መጋቢት ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአክሰስ ሪል ስቴት ስራ አስኪያጅ አቶ ኤርምያስ አመልጋ ከቤት ግንባታ ጋር በተያያዘ ደንበኞቻቸውን አጭበርብረዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸው እንዲታሰሩ ከተደረገ በሁዋላ፣ ፖሊስ የተለያዩ የጊዜ ቀጠሮዎችን ሲጠይቅ ቆይቷል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት አራዳ ችሎት በተከሳሹ ላይ አቃቢ ህግ ተደጋጋሚ የምርምራ ጊዜ ሲጠይቅ በመቆየቱ ከዚህ በሁዋላ ተጨማሪ ጊዜ መስጠት ተገቢ አይደለም በሚል፣ አቶ ኤርምያስ ...
Read More »Author Archives: Central
ልማት ባንክ ለሰፋፊ እርሻዎች ሲሰጥ በቆየው ብድር የደረሰበትን ኪሳራ የሚያጣራ አካል ተቋቋመ
ኢሳት (መጋቢት 14 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ኩባንያዎች ለሰፋፊ እርሻዎች ሲሰጥ በቆየው ብድር ላይ የደረሰበትን ኪሳራ የሚያጣራ አካል ተቋቋመ። ባንኩ ለበርካታ ኩባንያዎች በመቶ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ ቢያበድርም የሰጠው ብድር በትክክል የት እንደደረሰ እንደማይታወቅ የባንኩ ሃላፊዎች ገልጸዋል። በተለይ በተመሳሳይ የእርሻ መሬት ላይ የተሰጡ ተደራራቢ ብድሮች በባንኩ ላይ ከፍተኛ ኪሳራን ያስከተሉ ሲሆን፣ በብድር አሰጣጡ ሂደት መንግስት ከፍተኛ ...
Read More »ኢትዮጵያ መንግስት የፍትህ ሚኒስቴርን የሚያፈርስ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ አቀረበ
ኢሳት (መጋቢት 14 ፥ 2008) በሰብዓዊ መብቶች መከበር ዙሪያ ከተለያዩ አካላት በተደጋጋሚ ቅሬታ የሚቀርብበት የኢትዮጵያ መንግስት የፍትህ ሚኒስቴርን የሚያፈርስ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ አቀረበ። ለበርካታ አመታት በስራ ላይ የነበረውን ይህንኑ ሚኒስቴር በምስረታ ላይ የሚገኘው የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ተቋም እንደሚተካው ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በርካታ አንቀጾች እንዳሉት የተነገረለት ይኸው የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ተቋም በቅርቡ በፓርላማ ከጸደቀ በኋላ የፍትህ ሚኒስቴር ...
Read More »በማዕከላዊ እስር ቤት የህወሃት መርማሪዎች ከፍተኛ ሰቆቃ እንደሚፈጽሙ ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 14 ፥ 2008) በማዕከላዊ እስር ቤት የህወሃት መርማሪዎች ከፍተኛ አካላዊና ሞራላዊ ሰቆቃ በታሳሪዎች ላይ እንደሚፈፅሙ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ምክትል ፕሬዚደንት የነበሩት አቶ ዘመነ ምህረቱ ገለጹ። ከአስራ አራት ወራት እስር በኋላ ባለፈው መጋቢት 8, 2008 በዋስ የተለቀቁት አቶ ዘመነ ምህረት፣ በወህኒ ቤቶች ውስጥ ለምርመራ የተሰማሩት የህወሃት ገራፊዎች ለመናገር የሚከብድ ሰቆቃ በእርሳቸው ላይ እንደፈጸሙባቸው ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ...
Read More »ወደ ዳንሻ የሚወስዱት መንገዶች በቅድመ ሁኔታ ተከፈቱ
መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ሊላይ ሲሳይ፣ ከጎንደር ከተማ ተንስተው ወደ ዳንሻ ሲያመሩ መንገድ ላይ በጥቁር ላንድ ክሩዘር መኪና ይጓዙ የነበሩ ሰዎች፣ ከሾፌሮች ጋር በመነጋገር አፍነው ከወሰዱዋቸው በሁዋላ የአካባቢው ህዝብ ባስነሳው ተቃውሞ፣ መንገዶች ላለፉር አራት ቀናት ተዘግተዋል። በዳንሻና በሶረቃ ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን፣ መረጃው ወደ ተለያዩ ...
