ኢሳት (ሰኔ 21 ፥ 2008) ኢትዮጵያ የጸጥታው ም/ቤት ተለዋጭ አባል ሆና ተመረጠች። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ ለጸጥታው ም/ቤት ተለዋጭ አባልነት ስትመረጥ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑን መረዳት ተችሏል። በንጉሱ እንዲሁም በደርግ የስልጣን ዘመናት ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ም/ቤት ተመርጣ አገልግላለች። የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ም/ቤት ካሉት 15 አባላት ውስጥ አስሩ በተለዋጭ አባልነት የሚያገለግሉ ሲሆን፣ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ያላቸው ...
Read More »Author Archives: Central
በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በሴቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 21 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ በሴቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ድርጅት (UNOCHA) አስታወቀ። ድርቁ ነፍሰጡሮችንና የሚያጠቡ እናቶችንና በከፍተኛ ሁኔታ እየጎዳቸው እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ድርጅት ማክሰኞች ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በወቅታዊ የሃገሪቱ የድርቅ አደጋ ዙሪያ ሪፖርትን ያወጣው ተመድ፣ በድርቁ መባባስ የተነሳ ነፍሰጡሮችና የሚያጠቡ እናቶች ከምግብ አቅርቦት ማነስ ጋር የተያያዙ ውስብስብ የጤና ችግሮች ...
Read More »በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ላይ አሜሪካን የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አዲስ ህግ አጸደቀ
ኢሳት (ሰኔ 21 ፥ 2008) የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ስጋቱን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ከቆየ በኋላ S.RES432 የተሰኘ የሰብዓዊ መብቶች ህግ በምክር ቤቱ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አማካኝነት አጸደቀ። ሰኔ 16 ቀን 2008 ዓም በሜሪካን ህግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) አባል በሆኑት የሜሪላንድ ግዛት ሴናተር ቤንጃሚን ካርቲን አቅራቢነት በውጭ ጉድዮች ቋሚ ኮሚቴ የጸደቀው ህግ የኢትዮጵያ ...
Read More »በመኪና ተጭነው ወደ እንግሊዝ ሲጓዙ የነበሩ 28 ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኢሳት (ሰኔ 21 ፥ 2008) የእንግሊዝ ፖሊስ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ኤርትራ የፈለሱ 28 ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። በእቃ መጫኛ መኪና ውስጥ የተገኙት እነዚህ ስደተኞች አስራ አንዱ ኤርትራውያን፣ አስሩ ሱዳናውያን ሰባቱ ደግሞ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ዴይሊ ሜይል የተባለ በእግሊዝ አገር የሚታተመው ጋዜጣ ማክሰኞ ባወጣው ዘገባ አመልክቷል። በእቃ መጫኛ ከባድ መኪና ታጭቀው ከተገኙት ከእነዚሁ ስደተኞች መካከል ህጻናትና ሴቶች ይገኙበታል ተብሏል። ስደተኞቹ መጸዳጃ ቤት ...
Read More »የኮንሶ ወረዳ ወደዞን እንድታድግ የቀረበው ጥያቄ በደቡብ ክልል መንግስት ውድቅ ተደረገ
ኢሳት (ሰኔ 21 ፥ 2008) የኮንሶ ወረዳ ነዋሪዎች ወረዳዋ የተሻለ እድገት እንዲኖራት በማለት ወደ ዞን እንድትሻገር ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ውድቅ ማድረጉ ተገለጸ። በኮንሶ የተነሳው ራስን የማስተዳደር ጥያቄ በተወሰኑ ጥቂት ሰዎች የተጠየቀ እንጂ የአብዛኛው ህዝብ ጥያቄ አይደለም ያለው የደቡብ ክልል መንግስት ምክር ቤት፣ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም ሲል በመንግስት መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል። የኮንሶ የራስ አስተዳደር ጥያቄ አስተባባሪዎች በበኩላቸው ...
