Author Archives: Central

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ኢትዮጵያ ለድርጅቱ መርሆዎች እንድትገዛ ጥያቄ አቀረቡ

ኢሳት (ነሃሴ 6 ፥ 2008) ሂውማን ራይትስ ዎችን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በቅርቡ የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና የተመረጠችው ኢትዮጵያ ለድርጅቱ መርሆዎች እንድትገዛ ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል። ሃገሪቱ ያላት የቆየ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ታሪክ ቋሚ ላልሆነው የተለዋጭ አባልነት አያበቃትም፣ አባል ሆና ከተመረጠችም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተቀመጡ አለም አቀፍ ድንጋጌዎችንና ደንቦችን ታክብር ሲሉ ተቋማት በመጠየቅ ላይ ናቸው። ...

Read More »

የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች የመፍትሄ ያለህ እያሉ ነው

ነሃሴ  ፮ ( ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተቃውሞ እየተናጡ ባሉት የአማራ እና የኦሮምያ ክልሎች ዙሪያ የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የክልል ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የፌደራል ባለስልጣናት የቪዲዩ ኮንፈረንስ  እያደረጉ ነው፤ ስብሰባው መፍትሄ ማመንጨት አልቻለም። በቪዲዩ ኮንፈረንሱ ላይ የአማራ ፤ ኦሮምያ እና ትግራይ አመራሮች ፤ ቀን ላይ ካቢኒያቸውን ሰብስበው ሲጨርሱ ምሽት ከጠቅላይ ሚንስትሩ እና አማካሪዎቻቸው ጋር በቪዲዩ ኮንፈረንስ እየተነጋገሩ ...

Read More »

በባህርዳር ከተማ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችና የከተማዋ ነዋሪዎች  የታሰሩ ወጣቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ  አፈሳውም እንዲቆም ጠየቁ

ነሃሴ  ፮ ( ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአንድ ቀን በፊት በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችን በመሰብሰብ ሃገሪቱ ሰላማዊ እንድትሆን ህብረተሰቡን እንዲመክሩ ጠይቀዋል፡፡ የሃይማኖት አባቶች ለርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት ምላሽ በተለያየ ጊዜ ህዝቡ የሚያቀርበውን ጥያቄ በይደር ከማቆየት ይልቅ አፋጣኝ የሆነ መልስ መስጠት እንደሚገባ የተናገሩ ሲሆን አሁንም በወልቃይት የአማራ ማንነት ላይ የተነሳውን የህዝብ ...

Read More »

ህወሃት በበላይነት የሚመራው መንግስት በብሄረሰቦች መካከል መቃቃር እንዲፈጠር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 5 ፥ 2008) በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ሰላማዊ ሰልፈኞች በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ህዝባዊ ተቃውሞች በአገሪቷ ለተፈጠረው ቀውስ የህወሃትን አመራር ተጠያቂ ነው ቢሉም፣ ስልጣን ላይ ያለው የህወሃት ቡድን በበኩሉ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የትግራይ ህዝብን በጅምላ ኢላማ ያደረጉ ናቸው በማለት በሰላማዊ ሰልፈኞቹ ላይ ክስ እያቀረበ እንደሚገኝ በአሜሪካ አገር ዋሽንግተን ዲሲ የሚሰራጨው ናሽናል ፐብሊክ ሬዲዮ (NPR) የተባለ ጣቢያ በረቡዕ ስርጭቱ ገለጸ። በኦሮሚያና በአማራ ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያለው ተቃውሞ መፍትሄን እንዲያገኝ ሃሙስ ጥሪ አቀረበ

ኢሳት (ነሃሴ 5 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ዋነኛ የልማት አጋር የሆነው የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ በመካሄድ ላይ ያለው ተቃውሞ ያለምንም መዘግየት በሰላማዊ መንገድ መፍትሄን እንዲያገኝ ሃሙስ ጥሪውን አቀረበ። በተለይ ከቀናት በፊት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በተፈጸሙ ግድያዎች ስጋት እንዳደረበት የገለጸው ህብረቱ ተጨማሪ ሁከትና ግጭት ለሰላማዊ መፍትሄ እንቅፋት እንደሚሆን አስታውቋል። በሁለቱ ክልሎች ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ግድያ ምክንያት የሆነውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ መግለጫን ያወጣው ...

