ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዛሬው እለት በ9 ኦራል መኪኖች የተጫኑ ወታደሮች ዶጋው ገብተዋል። በከፍተኛ የቁጣ ስሜት ውስጥ የሚገኙት ወታደሮች ህዝቡ የኢሳት ስርጭቶችን እንዳይመለከት ለማድረግ በከተማዋ ያሉ ዲሾችን ሲነቃቅሉ ውለዋል። ነዋሪዎች እንደገለጹት ትናንት የግለሰቦችን የጦር መሳሪያዎች ለማስፈታት እንዲሁም በአካባቢው የተደራጁ ሃይሎች አሉ በሚል ከጎንደር የተንቀሳቀሰው የመከላከያ ሰራዊት፣ ዶጋው በረሃ ላይ ሲደርስ ከነጻነት ተዋጊዮች ተኩስ ተከፍቶበታል። ታዋቂው ...
Read More »Author Archives: Central
በደቡብ ክልል በአንድ ቀን በ3 አካባቢዎች በተነሳ ግጭት ወታደሮች ቆሰሉ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግጭቱን ተከትሎ በበና ኩሌ ወረዳ አልዱባ ቀበሌ ፖሊስ ጣቢያው ሙሉ በሙሉ ሲወድም፣ በበና ኩሌና ሃመር ወረዳዎች አዋሳኝ በሆነው ኤሪያ አንቡሌ ቀበሌ ደግሞ የቱሪስቶች መኪና በጥይት ተመቷል።በሳላማጎ ወረዳ በኃይል-ውኃ/ ኩራዝ 2 ስኳር ፕሮጀክት ማዞሪያ በፖሊሶች ላይ በደረሰ ጥቃት ደግሞ 3 ፖሊሶች ቆስለዋል። ግጭቶችን አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ምክትል ሊቀመንበር ...
Read More »በምዕራብ አርሲ በርካታ ነጋዴዎችና ወጣቶች ታሰሩ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቢሾፍቱ ከደረሰው እልቂት በሁዋላ ከፍተኛ ህዝባዊ አመጽን ባስተናገዱት አጄና አጎራባች ከተሞች የሚገኙ የአገር ሽምጋሌዎች፣ ነጋዴዎች፣ ምሁራን፣ ባለሀብቶችና ወጣቶች ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል። ኢሳት እና ኦኤም ኤንን የሚመለከቱ ሰዎች እየተደበደቡ ወደ እስር ቤት የሚወሰዱ ሲሆን፣ ዲሾቻቻውም እንዲነቀል ተደርጓል። ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አሁንም በአካባቢው ሰፍሯል። ባለፈው ሳምንት በዚህ ዞን በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከአንድ መቶ በላይ ...
Read More »የኢትዮጵያ መጻኢ እድል አስፈሪ ነው ሲል ዘኢኮኖሚስት መጽሄት ዘገበ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱንና አሳሳቢ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ዘ ኢኮኖሚስት መጽሄት ኢትዮጵያ ላይ አትኩሮ በሰራው የፖለቲካ እና ምጣኔ ሃብታዊ ዳሰሳ አመልክቷል። በቢሾፍቱ ከተማ ኢሬቻ የምስጋና በዓል ለማክበር በተሰበሰቡት ንፁሀን ዜጎች ላይ የደረሰውን እልቂት “አሰቃቂ” በማለት የዘገበው ዘ ኢኮኖሚስት፣ ከዚህ አሰቃቂ እልቂት በኋላ በኢትዮጵያ አስቸኳይ የጊዜ አዋጅ መታወጁን ፣ ...
Read More »ግብጽ የኢትዮጵያን ክስ ውድቅ አደረገች።
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በሀራቸው ላይ ያቀረበችውን አማጽያንን የመርዳት ክስ አጥብቀው አስተባብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ትናንት ሀሙስ ባደረጉት በዚሁ ንግግራቸው መንግስታቸው የኢትዮጵያ አማጽያንን እና ተቃዋሚዎችን ደግፎ እንደማያውቅና ይህንን የማድረግ ሀሳብም እንደሌለው መግለጻቸውን አሶሲየትድ ፕሬስን የጠቀሰው የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ያመለክታል። ግብጽ በአባይ ወንዝ ላይ እየተካሄደ ያለውን ግዙፍ የአኤልክቲሪክ ኃይል ...
