Author Archives: Central

ኢትዮጵያን እንደ አገር ለመቀጠል ከሚያሰጋቸው አገራት ተርታ ተመደበች

ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓመታዊው የአገራት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባቸውና ለሰው ልጆች ደኅንነት አስጊ የሆኑ አገራት ጥናት የደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ መደረጉን ተከትሎ፣ በዓለማችን ላይ ያሉ ለወደፊቱ እንደ አገር ለመቀጠል ከፊት ለፊታቸው ሥጋት ከተደቀነባቸው 25 አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ሆናለች። በዓመታዊው የአገራት የደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባቸው ለዜጎች ምቹ የደኅንነት ዋስትና ያላቸው በመባል ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ የዜጎችን ህይወት አስጊ ደረጃ ላይ እንደጣለው ጎል ኢትዮጵያ አስታወቀ

ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ውስጥ ተከስቶ የማያውቅ ርሃብ በኢትዮጵያ ውስጥ መከሰቱንና ከ10 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በርሃብ መጠቃታቸውን ጎል ኢትዮጵያ የድርቁን ሰለባዎች በማነጋገር ጥናታዊ ሪፓርቱን አቅርቧል። የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆኑ ወላጅ አልባ ሕጻናትን የሚያሳድጉ ወ/ሮ ዳኒስቶ የተባሉ በደቡብ ክልል ነዋሪ የደረሰባቸውን ሰቆቃ ሲናገሩ ”ባለቤቴን በድንገተኛ የሁለት ቀናት ሕመም በሞት ካጣሁ ...

Read More »

ህብር ስኳር ከመንግስት ጋር ቅርበት ያላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ባደረሱት ጫና ፈተና ውስጥ መሆኑ ተነገረ

ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2008) ስኳር በማምረት በሃገሪቱ ያለውን የስኳር ዕጥረት ለመቅረፍ ብሎም የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት የተቋቋመው ህብር ስኳር አክሲዮን ማህበር በመንግስት በኩል በተደረገበት ጫና እንዲሁም ግለሰቦች ባሳደሩበት ተፅዕኖ ሁለቱ ስራ አስኪያጆች ሲሰደዱ ድርጅቱ በህወሃት የጦር ጄኔራሎች በሚመራው ሜቴክ እስረኛ መሆኑ ተገለጸ። የመጀመሪያው ስራ አስኪያጅ አቶ አማረ ለገሰ ግፊቶች ሲበረቱባቸው ስራቸውን ለቀው ወደ አሜሪካ መመለሳቸውን ተከትሎ በስራ አስኪያጅነት የተሾሙትና አሁን ...

Read More »

የመኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ በተካሄደ ግጭት ቢያንስ ሶስት ሰዎች ተገደሉ

ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማ ህገወጥ የተባሉ የመኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ የተካሄደ እርምጃ ግጭትን ቀስቅሶ ሁለት የፖሊስ አባላትንና አንድ የወረዳ ስራ አስፈጻሚ ተገደሉ። በነዋሪዎች ዘንድ ተቃውሞን በቀሰቀሰው በዚሁ ግጭት መሞታቸው ከተረጋገጠው ፖሊሶችና የስራ ሃላፊ በተጨማሪ ሌሎች ፖሊሶችና የወረዳ አስተዳደሮች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ በጸጥታ ሃይሎች ላይ ግድያን የፈጸሙ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ቤታቸው ይፈርስባችሁዋል የተባሉ ነዋሪዎች ባስነሱት ተቃውሞ ፖሊሶች ተገደሉ

ሰኔ ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወረዳ አንድ በተለምዶ ቀርሳ፣ ኮንቶማ፣  ኤንቱ ሞጆ፣ ዱላ ማርያም፣ ሰፈራ፣ ማንጎ፣ ገብሬአል በሚባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ አባወራዎችና እማወራዎች የሚኖረባቸውን አካባቢወች በማፍረስ መሬቱን ለባለሀብቶች ለመስጠት የተጀመረውን እንቅስቃሴ የተቃወሙ ነዋሪዎች ከጸጥታ ሃይሎች  የተሰነዘረባቸውን ጥቃት ተከትሎ ድንጋዮችን በፖሊሶች ላይ ወረውረዋል። የመብራት ሃይል ሰራተኞች ኮንቶማ እና ማንጎ ሰፈር በሚባለው አካባቢ የሚገኘውን የሃይል ማስተላለፊያ ...

