(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2011) በጉራጌ ዞን ማረቆና መስቃን ወረዳዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት የየወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች እጅ አለበት በሚል በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉ ተገለጸ። በክልል ደረጃ በደኢህዴን ውስጥየሚገኙና የግጭቱ ዋና አቀናባሪዎችን ያልነካ እስር ችግሩን አይፈታውም ሲሉ ነዋሪዎች በመግለጽ ላይ ናቸው። የደቡብ ክልል ፖሊስ የማረቆ ወረዳ አስተዳዳሪን አቶ በለጠ ደራሮንና የመስቃን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታህ ሸምሱን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ባሳወቀበት መግለጫው ግጭቱን በመቀስቀስና በማባባስ ...
Read More »Author Archives: Central
በሞያሌ በትንሹ 12 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2011) በሞያሌ በሚገኘው የበቀለ ሞላ ሆቴል ላይ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ 12 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። ጥቃቱ የተፈጸመው የቦረና ኦሮሞና የሶማሌ ገሪ ብሄረሰብተወካዮች ከፌደራል መንግስቱ ሰራዊት አመራሮች ጋር ውይይት እያደረጉ በነበረ ጊዜ መሆኑን አዲስ ስታንዳርድ የተሰኘ የዜና ምንጭእማኞቹን ጠቅሶ ዘግቧል። በጥቃቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሳተፋቸውም ተገልጿል። በሞያሌ ሳምንቱን በደፈነውና እንደአዲስ ባገረሸው ግጭት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውም ታውቋል። የሞያሌው ግጭት መነሻው ...
Read More »በኢየሩሳሌም ጎለጎታ የሃይማኖት አባቶች ተደበደቡ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2011) በኢየሩሳሌም ጎለጎታ ግቢ ውስጥበሃይማኖት አባቶች ላይ ድብደባ መፈጸሙ ተገለጸ። በቤተክርስቲያኒቱ ቅጥር ግቢ በሚካሄድ ስብስባ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት አባቶቹ ላይ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ መፈጸሙን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ ብጹእ አቡነ እምባቆምን ጨምሮ ሶስት አባቶች በተፈጸመባቸው ድብደባ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል። ድብደባውን የፈጸሙት የህወሀት ደጋፊ የሆኑ ሶስት የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ሲሆኑ በእስራዔል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ...
Read More »ሕገ-መንግስትን መጣስ ዛሬ የተጀመረ አይደለም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 8/2011) በኢትዮጵያ ውስጥ ሕገ-መንግስት መጣስም ሆነ በክልሎች ጣልቃ መግባት ዛሬ የተጀመረ አይደለም ሲሉ ሌተናል ጀኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይ ገለጹ። ከአንድ አካባቢ የመጡ ሰዎች የፖለቲካስልጣኑን በበላይነት ይዘው ሕገ-መንግስቱን እየጣሱ ሕግ ሳይገዛቸው የቆዩበት ሁኔታ ዛሬ ለተከሰተው ችግር አስተዋጽኦ ማድረጉንምጄኔራሉ አመልክተዋል። የሕዉሃት ነባር ታጋይ እና በኢህአዴግ የስልጣን ዘመን እስከ ግንቦት ወር 1993 የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም የነበሩት ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ...
Read More »በኮንጎ ዴሞክራቲክ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከፍተኛ ውጥረት አነገሰ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 8/2011)በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ በመጪው ዕሁድ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሃገሪቱ ከፍተኛ ውጥረት መፍጠሩ ተሰማ። አሜሪካ ዜጎቿ ከርዕሰ መዲናዋኪንሻሳና ሌሎች ከተሞች ለቀው እንዲወጡ ያሳሰበች ሲሆን ብሪታኒያ ዜጎቿ ወደ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እንዳይገቡ ማስጠንቀቂያሰጥታለች። ላለፉት 17 ዓመታት በመሪነት የቆዩትን ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላን ለመተካት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከፊታችን እሁድ ታህሳስ 23 የሚካሄደው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለተቀናቃኝ ወገኖች ጥሪ አቅርቧል። ...
