Author Archives: Central

በህገወጥ የሰዎች ማዘዋወር ወንጀል የተጠረጠረ የአንድ ኢትዮጵያዊ በማልታ መታየት ጀመረ

ኢሳት (ጥር 2 ፥ 2009) በህገወጥ የሰዎች ማዘዋወር ወንጀል የተጠረጠረ የአንድ ኢትዮጵያዊ የፍርድ ሂደት በማልታ መታየት መጀመሩን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። ሰኞ በሃገሪቱ በሚገኝ አንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩ መታየት የጀመረው የ58 አመቱ ሃዱሽ አባይ ከ11 አመት በፊት 181 አፍሪካዊ ስደተኞችን ወደ ማልታ በተደራጀ የህገወጥ ድርጊት ማጓጓዙን በግለሰቡ ላይ የተመሰረተ ክስ አመልክቷል። አቶ ሃዲሽ በጉዳዩ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ...

Read More »

በፖሊስ ምርመራ ላይ የሚገኙትን ዶ/ር መረራ ጉዲናን በነጻ የማሰናበት ፍላጎት እንደሌለው ሃይለማሪያም ደሳለኝ ገለጹ

ኢሳት (ጥር 2 ፥ 2009) መንግስት ጉዳያቸው በፖሊስ ምርመራ ላይ የሚገኙትን ዶ/ር መረራ ጉዲና በነጻ የማሰናበት ፍላጎት እንደሌለው ገለጸ። በወቅታዊ የሃገሪቱ አበይት ጉዳዮች ዙሪያ ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መግለጫን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ዶ/ር መረራ እንደማይለቀቁ መናገራቸውን ለአሶሼይትድ ፕሬስ ዘግቧል። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራሩ ይልቁኑ ለፍትህ ይቀርባሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በቅርቡ ከአውሮፓ የፓርላማ አባላት ጋር ለመወያየት ወደ ...

Read More »

በቱርክ በሽብርተኝነት የተፈረጀው ተቋም በኢትዮጵያ ያቋቋማቸው ት/ቤቶች ለቱርክ መንግስት ተላልፈው እንዲሰጡ ጥያቄ ቀረበ

ኢሳት (ጥር 2 ፥ 2009) ቱርክ በሽብርተኛ ድርጅት የፈረጀችው አንድ ተቋም (ድርጅት) በኢትዮጵያ ያቋቋማቸው ትምህርት ቤቶች ለቱርክ መንግስት ተላልፈው እንዲሰጡ ሃገሪቱ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች። የቱርክ ባለስልጣናት በዚሁ በአሜሪካን በጥገኘት የሚገኙትን የተቋማት ፓርቲ አመራር ፋቱላህ ጉለንን እንዲሁም ያቋቋማቸው በርካታ ድርጅቶችን በሽብርተኛ ተቋም በመፈረጅ የተቃዋሚ አመራሩን ለፍርድ እንደምትፈልጋቸው ስትገልፅ  መቆየቷ ይታወሳል። የጉለን ንቅናቄ ተብሎ በሚጠራው በዚሁ ድርጅት የተቋቋሙ ስድስት ትምህርት ቤቶች ክጥቂት ...

Read More »

በጂጂጋ የተደረገው የጦር አዛዦች ስብሰባ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሚደረገው ዘመቻ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውሳኔ አሳለፈ

ጥር ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት በጂጂጋ ከተማ በተደረገው  የከፍተኛ የጦር አዛዦች ስብሰባ ላይ በሰሜን ጎንደር የሚደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ውሳኔዎችን አሳልፏል። የምእራብ እዝ ማሰልጠኛ ሰሜን ጎንደር በሚገኘው ሰራባ በሚባለው ቦታ ላይ እንዲሆን የመጨረሻ ውሳኔ  በደቡብ ምስራቅ እዝ በ13ኛ እና 32ኛ ክፍለ ጦሮች ስር የሚገኙ ሁለት ሬጀመንት ጦር ወደ ሰሜን ጎንደር በማምጣት፣ ሰሜን ጎንደርን ...

Read More »

በአማራና ኦሮምያ ክልሎች አዲስ የእስር ዘመቻ ተከፈተ

ጥር ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በሳምንቱ መጨረሻ በኦሮምያ በተለይም በአዳማ ፣ ጉጂ እና ቦረና ዞኖች፣ በአማራ ክልል ደግሞ በጎንደር እና አዊ ዞኖች በርካታ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። 10 ሺ ወጣቶች ከእስር መፈታታቸውን ባስታወቀ ሁለት ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ አዲስ የተጀመረው የእስር ዜና በነዋሪዎች ላይ ጫና እየፈጠረ ነው። በአማራ ክልል በተለይ ከወራት በፊት ተደርጎ በነበረው ህዝባዊ ...

