Author Archives: Central

አራተኛው የህዝብ ቆጠራ ህዳር ወር ላይ ይካሄዳል ተባለ

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሕዝብ ቆጠራ ኮምሽን በመጪው ዓመት ህዳር 10 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ አራተኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ እንደሚያካሂድ የኮምሽኑ ምንጮች ገለጹ። የሕዝብና ቤት ቆጠራ በ10 ዓመት አንድ ጊዜ የሚከናወን ሲሆን ኮምሽኑ በ1999/2000 ዓ.ም ያካሄደው ሶስተኛው ቆጠራ የብአዴን/ኢህአዴግ የፓርላማ አባላትን ጭምሮ በርካታ ዜጎችን ያስቆጣ ነበር። ኮምሽኑ ህዳር 25 ቀን 2001 ዓ.ም 3ኛውን የሕዝብና ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የዓለማቀፉ ፕሬስ ኢንስቲትዩት የ2017 የፕሬስ ጀግኖች ሽልማት አሸናፊ ሆነ።

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓለማቀፉ የፕሬስ ኢንስቲትዩት በምህጻረ ቃሉ- አይ ፒ አይ ይፋ እንዳደረገው፤69ኛውን የዓላማችን የፕሬስ ጀግኖች ሽልማት ፣ ፕሬስን ለማፈን የወጣውን የጸረ ሽብርተኝነት ህጉን በመተቸቱ ምክንያት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2011 ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛና ጦማሪ እስክንድር ነጋ አሸንፏል። አይ ፒ አይ ዛሬ ባወጣው በዚሁ መግለጫ የአፍጋኒስታን ጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ የነጻ ሚዲያ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ድርቅ ተከትሎ 16 ሺ ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መጠቃታቸው ተዘገበ

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኘው ዶሎ ዞን በ30 አመት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ድርቅ ምክያት በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ 16 ሺ ሰዎች መያዛቸውንና በየወሩም ከ3 ሺ 500 በላይ ሰዎች ወደ ህክምና ማእከል እንደሚገቡ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታውቋል። እንደ ድርጅቱ ዘገባ ከሆነ ወረርሽኙን ለመከላከል 1ሺ 200 ባለሞያዎች በ100 ጣቢያዎች አገልግሎት ለመስጠት ቢሞክሩም፣ ባካባቢው የመሰረተ ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአምቦ ከተማና አካባቢዋ ውጥረት ማንገሱ ተዘገበ

ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ለተጨማሪ ወራቶች ተራዝሞ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአምቦ ከተማና አካባቢዋ ውጥረት ማንገሱን ዘ-ኢኮኖሚስት መጽሄት ዘገበ። በሃገሪቱ ወቅታዊ ጸጥታ ዙሪያ ሰኞ ሪፖርትን ይዞ የወጣው አለም አቀፍ መጽሄቱ በከተማዋ የሚገኘው የአምቦ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ወታደራዊ ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስነብቧል። ባለፈው አመት በአምቦ ከተማና ዙሪያዋ በሚገኙ የገጠር መንደሮች ሲካሄድ ከቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በርካታ ሰዎች ...

Read More »

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪን ኮርፖሬሽን ለአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡሶችን ለማቅረብ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ኮንትራት ተረከበ

ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2009) የመንግስት የልማት ፕሮጄክቶችን ያለ ግልጽ ጨረታ በመረከብ ላይ የሚገኘው የብረታ ብረትትና ኢንጂነሪን  ኮርፖሬሽን ለአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡሶችን ለማቅረብ ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ኮንትራት ተረከበ። የህወሃት ጄኔራሎች የሚመሩት ኮርፖሬሽኑ 750 አውቶቡሶችን ለማቅረብ ከከተማው አስተዳደር ጋር የኮንትራት ስምምነት መድረሱን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የአዲስ አበባ መንገዶችና ትራንስፖርት ቢሮ በቀጣዩ ሳምንት ከኮርፖሬሽኑ ጋር የ3.5 ቢሊዮን ብር ስምምነት ...