Read More »የአባይን ግድብ ሊጎበኙ የሄዱ የመንግስት ጋዜጠኞች ታገዱ
መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአባይን ግድብ 5ኛ የምስረታ አመት ለማክበር ሽር ጉድ እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ስለግድቡ ለመዘገብ ወደ ስፍራው የተንቀሳቀሱ ጋዜጠኞች መንገድ ላይ እገዳ ተጥሎባቸዋል። ከአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ የተውጣጣው የጋዜጠኞች ቡድን፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በሚል ወደ ግድቡ እንዳይገቡ ተደርጓል። የፕሮጀክቱ ስራ መሪ ኢንጂነር ስመኛው ጉብኝቱ ከመካሄዱ በፊት ተጠይቀው፣ ጋዜጠኞች ቢመጡ ችግር እንደሌለና ሙሉ ...
Read More »በኦሮምያ በተነሳው ግጭት ከፍተኛ ንብረት አልወደምም ሲሉ አቶ ሃይለማርያም ተናገሩ
መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኮሚኒኬሽን ሚኒስትርና የመንግስት ጋዜጠኞች በክልሉ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከፍተኛ የሆነ የንብረት መውደም አስከትሏል በማለት ሲዘግቡ ቢቆዩም፣ ጠ/ሚኒስትሩ ግን በባለሀብቶች ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ከ100 ሚሊየን ብር የማይበልጥና ጉዳቱም አነስተኛ በመሆኑ ባለሀብቶቹን እንዳላስደነገጠ ተናግረዋል። አቶ ሀይለማርያም ከመንግስታዊው ዜና አገልግሎት ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቃለምልልስ በሀገሪቱ ቱርክ፣ ቻይናና ህንድ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እንዳላቸው፣ ባለሀብቶቹ መሰል ...
Read More »ለንግድ ሱቆች በወጣ የሽያጭ ጨረታ አስደንጋ ጭ ዋጋ ተሰጠ።
መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአብዛኛው ባለፈው አመት መጋቢት ወር በ10ኛ ዙር እጣ የወጣባቸው ኮንደሚኒየም ቤቶች ጋር አብረው ለተሰሩ ለንግድ ሱቆች በወጣ ጨረታ አስደንጋጭ ዋጋ ተሰጥቷል። ንብ ባንክ በልደታ አካባቢ ለሚገኝ የኮንደሚኒየም የንግድ ቤት ለአንድ ካሬሜትር 101 ሺ111 ብር ከ11 ሳንቲም እጅግ የተጋነነ ዋጋ በመስጠት 87 ነጥብ 19 እና 76 ነጥብ 29 ካሬሜትር ሁለት ቤቶችን አሸናፊ ...
Read More »የኢህአዴግ መንግስት 499ሺ ቶን ስንዴን ለመግዛት አለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱን ሮይተርስ ዘገበ
ኢሳት (መጋቢት 13 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ መንግስት 499ሺ ቶን ስንዴን ለመግዛት አለም አቀፍ ጨረታ ማወጣቱን ሮይተርስ የአውሮፓ የንግድ ተቋማት ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘገበ። የእርዳታ ድርጅቶት በበኩላቸው ከሁለት ሳምንት በኋላ ለተረጂዎች የሚቀርብ እርዳታ ሊያልቅ የሚችል በመሆኑ ድርቁ የከፋ ጉዳት ማድረስ ይጀምራል ሲሉ በድጋሚ አሳስበዋል። ከአለም አቅፍ ገበያ ተገዝቶ ወደሃሪቱ የሚገባው የስንዴ አቅርቦት በትንሹ ...
Read More »የመሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር አዋጅ እየተዘጋጀ ነው ተባለ
ኢሳት (መጋቢት 13 ፥ 2008) በተለያዩ ክልሎች የህገ ወጥ መሳሪያዎች ዝውውር መስፋፋትን ተከትሎ የመሳሪያ ዝውውሩን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ (ህግ) እየተዘጋጀ መሆኑን የፌዴራልና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታወቀ። በጋምቤላ ክልል ብቻ በ13 ወረዳዎች ውስጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መኖርንና ችግሩ ከክልሉ ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት መፍጠሩን የክልሉ ባለስልጣናት ገልጸዋል። ክልሉ ከጎረቤት ደቡብ ሱዳን ጋር የሚዋሰን በመሆኑ በርካታ የህገ ወጥ መሳሪያዎች ዝውውር በክልሉ በመታየት ...
Read More »