጧል
ግንቦት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው የመስኖ እርሻና የሶዳ አሽ ሥራዎች ለአብያታ ሐይቅ ህልውና አደጋ መሆናቸውን ምሁራን ናቸው ያስጠነቀቁት በአንድ ወቅት በዝዋይ በሚገኙ የአበባ እርሻዎች ሳቢያ ለብክለትና ለከፍተኛ የውኃ መጠን መቀነስ ችግር ተዳርጎ የቆየው አብያታ ሐይቅ፣ በአሁኑ ወቅት በመስኖ እርሻዎችና ሶዳ አሽ በሚያመርተው ፋብሪካ ሳቢያ ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጧል። ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ ከአንድ ትውልድ በላይ ላይዘልቅ እንደሚችል ያስጠነቀቁት ...
Read More »አርቲስት አበበች ደራራ አረፈች
ግንቦት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለረጂም ዓመታት በራስ ቴአትር በድምጻዊነት ስታገለገል የቆየችው አበበች ደራራ ባደረባት ህመም ሳቢያ በእስራኤል ግንቦት 8 ፣ 20005 ዓም አርፋለች። ድምጸ መረዋዋ አበበች ደራራ ለበርካታ አመታት ከሽታዋ ጋር ስትታገል መቆየቷን በቅርብ የሚያውቁዋት ሰዎች ተናግረዋል። የአበበች ደራራ የቀብር ስነስርአት በኖረችበት የቴል አቪቭ ከተማ መፈጸሙን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ኢሳት ለአርቲስ አበበች ደራራ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል።
Read More »በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የተጀመረው ተቃውሞ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎአል
ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋሞ ካምፓስ ትናንት ከምሽቱ 4 ሰአት ላይ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ያዋለ ሲሆን “ተማሪዎች መብታችን ይከበር፣ ድምጻችን ይሰማ፣ ጥያቄያችን ይመለሰ፣ ተምሮ ለኮብል ስቶን ” የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ግቢውን የተቆጣጠሩት ሲሆን ተማሪዎች እርስ በርስ እንዳይገናኙ አድረገዋል። ተማሪዎች የምግብ መበላሸትን ሰበብ አድርገው አድማውን ቢጀምሩም፣ ሌሎች ከትምህርት ...
Read More »የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመር የመንግስት ሰራተኞች የአባልነት ክፍያ በግዴታ እንደሚቆረጥባቸው ተናገሩ
ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት እጅ በገባው የፕሬዚዳንቱን ሚስጢራዊ ንግግሮች በያዘው ፊልም ውስጥ እንደተመለከተው ፣ አቶ አብዲ የኢህአዴግ አጋር ድርጅት የሆነው የሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲ ፓርቲ ( ሶህዴፓ) አባላት በግዴታ የአባልነት መዋጮ እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ” መንግስት በአንድ በኩል ገንዘብ ይሰጣል በሌላ በኩል ደግሞ ገንዘብ ከፋዩዋ በግዴታ ከሰራተኞች እየቆረጠች ትወስዳለች” ብለዋል አቶ አብዲ። አቶ አብዲ ድርጅታቸው ሶህዴፓ 40 ...
Read More »በአውሮፓ ህብረት መቀመጫ ብራሰልስ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ
ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሆላንድ እና የቤልጂየም የኢትዮጵያውያን ማህበሮች ባዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት አቅርበዋል። ኢትዮጵያውያኑ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል እንዲሁም መንግስት በሀይማኖቶች ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት አውግዘዋል። የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ ሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲቆሙም ጠይቀዋል።
Read More »የኢትዮጽያ መንግስት በሰሜን ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሠፈሩ ሰዎችን በአስቸኳይ እንዲወጡ ካላደረገ የፓርኩን የምዝገባ ዕውቅና እንደሚሰርዝ ዩኔስኮ አስጠነቀቀ፡
ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በፌዴራል መንግስት ስር ከሚተዳደሩ 13 ብሔራዊ ፓርኮች አንዱና ዋናው የሆነው የሰሜን ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ የተመዘገበ ሲሆን ፓርኩ ከመመስረቱ በፊት ጀምሮ ሰፍረው የነበሩ ሰዎችን ከአካባቢው ለማስወጣት ከዚህ ቀደም የተደረጉ ተደጋጋሚ ጥረቶች አለመሳካታቸውን ተከትሎ ዩኔስኮ በቅርቡ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ታውቋል፡፡ ከዩኔስኮ ማስጠንቀቂያ የደረሰው የኢትዮጵያ መንግስት በፓርኩ ክልል ውስጥ የሚገኙ ከ300 በላይ አባወራዎችን ለማስወጣት ጥረት መጀመሩን ...
Read More »በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት ዳይሬክተር በርሳቸው ጥፋት ቤተሰቦቼ መታሰራቸው አግባብ አይደለም “ሀገሪቱ ምን አይነት ገር እየሆነች ነው” ሲሉ ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቀረቡ
ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ገብረዋሕድ ወ/ጊዮርጊስ የጉምሩክ ባለሥልጣን ም/ዳይሬክተር ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው የሚባሉት ባለቤታቸው ኮ/ል ሃይማኖት ተስፋይ መታሰራቸውና ልጃቸውም መደገማቸው ፈጽሞ አግባብ አይደለም ካሉ በኋላ እኔ በጥፋቴ ልጠየቅ ቤተሰቦቼ ለምን? ምን አይነት ሀገር እየሆንን ነው በማለት ታላንት ከሰዓት ባስቻለው ችሎት ጠይቀዋል። የአቶ ገብረዋሕድ ወ/ጊዮርጊስ ባለቤት ኮ/ል ሃይማኖት ተስፋይ እናታቸው ወ/ሮ ንግሥቲና ልጃቸው ...
Read More »