Read More »ወደ ቤተ መንግስት ያለፈቃድ ያቀኑት ወታደሮች ዝርዝር ቅጣት ይፋ ሆነ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 8/2011) ወደ ቤተ መንግስት ያለፈቃድ ካቀኑ ወታደሮች ውስጥ 66ቱ ላይ የተላለፈባቸው ዝርዝር ቅጣት ይፋ ሆነ። ከነትጥቃቸው ያለፈቃድ ወደ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ካመሩት 200 የሰራዊት አባላት መካከል 66ቱ ላይ ከ5 እስከ 14 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡ ፋይል ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ከ500 ሰው በላይ በተገኘበት ግልጽ ችሎት መታየቱ ታውቋል። በውሳኔው መሰረት አንድ ተከሳሽ በ14 ዓመት ጽኑ ...
Read More »አቶ መላኩ ፈንታ የአልማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆኑ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 8/2011) አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር(አልማ) ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ፡፡ በሚኒስትር ማዕረግ የቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ በሕወሀት አገዛዝ ወቅት በሐሰት ተወንጅለው ላለፉት 5 አመታት በእስር ላይ መቆየታቸው ይታወሳል። ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ ያገኙት አቶ መላኩ ፈንታ ለእስር በባለስልጣናት የተዳረጉት የተሰወረ ቀረጥ እንዲከፈል በመታገላቸው እንደሆነ ሲነገር ...
Read More »ፕሬዝዳንት ኢሳይስ ኬንያ ገቡ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 5/2011) በኢትዮጵያ፣ኤርትራና ሶማሊያ መሪዎች መካከል የተጀመረው የሶስትዮሽ የምክክር መድረክ አካል የሆነ ጉብኝት ለማድረግ ትላንት ሞቃዲሾ የነበሩት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይስ አፈወርቄ ዛሬ ኬንያ ናይሮቢ ገብተዋል። ወደስልጣን ከወጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶማሊያን የጎበኙት አቶ ኢሳያስ አፈወርቄ፣ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሚስተር መሃመድ አብዱላሂ ጋርበሁለቱ ሃገራትና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተመልክቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የአልሻባብ ኮማንደር የነበረውና ከአልሻባብ የከዳው ሙክታር ሮቦው በሶማሊያ ...
Read More »ቱባቱባ የቀድሞ ባለስልጣናትን ወደ አንድ ቦታ መሰብሰብ ይገባል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 05/2011) በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ስርዓት አልበኝነት መልክ ለማስያዝ ቱባቱባ የቀድሞ ባለስልጣናቱን ወደ አንድ ቦታ መሰብሰብ እንደሚገባ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አሳሰቡ። የትግራይ ህዝብም በውስጡ የበቀሉትንአረሞች እየሰማ የነርሱ መሸሸጊያ ሊሆን አይገባም ያሉት ፕሮፌሰርር መስፍን ወልደማርያም ሌላውም ህዝብ የትግራይን ህዝብ ከህዉሃትለይቶ እንዲመለከት ጥሪ አቅርበዋል። እነ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚሰብኩት ፍቅር፣ ሰላምና ይቅር ባይነት በህጋዊ ሰይፍ ካልታገዙ እነሱንም ሆነ ህዝቡን ወደ ...
Read More »ማንነትን ማክበርና ማስከበር የልዩነት ግንብን መገንባት አይደለም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ /2011) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ማንነትን ማክበርና ማስከበር አጥር ማጠርና የልዩነት ግንብ መገንባት አይደለም ሲሉ ገለጹ። በጎንደር በተካሄደውና በአማራና ቅማንት ማህበረሰብ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሚመክረው መድረክ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት መሪዎች ከማለፋቸው በፊትየማያልፍ ጠባሳ ለትወልዱ ጥለው እንዳያልፉ ሊጠነቀቁ ይገባል። አቶ ደመቀ መኮንን እንዳሉት ማንነትን ማክበርና ማስከበር አጥር ማጠርና የልዩነት ግንብ መገንባት አይደለም ። ህዝብን ማድመጥና ታሪካዊ ...
Read More »