Author Archives: Central

አርሶ አደሩ ከግብር ጋር በተያያዘ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉ ተገለጸ

መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት ኮሚዩኒኬሺን ጽ/ቤት  ከህዝብ ባሰባሰበው መረጃ እና ከክልሎች የተላከው የጽሁፍ ሰነድ እንዳመለከተው ፤ የኦሮምያ ፤ የአማራ እና የደቡብ ክልል አርሶ አደሮች ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ወስዳችሁ ግብር እና የማዳበሪያና የምርጥ ዘር እዳችሁን አንክፍልም ብላችኃል በሚል እየታሰሩና ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑ ተመልክቷል። “በእድሜ የገፉ እናት አባቶችን ታስረው ይንገላታሉ ፤ ከብቻችንን ከቤታችን በሃይል ነድተው ...

Read More »

የአባይ ግድብ መዋጮ መቀዝቀዙ መንግስትን ስጋት ላይ ጥሎታል

መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በያዝነው ወር የሶስተኛ ዓመት የምስረታ ልደቱ የሚከበርለት የአባይ ግድብ ግንባታ እስካሁን ከወጣው ወጪ በሕዝብ መዋጮ መሸፈን የተቻለው 26 በመቶ ያህሉን ብቻ መሆኑና ሕዝቡ ለግድቡ እያደረገ ያለው ድጋፍ መቀዛቀዝ ማሳየቱ ታውቋል። ግድቡ በመጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም በቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ በይፋ ግንባታው የተጀመረ ሲሆን በወቅቱም የገንዘብ ምንጩ ሕዝቡ ...

Read More »

በሀረር ለ2ኛ ጊዜ የተነሳውን የእሳት አደጋ መንስኤ በተመለከተ የክልሉ መንግስትና ህዝቡ የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጠ ነው

መጋቢት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሀረር በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ህዝቡ መንግስትን ተጠያቂ ሲያደርግ፣ መንግስት በበኩሉ ድብቅ የፖለቲካ አላማ ያላቸው ሀይሎችን ያደረሱት ቃጠሎ ነው ይላል። ቅዳሜ ምሽት ሲጋራ ተራ እተባለ በሚጠራው የንግድ ማእከል ላይ በተነሳው እሳት በርካታ ንብረት ወድሟል። ከሳምንት በፊት መብራት ሃይል እየተባለ በሚጠራው የንግድ ማእከል በደረሰው ቃጠሎ ደግሞ ከ20 ...

Read More »

የኦህዴድ አባላት በአቶ አለማየሁ ሞት ጉዳይ ጥያቄ እያቀረቡ ነው

መጋቢት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሚያ ክልል እና የኦህዴድ ፕሬዚዳንት የነበሩትና ሰሞኑን ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የአቶ አለማየሁ አቶምሳ የሞት መንስኤ እንዲጣራ የኦህዴድ መካከለኛና ዝቅተኛ ካድሬዎችና አባላት በየመድረኩ ጥያቄ እያነሱ መሆኑ ከፍተኛ አመራሩን ጭንቀት ውስጥ እንደጣለው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡ አቶ አለማየሁ ለሞታቸው መንስኤ የሆነው ከምግብ ጋር የተሰጣቸው መርዝ ነው የሚሉ መረጃዎች ኢሳትን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ...

Read More »

በአማራ ክልል ከፍተኛ የዘይትና ስኳር እጥረት ተከሰተ

መጋቢት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የአትክልት ዘይት  ሙሉ በሙሉ ከገበያ ጠፍቷል ማለት እንደሚቻል ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ስኳር እና የተለያዩ የሸቀጣ ሸቀጥ ምርቶች እጥረት መከሰቱን ተከትሎ፣ የእቃዎች ዋጋም እየናረ ነው። የአንድ ሊትር ዘይት የመሸጫ ዋጋ ከ25 ብር ወደ 35 ብር ከፍ ያለ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 45 ብር መሸጥ መጀሩን ነዋሪዎች ይናገራሉ። በአንድ ለአምስት ካልተደራጁ ...