Read More »

በሶማሌ ክልል የተከሰተውን ኮሌራ በቁጥር ስር ለማዋል የውጭ ሃገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ

ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ለሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን የኮሌራ በሽታ ስርጭት (ወረርሽኝ) በቁጥር ስር ለማዋል የውጭ ሃገራት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የፈረንሳዩ አለም አቀፍ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ግብረ ሰናይ ድርጅት ጥሪውን አቀረበ። በክልሉ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት በመደገፍ ላይ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ፣ ከ16 ሺ በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ይፋ አድርጓል። የፌዴራልና የክልሉ ባለስልጣት በበሽታው ስርጭት ሳቢያ በሰዎች ...

Read More »

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለግል ባለሃብቶች የሚሰጠውን የኢንቨስትመንት ብድር አቋረጠ

ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያወጣውን አዲስ መመሪያ ተከትሎ ንግድ ባንክ ለረጅም አመታት ለግል ባለሃብቶች ሲሰጥ የቆየውን ብድር ከሚያዚያ 2 ፥ 2009 አም ጀምሮ ማቋረጡን ካፒታል የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል። ብሄራዊ ባንክ ከንግድ ባንክ ብድር እንዳያገኙ የተደረጉ ባለሃብቶች ጥያቄያቸውን ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ በማቅረብ እንዲያስተናግዱ ትዕዛዝ መስጠቱ ታውቋል። በዚሁ የብሄራዊ ባንክ አዲስ መመሪያ መሰረት የብድር ጥያቄን አቅርበው ውሳኔን በመጠባበቅ ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የአለማችን የፕሬስ ነጻነት ጀግና በሚል ተመረጠ

ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2009) መቀመጫውን በኦስትሪያ ቬይና ያደረገው አለም አቀፍ የፕሬስ ኢንስቲትዩት ከአለም አቀፉ የሚዲያ ድጋፍ (IMS) ጋር በጋራ እስክንድር ነጋ የአለማችን የ2017 የፕሬስ ነጻነት ጀግና በሚል ሰይመውታል። አለም አቀፉ የፕሬስ ኢንስቲትዩት ማክሰኞ ኤፕሬል 25, 2017 ከአውስሪያ መዲና ቬይና ባወጣው መግለጫ፣ ሃሳብን ለመግለፅ ነጻነት ወደር የሌለው ፅናትን ለሚያሳዩ የአለማችን ጋዜጠኞች የሚሰጠው ይኸው ሽልማት ለ2017 እስክንድር ነጋ መመረጡን አስታውቋል። ላለፉት ...

Read More »

አሜሪካ አልሸባብ ላይ ልታካሄድ ባቀደቸው አዲስ ወታደራዊ ጥቃት ዙሪያ ላይ ለመምከር የመከላከያ ሚኒስትሯ ወደጅቡቲ ላከች

ኢሳት (ሚያዚያ 16 ፥ 2009) የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ሃገራቸው በሶማሊያ ታጣቂ ሃይል አልሸባብ ላይ ልታካሄድ ባቀደቸው አዲስ ወታደራዊ ጥቃት ዙሪያ ላይ ለመምከር ትላንት ዕሁድ በጅቡቲ ጉብኝት አደረጉ። የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር በአል-ሸባብ ታጣቂ ሃይል ላይ አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲያካሄድ በሃገሪቱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ ትዕዛዝ ከተሰጠው በኋላ የመከላከያ ሚኒስትሩ በጅቡቲ ጉብኝት ሲያደርጉ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ታውቋል። የመከላከያ ሚኒስትሩ ማቲስ ...

Read More »

የአቶ አሰፋ ጫቦ የቀብር ስነ-ስርዓት በኢትዮጵያ እንደሚፈጸም ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 16 ፥ 2009) ታዋቂው ጸሃፊ፣ የህግ ባለሙያና የቀድሞ የፓርላማ አባል የአቶ አሰፋ ጫቦ የቀብር ስነስርዓት በትውልድ ሃገራቸው ኢትዮጵያ እንደሚፈጸም ተገለጸ። አስከሬኑን ወደ ኢትዮጵያ ለመሸኘትም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። እሁድ ሚያዚያ 15 ፥ 2009 በዬስ አሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ዳላስ ከተማ ህይወታቸው ያለፈው አቶ አሰፋ ጫቦ፣ ከ73 አመታት በፊት በደቡብ ኢትዮጵያ በጋሞጎፋ ጨንቻ ከተማ መወለዳቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል። የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ...

Read More »