Read More »

በምእራብ ጎጃም ደንበጫ ከተማ የተጀመረው የመምህራንና የተማሪዎች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

ሰኔ ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ በደንበጫ የተጀመረው የተማሪዎች እና የመምህራን አድማ መቀጠሉን ተከትሎ ፣ፖሊሶች በሃይል በወሰዱት እርምጃ በርካታ ተማሪዎች ተጎድተዋል። ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ የ11ኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተይዘው መታሰራቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ ግጭቱ ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል ብለዋል:: መምህራን የጠየቅነው የደሞዝ ማስተካከያ ካልተደረገ የተማሪ ውጤት አንሰጥም ማለታቸውን ተከትሎ፣ ተማሪዎች ከመምህራን ...

Read More »

በሃመር ወረዳ የተጀመረው ግጭት መቀጠሉ ተሰማ

ሰኔ ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃመር እና ኤርቦሬ ጎሳዎች መካከል የተጀመረው ግጭት ተባብሶ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ችግሩ ከግጦሽ መሬት ጋር በተያያዘ ይጀመር እንጅ፣ ከትናንት ጀምሮ መልኩን በመቀየር በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሎአል። የአገር ሽማግሌዎች ችግሩን ለመፍታት ጥያቄ ሲያቀርቡ የዞኑ የፖለቲካ ምክትል ሃላፊና የሀመር ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ወሌ ለአገር ሽማግሌዎች_ አርበኞች ...

Read More »

ከመከላከያ ሰራዊት ተሰናብተው በየከተማው የሚገኙ ዜጎች ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡

ሰኔ ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እሁድ ሰኔ 19/2008 በብቸና ከተማ በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ቅሬታቸውን ያቀረቡት የተመላሽ ሰራዊት አባላት በደረቅ ቆሻሻ ተሰብስበው በመሰማራት ኑሯቸውን በመግፋት ላይ ቢሆኑም የመንግስት አመራሮች ግን ከእርዳታ ይልቅ ጥላቻ እያሳዩዋቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ወደ መከላከያ ሰራዊቱ እንዲገቡ በርካታ እንክብካቤና የማስመሰያ ቅስቀሳ ተደርጎላቸው እንደተሸኙ የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎች በተቀናሽነት ሲመለሱ ግን አግባብ ባልሆነ ...

Read More »

ቢሮውን በአዲስ አበባ የከፈተው የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ለመንግስትና ለግል ተቋማት ብድር ሊሰጥ ነው ተባለ

ኢሳት (ሰኔ 21 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ያጋጠመውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ተከትሎ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ቢሮውን በአዲስ አበባ በመክፈት ብድርን ከመንግስትና ለግል ተቋማት ለማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት ፈጸመ። በአለም አቀፍ ደረጃ ግዙፍ የሆነው ይኸው ባንክ ቅርንጫፍ ቢሮውን በኢትዮጵያ በመክፈት ብድርን ማቅረብ እንደሚጀምር ታውቋል። ሃገሪቱ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ተከትሎ የቱርኩ ዚሪት ባንክ ከወራት በፊት ከሃገር ውስጥ ብድርን ከማቅረብ ስምምነት የፈጸመ ሲሆን ...

Read More »

“አርበኞች ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ የደረግነው ጉዞ የሃገር ወዳድነት መለኪያ እንጂ ወንጀል አይደለም” ብርሃኑ ተክለያሬድና እየሩሳሌም ተስፋው

ኢሳት (ሰኔ 21 ፥ 2008) ወደ ኤርትራ ያደረግነው ጉዞ የሃገር ወዳድነት መለኪያ እንጂ ወንጀል አይደለም ሲሉ እነብርሃኑ ተክለያሬድ ለፍርድ ቤት የተከሳሽነት ቃላቸውን ሰጡ። አርበኞች ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊሻገሩ ሲሉ ተይዘው በወህኔ ቤት የሚገኙት የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባላት የነበሩ ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድና ወጣት እየሩሳሌም ተስፋው ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ይህንን ያቀረቡት በጽሁፍ ሲሆን፣ እንዳያነቡ መከልከላቸውም ተመልክቷል። ...

Read More »