Read More »በየመን እስር ቤት ታስረው የነበሩ ወደ 1000 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ባልታወቁ ሃይሎች መለቀቃቸው ተገለጸ
ኢሳት (ጥቅምት 3 ፥ 2008) በሰሜን የመን በሚገኝ አንድ እስር ቤት ውስጥ የነበሩ ወደ 1ሺ አካባቢ ኢትዮጵያውያን ማንነታቸው ባልታወቁ ሃይሎች ከእስር ቤት እንዲወጡ ተደርጎ ወደ ሌላ ግዛት መወሰዳቸውን የሃገሪቱ ባለስልጣናት ሃሙስ ይፋ አደረጉ። አታክ በሚባል ግዛት ውስጥ በሚገኘው የሻብዋ ከተማ እስር ቤት የነበሩት ስደተኛ ኢትዮጵያውያኑ የተቀነባበረ የማስመለጥ ድርጊት እንደተፈጸመባቸውና እስረኞቹ በሙሉ በተሽከርካሪ ወደ ሌላ ግዛት መወሰዳቸውን አል አረቢ የተሰኘ የየመን ...
Read More »በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የውጭ ሃገራት ተወካዮች መንግስት የተቋረጠውን የኢንተርኔት አገልግሎት አለማስጀመሩ በስራቸው ላይ ችግር እየፈጠረ ነው አሉ
ኢሳት (ጥቅምት 3 ፥ 2008) መቀመጫውን በአዲስ አበባ ከተማ ያደረጉ የውጭ ሃገራት ተወካዮች መንግስት የተቋረጠውን የኢንተርኔት አገልግሎት አለማስጀመሩ በስራቸው ላይ ችግር መፍጠሩን ገለጡ። ረቡዕ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ጋር ተግባራዊ ተደርጎ በሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዙሪያ ውይይትን ያካሄዱ አምባሳደሮች የኢንተርኔት አገልግሎት መቼ እንደሚቀጥል ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል። ይሁንንና የመንግስት ባለስልጣናት አገልግሎቱ መቼ እንደሚጀምር ማረጋገጫ አለመሰጠቱ ስጋት እንደሆነባቸው በኢትጵያ የዴንማርክ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረትና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጠንካራ ዕርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ
ኢሳት (ጥቅምት 3 ፥ 2008) በኢትዮጵያ እየተባባሰ መጥቷል ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ግምት ውስጥ በማስገባት የአውሮፓ ህብረትና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጠንካራ ዕርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ። የአውሮፓ ፓርላማ ንዑስ ኮሚቴ በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ባዘጋጀው መደረክ ላይ የታደመው ሂውማን ራይትስ ዎች፣ የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እጅጉን አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን አብራርቷል። በመድረኩ ለተሳተፉ የአውሮፓ ህብረትና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ተወካዮች የሰብዓዊ መብት ...
Read More »በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ከ500 ሰዎች በላይ መሞታቸውን የኢትዮጵያ መንግስት አመነ
ኢሳት (ጥቅምት 3 ፥ 2008) በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ሲካሄዱ ከነበሩ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ጋር በተገናኘ ከ500 በላይ ሰዎች መሞታቸውን መንግስት አመነ። ሂውማን ራይትስ ዎችና ሌሎች አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ለወራት በዘለቀው በዚሁ ተቃውሞ ከ700 የሚበልጡ ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን ሲገልፅ ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በኦሮሚያ ክልል ብቻ 170 ሰዎች፣ በአማራ ክልል ደግሞ 120 አካባቢ ሰዎች መሞታቸውን በመግለፅ ...
Read More »የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ህዝባዊ ተቃውሞ እያባባሰው ሊሄድ እንደሚችል ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ዘገበ
ኢሳት (ጥቅምት 3 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሃገሪቱ በመስፋፋት ላይ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ከመቆጣጠር ይልቅ እያባባሰው ሊሄድ እንደሚችል ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አቋሙን በሚገልጽበት ርዕሰ አንቀጹ ባልስተላለፈው መልዕክት አስታወቀ። የኢትዮጵያ አመራሮች ስኬት ሊያመጣ ያልቻለውን የአፈና ፖሊሲያቸውን አጠናከረው ቀጥለዋል ሲል የገለጸው አለም አቀፍ ጋዜጣው፣ በቅርቡ ተግባራዊ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የዚህ ማሳያ መሆኑን በጽሁፉ አትቷል። ተግባራዊ ተደርጎ ...
Read More »