Read More »የህወሃት አባላት ያልሆኑ የደህንነት አባላት በጥርጣሬ እየታሰሩ ነው
ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት አባል የነበሩና በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ በተለይም በሶማሊያ በሚካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ላይ ቁልፍ ሚና ነበራቸው የተባሉ 3ቱ ነባር የደህንነት አባላትና አስተባባሪዎች ከተገደሉ በሁዋላ፣ ከግድያው ጀርባ እጃቸው ሊኖርበት ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ የህወሃት አባላት ያልሆኑ የሌሎች ብሄረሰቦች የደህንነት አባላት እየተያዙ ነው። እስካሁን ከተያዙት መካከል አብዛኞቹ የኦሮሞ ተወላጅ ...
Read More »ቤታቸው በህገወጥ መንገድ ይፈርስባችሁዋላ በመባላቸው ሰዎች ተቃውሞአቸውን ገለጹ
ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ወረዳ 11 በአካባቢው መጠሪያ ቀርሳና ኮንቱማ በሚባሉ አካባቢዎች ቤቶችን በህገወጥ መንገድ ሰርታችሁዋል የተባሉ ነዋሪዎች፣ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ካላፈረሱ ግን መንግስት እንደሚያፈርስባቸው ከተነገራቸው በሁዋላ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል። “አንድ የአራት እናት ልጆችና የአንድ ሳምንት አራስ የሆኑት እናት “ መሄጃ የለኝም፣ መሞቴ ነው ድረሱልኝ “ ብላለች። ልጆቼን ...
Read More »ፍርድ ቤት እነ አቶ አግባው ሰጠኝ እንዲከላከሉ ወሰነ
ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ በተከሰሱ 16 ተከሳሾች ላይ ብይን የሰጠ ሲሆን፣ አቶ አግባው ሰጠኝን ጨምሮ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን፣ በላይነህ ሲሳይ፣ አለባቸው ማሞ፣ አወቀ ሞኝሆዴ ፣ ተስፋየ ታሪኩ፣ ቢሆነኝ አለነ፣ ተፈሪ ፈንታሁን ፣ፈረጀ ሙሉ፣ አትርሳው አስቻለው ፣ እንግዳው ...
Read More »ከ100 በላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መዘጋታቸው ተነገረ
ኢሳት (ሰኔ 20 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ህግ ከሚፈቅደው ውጪ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል የተባሉ ከ100 በላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተዘጉ። ከበርካታ አመታት በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት ስራ ላይ የነበሩ ድርጅቶች ከተቋቋሙበት አላማ ውጭ ሲንቀሳቀሱ እና ያለመንግስት ፈቃድ የባንክ ሂሳብ ሊከፍቱ የነበሩ ናቸው ሲል የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ሰኞ አስታውቋል። የዘንድሮ በጀት አመት ሪፖርቱን ያቀረበው ኤጀንሲው እርምጃ የተወሰደባቸው 108 ድርጅቶቹ የገቢ ...
Read More »በታንዛኒያ የሞቱ የ19 ኢትዮጵያውያን ሬሳ ኢትዮጵያ ገባ
ኢሳት (ሰኔ 20 ፥ 2008) ለውዝ፣ ጥራጥሬና አሳ በጫነ የጭነት መኪና ተጭቀው ከታንዛኒያ ወደ ዛምቢያ ለመሻገር ከሞከሩ 95 ኢትዮጵያውያን 19ኙ ህይወታቸው ማለፉ ሲታወስ፣ የ19ኙም አስከሬን ኢትዮጵያ መግባቱ ታውቋል። መድረሻቸውን ደቡብ አፍሪካ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ተነስተው ኬንያ አቋርጠው ታንዛኒያ የደረሱት ኢትዮጵያውያን ዛምቢያ ላይ ህይወታቸው ያለፈው በሳምንቱ መጨረሻ ነበር። በረሃ አቋርጠው ሲጓዙ ታፍነው ከሞቱን 19 ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ፣ ሌሎች 76 ኢትዮጵያውየን በመኪና ውስጥ የነበሩ ...
Read More »