Read More »

በአዳማ እና አካባቢው የውሃ እጥረቱ ተባብሶ ቀጠለ

ጥር ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዳማ ወረዳ አካባቢዎች የውሃ እጥረቱ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ነዋሪዎቹ ለከፍተኛ ወጪና እንግልት ተዳርገዋል። በተለይ በአዳማ ናዝሬት ከተማ ውስጥ ያሉት የውሃ መስመሮች በአብዛሃኛው አገልግሎት አይሰጡም። ከዓመት በአል ዋዜማ ቀናት ጀምሮ ከተማ እና በአጎራባች ቀበሌዎች ውሃ ለማግኘት ረዥም ሰዓታት ወረፋ ለመያዝ ተገደዋል። የከተማዋ አስተዳደር ለውሃ ችግሩ እልባት ከመስጠት ይልቅ አሁንም በአዳዲስ የሹም ሽር ሹመት ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከተማ ከንግድ ይዞታቸው የተፈናቀሉ ነጋዴዎች ለከፍተኛ ስቃይ ተዳረጉ

ጥር ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በልማት ስም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለዘመናት ሃብት አፍርተው በንግድ ስራ ላይ ይተዳደሩበት ከነበሩት ይዞታቸው የተፈናቀሉ ነጋዴዎች ለሶስት ዓመታት በስቃይ ላይ መሆናቸውን አስታወቁ። ነጋዴዎቹ ቤተሰባቸውን ከሚያስተዳድሩበት ይዞታቸው ተነስተው በምትኩ ተለዋጭ ቦታ ይሰጣችኋል ቢባሉም እስካሁን ድረስ መስተዳድሩ የገባላቸውን ቃል አላከበረም። ቁጥራቸው ከአንድ ሺሕ በላይ የሚሆኑት እነዚህ ነጋዴዎች ከአስር በላይ የአክሲዮን ማኅበራትን መስረተው ተደራጅተው ...

Read More »

የውጭ አገር ምንዛሪ እጥረትን ተከትሎ የባህረ-ሰላጤ ሃገራት ገንዘባቸውን በኢትዮጵያ እንዲያስቀምጡ በመደረግ ላይ ነው ተባለ

ኢሳት (ጥር 1 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ የባህረ-ሰላጤ ሃገራት ገንዘባቸውን በኢትዮጵያ እንዲያስቀምጡ በመደረግ ላይ መሆኑን መንግስት ሰኞ ይፋ አደረገ። በወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ ለሃገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን መግለጫን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ ሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ውስጥ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ላለፉት ሶስት አመታት የውጭ ምንዛሪ ግኝቷ የቀነሰው የምትልካቸው የግብርና ምርቶች ...

Read More »

ሱዳንን መሸጋገሪያ በማድረግ ከኢትዮጵያ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 1 ፥ 2009) የሱዳን ባለስልጣናት ሃገሪቱ መሸጋገሪያ በማድረግ ከኢትዮጵያ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ስጋት እንዳሳደረባቸው ገለጹ። የስደተኞች ዝውውርን ለመቆጣጠር የተቋቋመው የፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ አገልግሎት ሃላፊ የሆኑት መሃመድ ሃምዳን ባለፉት ሰባት ወራቶች ብቻ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ 1ሺ 500 ስደተኞች በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ለሱዳን መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። ከኢትዮጵያ የሚሰደዱ ሰዎች ሱዳንን ለመሸጋገሪያነት በመጠቀም ወደ ግብፅ፣ ሊቢያ እና ...

Read More »

የብሪታኒያ መንግስት ለትምህርታዊ ፕሮግራሞች ሊሰጥ የነበረውን ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ አገደ

  ኢሳት (ጥር 1 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ለሚተላለፉ ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ሊሰጥ የነበረውን ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ አገደ። የሃገሪቱ አለም አቀፍ የልማት ትብብር ባለፈው ወር “የእኛ” የሚል መጠሪያ ላላቸው ቡድኖች የ5.2 ሚሊዮን ፓውንድ (ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ) ድጋፍ ለማድረግ ውሳኔን አስተላልፎ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል። ይሁንና፣ ድርጅቱ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የብሪታኒያ የፓርላማ አባላት እንዲሁም የመገናኛ ተቋማት ገንዘቡ ...

Read More »