Author Archives: Central

የሙስሊሙን የመብት ጥያቄ አንስተው ሲታገሉ በነበሩት በኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ

  ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው በአሸባሪነት ተወንጅለው በወህኒ ቤት ከሚገኙ ሙዝሊሞች በአንዱ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ። የግድያ ሙከራውን ያደረገው በእስር ቤት ውስጥ እስረኞችን የሚከታተል ሰላይ መሆኑን የአይን ምስክሮች ለኢሳት በላኩት መረጃ አመልክተዋል። የግድያው ሙከራው በእስር ቤቱ ሃላፊዎች የተቀነባበረ መሆኑን የሚገልጹት ምንጮች፣ ዓላማው የኮሚቴው አባላቱ ይቅርታ እንዲጠይቁ ለማስገደድ እንደሆነ ያምናሉ። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት ግድያ በፈጸሙ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅቻለሁ እያለ ነው

ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2008) የደቡብ ሱዳን መንግስት በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያን የፈጸሙ ታጣቂዎች ላይ ወታደራዊ እርምጃን ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታውቋል። ሃገሪቱ እወስደዋለሁ ያለችው ይኸው ወታደራዊ እርምጃ ከኢትዮጵያ መከላከልያ ሰራዊት ጋር በጥምረት እንዲሚካሄድ የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለፁን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል። በ13 መንደሮች የተፈጸመው ጥቃት በሺዎች በሚቆጠሩና ከባድ መሳሪያን በታጠቁ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች መከናወኑንም ጋዜጣው የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ በዘገባው ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ አመራሮች በጋምቤላ ግድያ ውዝግብ ውስጥ ገቡ

ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት በጋምቤላ ክልል በተፈጸመው ጥቃት የደቡብ ሱዳን መንግስትና አማጺያን እጃቸው የለበትም ቢልም የሃገሪቱ የፖለቲካ አመራሮች በጥቃቱ ዙሪያ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ተገለጠ። የሙርሴ ጎሳ ታጣቂዎች በብዛት የሚኖሩበት የደቡብ ክልል የቦማ ግዛት ገዥ የሆኑን ባባ መንዳ ጥቃቱ ኮብራ ተብሎ በሚጠራ አንጃ መፈጸሙን ይፋ እንዳደረጉ አሶሼይትድ ፕሬስ ሃሙስ ዘግቧል። ይኸው ታጣቂ ሃይልም በሙርሴና በአኝዋክ የጎሳ ታጣቂዎች የሚመራ ...

Read More »

የአሜሪካ ሴናተሮች በኢህአዴግ እየተወሰደ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ በጽኑ አወገዙ

ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2008) 11 የአሜርካ ሴናተሮች የኢህአዴግ መንግስት የአገሪቷን ህገ-መንግስቱን በመጠቀም ሃሳባቸውን በገለጹት ሰላማዊ ሰልፈኞች፣ ጋዜጠኞች፣ እና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት ላይ እያደረሰ ያለውን የጉልበትና የጠብ-አጫሪነት እርምጃ በጽኑ አወገዙ። የሜሪላንድ ግዛት ሴናተር ቤን ካርዲን፣ እንዲሁም ሲናተር ሩቢዮ  ሌሎች 9 ሴናተሮች  ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ፣ ህወሃት/ኢህአዴግ ፈጽሟል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ግድያ የአሜርካ መንግስት እንዲያጣራ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ...

Read More »

በጋምቤላ ታፍነው የተወሰዱትን ህጻናት ለማስመለስ የተወሰደ ወታደራዊ እርምጃ የለም ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2008) ባለፈው ሳምንት በጋምቤላ ክልል ተፈጽሞ በነበረው ጥቃት ታፍነው የተወሰዱ ከ100 በላይ ህጻናት ያሉበት ስፍራ ታውቋል ቢባልም በአካባቢው የተወሰደ ወታደራዊ እርምጃ አለመኖሩን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ሃሙስ ዘገቡ። ጥቃቱን ከደቡብ ሱዳን መነግስት ጋር በጋራ ለማካሄድ ምክክር በማካሄድ ላይ ሲሆን በዚሁ ጥቃት ልጆቻቸው ታፍነው የተወሰዱባቸው ወላጆች በበኩላቸው ልጆቻቸውን በህይወት እናገኛለን የሚል ተስፋ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ህጻናቱ በህይወት ለመታደግ ...

