ኢሳት ( መጋቢት 27 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለፈው አመት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ደርሶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ያስነሱት በወንጀል ተጠርጥረው የፍርድ ሂደትን የሚጠባበቁ እስረኞች ናቸው ሲል ለፓርላማ ገለጸ። በአጀንዳው ዙሪያ ያካሄደው ጥናት አስመልክቶ ለፓርላማው ሪፖርቱን ረቡዕ ያቀረበው መንግስታዊው ኮሚሽን ከዚሁ በፊት ከሳሽ አቃቤ ህግ እስረኞቹን ተጠያቂ ያደረገበት ሂደት በተመሳሳይ ሁኔታ አቅርቧል። ባለፈው አመት ነሃሴ ወር በእስር ቤቱ ...
Read More »Author Archives: Central
ሱዳንና ኢትዮጵያ በፖለቲካና ወታደራዊ ዘርፎች ትስስር ለመመስረት የሚያስችል አዲስ ስምምነት መድረሳቸው ተነገረ
ኢሳት ( መጋቢት 27 ፥ 2009) የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ሃገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በፖለቲካና በወታደራዊ ዘርፎች ትስስር ለመመስረት የሚያስችል አዲስ ስምምነት መደረሱን አስታወቁ። ለሶስት ቀን ጉብኝት ማክሰኞ አዲስ አበባ የገቡት ፕሬዚደንት አል-በሽር የኢትዮጵያ ደህንነት እና ፀጥታ ከሱዳን ተለይቶ አይታይም ሲሉ ለጋዜጠኞች መግለጻቸውን ሱዳን ትሪቢዮን ጋዜጣ ዘግቧል። ካለፈው አመት ጀምሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሁለትዮሽ ስምምነት የደረሱት ሁለቱ ሃገሮች የፖሊስ የደህንነትና የሰራዊት ...
Read More »በኢትዮጵያ የምግብ ዋጋ ንረት ወደ 8.7 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገለጸ
ኢሳት ( መጋቢት 27 ፥ 2009) አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በማሻቀብ ላይ ያለን የምግብ ዋጋ ንረት ተከትሎ የመጋቢት ወር የዋጋ ግሽበት ከሰባት በመቶ ወደ 8.5 በመቶ ከፍ ማለቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። የወተት ተዋጽዖን ጨምሮ በስጋና በመሰረታዊ የምግብ ሸቀጣሸቀጦች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መመዝገቡን የገለጸው ኤጀንሲው በተለይ የምግብ ዋጋ ባለፈው ወር ከነበረበት የ7.8 ወደ 9.6 በመቶ ሊያድግ መቻሉን መንግስታዊ ...
Read More »በዋልድባ ገዳም አቅራቢያ በአማራና በትግራይ ሚሊሺያዎች መካከል የተጀመረው ግጭት መቀጠሉ ተገለጸ
ኢሳት ( መጋቢት 27 ፥ 2009) በዋልድባ ገዳም አቅራቢያ በአማራና በትግራይ ሚሊሺያዎች መካከል ትናንት የተጀመረው ግጭት መቀጠሉን የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ለንግስ አምበርታት ገዳም የነበሩ ምዕመናን በግጭቱ ከጉዟቸው መገታታቸው ታውቋል። በዋልድባ አምበርታት ገዳም መጋቢት 27 ፥ 2009 በሚከበረው የመድሃኒያለም ክብረ በዓል ላይ ለመገኘት ይጓዙ የነበሩ የአማራ ክልል ሚሊሺያዎች ትጥቃቸው እንዲፈቱ በመጠየቃቸው ማክሰኞ ዕለት በተጀመረው ግጭት ከሁለቱ ወገን 6 ሚሊሺያዎች ተገድለዋል። ...
Read More »በአዲስ አበባ የሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናት ለአባይ ግድብ እያንዳንዳቸው 50ሺህ ብር፣ ካህናትም የአንድ ወር ደሞዛቸው እንዲያዋጡ በድጋሚ ታዘዙ
ኢሳት ( መጋቢት 27 ፥ 2009) ለአባይ ግድብ ግንባታ በአዲስ አበባ የሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናት እያንዳንዳቸው 50ሺህ ብር እንዲያዋጡ በድጋሚ ታዘዙ። በአብያተ-ክርስቲያናቱ የሚያገለግሉ ካህናትም የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለግድቡ ግንባታ እንዲሰጡ ተወስኗል። በጠቅላይ ቤተክህነት የሚገኙ የእሳት ምንጮች እንደገለጹት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 90 ያህል አብያተ-ክርስቲያናት እያንዳንዳቸው የሚያዋጡት 50ሺህ ብር እንዲሁም የካህናቱ የአንድ ወር ደሞዝ በጠቅላይ ቤተ-ክህነት በኩል ለህዳሴው ግድብ ብሄራዊ ምክር ቤት ገቢ ...