Read More »

በጎንደር በሀገር ሽማግሌዎች ተቃውሞን ለማብረድ እየተካሄዱ ያሉ ድርድሮች በነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታን መቀስቀሱ ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 5 ፥ 2008) በሰሜን ጎንደር ዞን ስር በሚገኙ በርካታ ወረዳዎች የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ሃሙስ ድረስ ስራ አለመጀመራቸውንና በሀገር ሽማግሌዎች ተቃውሞን ለማብረድ እየተካሄዱ ያሉ ድርድሮች በነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታን መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። በዞኑ አለፋ ወረዳ እና አካባቢዋ ያሉ ነዋሪዎች ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በዞሩ ባሉ ወረዳዎች የመንግስት መዋቅሮች ሙሉ ለሙሉ ስራ ማቆማቸውን ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት ግድያውን አስመልክቶ የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያቀረበውን የማጣራት ጥያቄ እንደማይቀበል ገለጸ

ኢሳት ( ነሃሴ 5 ፥ 2008) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው ግድያ በአለም አቀፍ ገለልተኛ አካል ማጣራት እንዲካሄድበት ሲል ያቀረበን ጥያቄ የኢትዮጵያ መንግስት ፈቃደኛ እንደማይሆን ሃሙስ አስታወቀ። የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ ረቡዕ ባስተላለፈው ጥሪ የኢትዮጵያ መንግስት ለአለም አቀፍ መርማሪ አካል በሩን ክፍት እንዲያደርግ ከዋና መስሪያ ቤቱ ስዊዘርላንድ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። ይሁንና ለተባበሩት መንግስታት ጥሪ ምላሽን የሰጠው የኢትዮጵያ ...

Read More »

የመሬት ፖሊሲው ካልተሻሻለ ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ ዕርስ በእርስ ግጭት ሊያመራ ይችላል ተባለ

ኢሳት ( ነሃሴ 5 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት የመሬት ፖሊሲው ላይ ማሻሻያ የማያደርግ ከሆነ በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ ዕርስ በእርስ ግጭት ሊያመራ ይችላል ሲሉ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር መግለጻቸውን ሮይተርስ ሃሙስ ዘግቧል። በሃገሪቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ናት ሲሉ ለዜና አውታሩ የገለጹት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ህዝብ ገዢው የኢህአዴግ መንግስት ለ25 አመታት በፈጸመው ድርጊት መሰላቸታቸውን ...

Read More »

በመላ አገሪቱ የሚታየው ውጥረት እንደቀጠለ ነው

ነሃሴ  ፭ ( አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ገዢው ፓርቲ  በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስቆም የጸጥታ ሃይሉን በብዛት በማሰማራት ውጥረቱን አባብሶታል። የፌታችን ቅዳሜ እና እሁድ ተቃውሞ ይካሄድባቸዋል በሚባሉት በርካታ የ አማራ ክልል ወረዳዎች ብዛት ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የፌደራል ፖሊሶች እየገቡ ሲሆን፣ ተቃውሞውን ሊያስተባብሩ ይችላሉ የተባሉት ደግሞ እየታፈሱ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ  የተለያዩ አለማቀፍ ሚዲያዎች ሽፋን እየሰጡት ነው።

ነሃሴ  ፭ ( አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታላላቅ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃንና የሰብዓዊ መብት ተቋማት በኢትዮጵያ በተለይ በኦሮሚያና አማራ ክልል ውስጥ የተካሄደውን የጅምላ ግድያ በስፋት አትኩሮት ሰጥተው ዘግበውታል። በዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ጨምሮ መላውን ኦሮሚያ ክልል በጎንደርና አካባቢው በባህርዳር የተካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች በጸጥታ አስከባሪዎች በግድያ ምላሽ መሰጠቱን ቢቢሲ ዘግቧል። ሁለቱ ታላላቅ የአገሪቱ ብሔረሰቦች  አነስተኛ ቁጥር ባለው አንድ ...

Read More »