Author Archives: Central

ከአውስኮድ ክለብ ጋር ባህርዳር ላይ የእግር ኳስ ግጥሚያ ማድረግ የነበረበት የመቀሌ ቡድን በጸጥታ ምክንያት ጨዋታውን ሰረዘ

ኢሳት (ሰኔ 13 ፥ 2009) ከአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት /አውስ ኮድ / ክለብ ጋር የእግር ኳስ ውድድር ለማካሄድ ባህር ዳር መግባት የነበረበት የመቀሌው ከነማ ቡድን በጸጥታ ስጋት ምክንያት ጨዋታውን መሰረዙ ተሰማ ። የመቀሌው እግር ኳስ ክለብ ከአማራ ስፖርት ኮሚሽንና ከክልሉ መንግስት የጸጥታ ዋስትና እንዲሰጠው ጠይቆ የጽሁፍ ደብዳቤ ባለማግኘቱ በጸጥታ ስጋት ጨዋታውን መሰረዙ ታውቋል።   በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደራል ህግና ...

Read More »

በአዲስ አበባ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የቀን ገቢ ግምት አሰራር አድሎአዊ እንደነበረ ተገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 13 ፥ 2009) የአዲስ አበባ አስተዳደር የገቢዎች ኤጀንሲ በግንቦት 30 ቀን 2009 አ ም እንዳጠናቀቀ ይፋ ያደረገው የቀን ገቢ ግምት የስነ-ምግባር ችግር ያለበት በሙስና በዘመድ አዝማድና የፖለቲካ አባልነት ምክንያት አድሎአዊ አሠራር የተከተለ መሆኑን የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ። ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባላስልጣና የአዲስ አበባ ከተማ ታክስ ፕሮግራም ዘርፍ በቀን ገቢ መረጃ አሰባሰብ ሂደት ላይ ከነጋዴ ተወካዮችና የነዋሪዎች ...

Read More »

የተምች ወረርሽን በ6 የኢትዮጵያ ክልሎች ተከሰተ

  ኢሳት (ሰኔ 13 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ የተረጂዎች ቁትር ከ5.6 ሚሊዮን ወደ 7.8 ሚሊዮን በተሻገረበት ወቅት በ6 የሀገሪቱ ክልሎች የተምች ወረርሽን መከሰቱ ተገለፀ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳስታወቀው በ35 ዞን 233 ወረዳዎች ችግሩ ተከስቷል።  የተባበሩት መንግስታት የሠብዓዊ ዕርዳት ማስተባበሪያ ቢሮ ወረርሽኙን በቅድሚያ የተከሰተው በደቡብ ክልል ሻላ ዞን የኪ ወረዳ ቢሆንም አሁን በ6 ክልሎች ተጨማሪ 232 ወረዳዎችን አጥቅቷል። ወረዳዎቹ የችግሩ ...

Read More »

በባህርዳር ማረሚያ ቤት በርካታ ወታደራዊ አዛዦች መታሰራቸውን ምንጮች ገለጹ

ሰኔ ፲፫( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ የተደረገውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ በመከላከያ ውስጥ በተደረገው የ “ ጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ” ሰበብ ከ50 ያላነሱ እስከ ኮሎኔልነት የሚደርስ ወታደራዊ ማእረግ ያላቸውና ተራ ወታደሮችና ለስርዓቱም ታማኞች አይደሉም በሚል ታስረው እንደሚገኙ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። እስረኞቹ ጃዊ ውስጥ በሚገኝ የመከላከያ ካምፕ ውስጥ ለወራት ታስረው ከቆዩ በሁዋላ፣ በአማራነታቸው ብቻ ተገምግመው መታሰራቸውን ...

Read More »

አቃቤ ሕግ ዶ/ር መረራ ጉዲና ለሁለተኛ ጊዜ ላቀረቡት አቤቱታ መልስ ሰጠ

ሰኔ ፲፫( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ወር የዶ/ር መረራ ጉዲና ጠበቃ በዶ/ር መረራ ላይ የቀረበው ክስ ከኢሳት እና ኦኤምኤን ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ክስ ጋር ተለይቶ እንዲታይ ጠይቆ ነበር። አቃቢ ህግ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን አስተያየት በጽሁፍ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም በጉዳዩ ላይ ለመወሰን ለሰኔ 30 ቀን 2009 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚታየው የዘይት እጥረት እንደቀጠለ ነው