Read More »የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር ስም እየተራቆተ መሆኑ ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 26 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ ሃገሪቱ ልማት ባንክ በብድር ስም እየተራቆተ መሆኑን ምንጮች ገለጹ። ለባንኩ ፕሬዚደንት በጉቦ መልክ እጅግ ዘመናዊ ቤት የተሰራላቸው ቢሆንም፣ እርሳቸው የሚኖሩበት ግን ባንኩ በዋስትና በወረሰው ቤት ውስጥ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የህወሃት ንብረት ለሆነው ኤፈርት ኩባንያዎች ብድር ምንጭነት በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት፣ ከገዢው ፓርቲ ጋር ቅርበት ያላቸው ባለሃብቶችም ...
Read More »በኢትዮጵያ አህዮች እንዲታረዱ መደረጉ ተቃውሞ ሊቀሰቀስ ይችላል ተባለ
ኢሳት (መጋቢት 26 ፥ 2009) በኢትዮጵያ አህዮች እንዲታረዱና ስጋና ቆዳቸው ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ መወሰኑ በኢትዮጵያውያን ዘንድ እያነጋገረ ሲሆን፣ በአፍሪካዊቷ ቡርኪናፋሶም ያስከተለው ቁጣ በኢትዮጵያ ሊደገም እንደሚችል የፖለቲካ ተመልካቾች ይገልጻሉ። በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ድርጊቱ ተቃውሞና ቁጣ ማስከተሉን ማስታወስ ተችሏል። መንግስት ከእንግዲህ ፈቃድ አልሰጥም ያለ ቢሆንም፣ ከዚህ በፊት የሰጠውን ግን አልሰረዘም። የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በበኩሉ ለውጭ ገበያ ይቀርባል ተብሎ የታሰበው የአህያ ስጋ ...
Read More »በሶማሊያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከይዞታቸው ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 26 ፥ 2009) በሶማሊያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከተጨማሪ ወታደራዊ ይዞታዎች ለቀው መውታጣቸውን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። ቁጥራቸው ያልተገለጸው ወታደሮቹ በማዕከላዊ ሶማሊያ ከሚገኘውና ኤልቡር ተብሎ ከሚጠራ አስተዳደር ለቆ መውጣቱን የአካባቢው የክልል ባለስልጣናት ለመገናኛ ብዙሃን አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች ለረጅም ጊዜ ተቆጣጥረው ከቆዩት አስተዳደር በምን ምክንያት ለቀው እንደወጡ የታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን፣ የሶማሊያው ታጣቂ ሃይል አልሸባብ ኤልቡርን እንደተቆጣጠረ ቪኦኤ የእንግሊዝኛው ክፍል ዘግቧል። ...
Read More »የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከግብፅ ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ ገለጹ
ኢሳት (መጋቢት 26 ፥ 2009) የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በሽብርተኛ ላይ እየተደረገ ያለውን ዘመቻ ለማጠናከር ከግብፅ ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ ሰኞ ይፋ አድርገዋል። ከቀድሞው የግብፅ ፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባራክ ከስልጣን መወገድ በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በ White House የተጋበዙት ፕሬዚደንት አብደል ፈታህ አልሲሲ በበኩላቸው ፕሬዚደንት ትራምፕ በጸረ-ሽብርተኛ ላይ የያዙትን አቋም እንደሚያደንቁና ተባብረው እንደሚሰሩ ምክክር መካሄዱን ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። ሁለቱ መሪዎች ለሰዓታት በዝግ ባካሄዱት ...
Read More »በዋልድባ ገዳም አቅራቢያ በአማራና በትግራይ ሚሊሺያዎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከተሎ ከሁለቱም ወገን የሰው ህይወት ጠፋ
ኢሳት (መጋቢት 26 ፥ 2009) በዋልድባ ገዳም አቅራቢያ በአማራና በትግራይ ሚሊሺያዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ከሁለቱም ወገን ታጣቂዎች ተገደሉ። ማክሰኞ መጋቢት 26, 2009 አም ለተቀሰቀሰው ግጭት መነሻ የሆነው በዋልድባ ገዳም ለሚከበረው አመታዊ የመድሃኒያለም በዓል የሚጓዙ የአማራ ሚሊሺያዎች ትጥቅ እንዲፈቱ በመጠየቃቸው እንደሆነም መረዳት ተችሏል። በታሪካዊው ዋልድባ አበረንታት ገዳም መጋቢት 27 ለሚከበረው አመታዊ የመድሃኒያለም የንግስ በዓል በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ከዋዜማ ቀናት ጀምሮ ወደገዳሙ ...
Read More »