Read More »

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው

መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባልተለመደ መልኩ ወጣት የሰማያዊ ሴት አመራሮችና አባላት አለማቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ በተዘጋጀ ሩጫ ላይ የመብት ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ፍትህ ጥያቄዎችን በማንሳት መንግስት አፋጣኝ መልስ እንዲሰጥ በተቃውሞ ድምጽ ማቅረባቸውን ተከትሎ በቁጥጥር ስር ውለው ለአምስት ቀናት በእስር ካሳለፉ በሁዋላ ዛሬ በድጋሜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ፖሊስ በእስረኞቹ ላይ የማደርገው ምርመራ አልተጠናቀቀም ...

Read More »

ህዝቡ ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጣ እየተገደደ ነው

መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ ካድሬዎች በተለይ በአዲስ አበባና በአጎራባች ከተሞች ባሉ ቤቶች እየዞሩ ለመለስ ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ ከ50 ብር ጀምሮ እንዲከፍሉ እያስገደዱ ነው። እድሮች በነፍስ ወከፍ ከ8 ሺ ብር ጀምሮ እንዲከፍሉ መመሪያ ተላልፎላቸዋል። በዚህ መመሪያ የተሰላቹና የተበሳጩ ሰዎች “ወዴት እንሂድ” ሲሉ ለኢሳት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የመለስ ፋውንዴሽን በወ/ሮ አዜብ መስፍን ሊቀመንበርነት የሚመራ ሲሆን የአቶ መለስን አስከሬን በቋሚነት የሚያርፍበትን ...

Read More »

በሳውድ አረቢያ አንድ ኢትዮጵያዊት ራሱዋን አጠፋች

መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከ10 ወራት በላይ የሰራችበትን ደሞዙዋን ባለመስጠታቸው ከአሰሪዎቹዋ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብታ የነበረችው ኢትዮጵያዊት ተማም በሚባል ከተማ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ልብሷን ቀዳ ራሱዋን በመስቀል ማጥፋቱዋን በእስር ቤት ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ እስረኞች ለኢሳት ገልጸዋል። ወርቅነሽ የምትባለዋ ሟች አስከሬን በትናንትናው እለት ምርመራ እንደተደረገበትና ፖሊሶች አስከሬኑን መውሰዳቸው ታውቋል። በዚሁ እስር ቤት ውስጥ አንዲት ወጣት ባለፉት ...

Read More »

በምእራብ አርማጮ የሽፍታ ቤተሰቦች ናችሁ በሚል ብዙ ነዋሪዎች ታስረው በመሰቃየት ላይ ናቸው

ማጋቢት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮ-ሱዳን ድነበር አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የምእራብ አርማጭሆ ነዋሪዎች እና በሽፍታ ቤተሰብነት የተጠረጠሩ ከ20 ያላነሱ ቤተሰቦች ታስረው እንደሚሰቃዩ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያሳያል። የሽፍቶቹ ቤተሰቦች ለእስር የሚዳረጉት ሽፍቶችን አሳምነው እጃቸውን ለመንግስት እንዲሰጡ ወይም ገድለው እንዲያቀርቡ ለማድረግ ነው። ይሁን እንጅ አብዛኞቹ ሽፍቶች እጃቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በቤተሰቦቻቸው ላይ የሚደርሰው እንግልት እየጨመረ ነው። በእስር ላይ ከሚገኙት ...

Read More »

በኢትዮጵያ ህጻናትን በማደጎነት የሚልኩ የውጭ ድርጅቶች ዘመቻ ሊጀምሩ ነው

ማጋቢት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሀን የተለቀቀ አንድ የድምጽ ማስረጃ እንደሚያሳየው ህጻናትን በጉዲፈቻ ስም ወደ ውጭ አገራት የሚልኩ በተለይም የአሜሪካ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ያወጣውን ህግ በመቃወም ዘመቻ ሊጀምሩ መሆኑን ውሳኔ ላይ ደርሰዋል። የኤጀንሲው ተወካዮች እንደሚገልጹት፣ መንግስት በቅርቡ የጣለው እገዳ በመገናኛ ብዙሀንና በህዝቡ ተጽእኖ የመጣ ነው። አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት በቂ ገንዘብ እስከተከፈለ ድረስ የጉዲፈቻ ሂደቱ ...

Read More »