ሰኔ ፲፫( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 11 በመቶ እድገት መገኘቱ በየጊዜው በሚነገርባት ኢትዮጵያ የዘይትና የስኳር እጥረት ለአመታት ዋና ተፈላጊ የምግብ ሸቀጦች ሆነው ቀጥለዋል። በዋና ከተማዋ ዜጎች ዘይት ለማግኘት ሌለቱን በሰልፍ ያሳልፋሉ። ዘይት አከፋፋይ ድርጅቶች ዜጎች በሌሊት እንዳይሰለፉ ማስታወቂያዎችን እስከመለጠፍ ቢደርሱም፣ ወረፋው አልቀነሰም። አንድነት የሸማቾች ማህበር ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓም ባወጣው ማስታወቂያ “ አገልግሎት የሚሰጡ ...

Read More »

የአርበኞች ግንቦት7 አባላት አንድ ኮማንደርን ጨምሮ በርካታ ወታደሮችን መግደላቸውን ገለጹ

ሰኔ ፲፪( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጅቱ ለኢሳት በለካው መረጃ የአርበኞች ግንቦት7 ልዩ ኮማንዶ በእብናት ከተማ ወታደራዊ ጊዚያዊ ጣቢያ ላይ ሰፍሮ በሚገኙ ወታደሮች ላይ በወሰዱት ጥቃት የጦሩ አዛዥ የሆነውን ኮማንደር አወቀን ጨምሮ በርካታ ወታደሮችን መግደላቸውን አስታውቀዋል። ኮማንደሩ በከፍተኛ ወታደራዊ አጀብ ወታደራዊ አመራሮች፣ የክልል ባለስልጣናት፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት አርማጭሆ ላይ መቀበሩን የገለጸው ድርጅቱ፣ አዛዡ አስቀድሞ ...

Read More »

በጣና ሃይቅ ዳርቻ በሚገኙ ከተሞች የመሬት ቅርምቱ ጨምሯል

ሰኔ ፲፪( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣቶች በተወለድንበት ምድር ነጻነት አጥተናል ይላሉ በጣና ሃይቅ ዳርቻ በሚገኙ በጎርጎራ ፣ቁንዝላና ባህርዳር ከተሞች ዙሪያ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደተናጉሩት “ የጣና ሃይቅ አካባቢ በልማት ስም ተሸንሽኖ በመሰጠቱና ለአመታት ያለምንም ስራ ታጥረው በመቀመጣቸው ህዝቡ እየተቸገረ ነው። በጎርጎራና ዙሪያዋ ለ23 ዓመታት ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች አሉ። አርሶአደሮች የእርሻ መሬት አጥተው በችግር ላይ ናቸው። ...

Read More »

የኮልፌ ቀራኒዮ ነዋሪዎች ጥያቄያቸውን እንዳያቀርቡ ታገዱ

ሰኔ ፲፪( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ በኮልፈ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ካራ ቆሬ/ ሬጲ አካባቢ ሰኔ 03 ቀን 2009 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ በከፍተኛ ቃጠሎ የጋየውን የሮያል ስፖንጅ ፋብሪካ ተከትሎ እሁድ ሰኔ 4/09 ከ 1200 በላይ ነዋሪዎችን የሚወክሉ 205 የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ለ3 ሠዓታት ያክል ተሰብስበው ፋብሪካው በህብረተሰቡ ላይ ያደረሰውን ጉዳት በዝርዝር በመጻፍ ለመስተዳድር ባለስልጣናት ...

Read More »

በምስራቅ ኢትዮጵያ ጥንታዊ የንግድ ማዕከል ተገኘ

ሰኔ 9 ፥ 2009 በምስራቅ ኢትዮጵያ ሃርላ በሚባል አካባቢ በመሰማራት ቁፋሮ ሲያደርጉ የነበሩ የስነ ምድር ተመራማሪዎች ከክርስቶስ ልደት በፊት በ10ኛው ክፍለ ዘመን የንግድ ማዕከል የነበረ አንድ ከተማ ማግኘታቸውን ገለጹ። ከግብጽ፣ ከህንድና፣ ከቻይና ወደ ከተማው የገቡ  የተለያዩ ቁሳቁሶችም መገኘታቸው ተገልጿል። ከማዳጋስካር፣ ከማልዲቭስ እና ከየመን ጭምር የመጡ የተለያዩ ጌጣጌቶች በአካባቢው ተቀብረው መገኘታቸው ቢቢሲ በድረገጹ አስነብቧል።  ከዚህ በተጨማሪ የስነ-ምድር ተመራማሪዎች በ12ኛው ክ/ዘመን የተገነባ ...

Read More »