Read More »

ታንዛኒያ 74 ኢትዮጵያውያንን ወደኬንያ ድንበር አባረረች

ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2008) በቅርቡ ወደሃገሯ በሚገቡ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመር ስጋቷን ስትገልፅ የቆየችው ታንዛኒያ 74 ኢትዮጵያውያንን በኬንያ ድንበር አሰፈረች (ጣለች)። የታንዛኒያ መንግስት ማክሰኞ የወሰደው ይህንኑ እርምጃ ተከትሎም በሃገሪቱና በኬንያ መንስታት በኩል ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት መፍጠሩ ታውቋል። ”ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደሃገራቸው መመለስ ሲገባቸው በኬንያ ድንበር መጣላቸው ተገቢ አይደለም ስትል ኬንያ በታንዛኒያ መንግስት ላይ ተቃውሞዋን እንደገለጸች ኒውስ 24 የተሰኘ ጋዜጣ በዘገባው አስፍሯል። ...

Read More »

በጋምቤላ የተጨፈጨፉትን ወገኖች በተመለከተ የመከላከያ ሰራዊቱን ገመና የሚያጋልጡ መረጃዎች እየወጡ ነው

ሚያዚያ ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአካባቢው የሰፈረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች የሙርሌ ጎሳ አባላት በተደጋጋሚ የሚፈጽሙትን ጥቃት ለመከላከል አለመቻሉን የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩ ምሁራን ገልጸዋል። በደቡብ ሱዳን የሚገኙ የሙርሌ ጎሳ አባላት በኑዌር ኢትዮጵያውያን ላይ ፣ ሚያዚያ 7፣ 2008 ዓም ባደረጉት ጥቃት ከ230 በላይ ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ140 በላይ ህጻናትና ሴቶች ደግሞ በታጣቂዎቹ ተወስደዋል። መንግስት የተጠለፉት ዜጎች ...

Read More »

ኦፌኮ በኦሮምያ የሚደረገውን ተቃውሞ ለማዘናጋት መንግስት የሚወስደውን የማዘናጊያ እርምጃ ነቀፈ

ሚያዚያ ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ባወጣው መግለጫ ፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ዉስጥ ያለዉን ሕዝባዊ መነሳሳት ለማዘናጋትና ለማዳፈን ሲል መንግስት በሚቆጣጠራቸዉ የዜና ማሰራጫዎች ተጎጂ የሆነዉን ሕዝባችንን በይበልጥ ለመጉዳት ታስቦ በሚመስል መልኩ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ተከፍቷል ብሎአል። መንግስት መልካም አስተዳደርን ያጓደሉ ናቸዉ በማለት በመጀመሪያ 300 ባለሥልጣኖችን አሁን በቅርቡ ደግሞ 863 ባለሥልጣኖችንና ኃላፊዎችን ከሥልጣን አባርሬአለሁ በማለት መንግስት ...

Read More »

የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ታንዛኒያና ኬንያ ድንበር ላይ መጣላቸው ተዘገበ

ሚያዚያ ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሕገወጥ መንገድ የታንዛኒያን ድንበር አቋርጣችሁ ገብታችኋል ተብለው በታንዛኒያ ፍርድ ቤት የተበየነባቸውን የእስር ጊዜያት ያጠናቀቁ 74 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በታንዛኒያና ኬንያ ድንበር ታቬታ በምትባል የድንበር አዋሳኝ ስፍራ ላይ ተጥለዋል። የታንዛኒያ መንግስት በገባችሁበት በኬንያ ተመለሱ በማለት ሰብዓዊ መብታቸውን በመጣስ ከሕግ ውጪ ስደተኞቹን ከግዛቱ ሲያባርር፣ የኬንያ መንግስት በበኩሉ ስደተኞቹ የእስር ጊዜያቸውን እንደጨረሱ ወደ ትውልድ አገራቸው መላክ ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት በጋምቤላ ታፍነው የተወሰዱት ህጻናት ጉዳይ አሳስቦኛል አለ

ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2008) ከአምስት ቀን በፊት ከጋምቤላ ክልል ታፍነው የተወሰዱት ወደ 100 አካባቢ የሚጠጉት ህጻናት ደህንነት አሳስቦት እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታወቀ። በክልሉ የተፈጸመውን ግድያ ያወገዘው የህጻናት መርጃ ድርጅቱ ከቀያቸው ታፍነው የተወሰዱ ህጻናት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱም ጥሪውን አቅርቧል። የኢትዮጵያ መንግስት ታፍነው የተወሰዱ ህጻናትን ለመታደግ ዘመቻ መክፈቱን ቢገልጽም ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ታጣቂዎች የሚገኙበትን ስፍራ ...

Read More »