(ኢሳት ዲሲ–ጥር 11/2010) ኢትዮጵያውያን የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ ባለመላክ የሕወሃትን አገዛዝ ለማዳከም የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን የሚያሳይ ጥሪ ተላለፈ። አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረ ሃይል ለኢትዮጵያውያን ያስተላለፈው ጥሪ 3 መንገዶችን በመጠቀም የሕወሃትን አገዛዝ ማዳከም እንደሚቻል አመላክቷል። አንደኛው ዌስተርን ዩኒየንና መኒግራምን ከመጠቀም ይልቅ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም የሚል ነው። በ2ኛ ደረጃ ደግሞ ሌሎች አማራጮች ካልተገኙና በባንክ በኩል መላክ የግድ ከሆነ የሚላከውን ገንዘብ መጠን ...
Read More »Author Archives: Central
ኢትዮጵያና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ ሃይል ለማስፈር ተስማሙ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 11/2010) ኢትዮጵያና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ ሃይል በድንበሮቻቸው አካባቢ ለማስፈር ተስማሙ። ሁለቱ ሀገራት የጋራ ወታደሮቻቸውን የሚያሰፍሩት የአባይ ግድብ በሚገኝበት የቤንሻንጉል ክልልና በሱዳን የብሉናይል ግዛት ድንበሮች አቅራቢያ ነው። በሱዳኑ የብሉናይል ግዛት ዋና ከተማ ዳማ ዚን የተፈረመው ስምምነት የተካሄደው በአፍሪካ ቀንድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከሰተ ያለውን ውጥረት ተከትሎ መሆኑ ታውቋል። በአፍሪካ ቀንድ ባሉ ሀገራት ከወትሮው የተለየ ውጥረት መንገሱ ይነገራል። ምክንያቱ ደግሞ ...
Read More »የሳሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ውዝግብ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 11/2010) በአዲስ አበባ ሳሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የተፈጠረው ውዝግብ እንደቀጠለ መሆኑ ተሰማ። ትላንት በጥምቀት በዓል ዋዜማ በአካባቢው የተኩስ እሩምታ እንደነበረ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የፌደራል ፖሊስ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮችን በጅምላ በማፈስ ካሰረ በኋላ በህዝብ ተቃውሞ መፈታታቸው ታውቋል። የቤተክርስቲያኒቱን ሀብትና ንብረት ከዘረፋ ለመታደግ ህዝቡ የጀመረውን ትግል ለማስቆም በህወሃት አገዛዝና በፓትርያርኩ የሃይል ርምጃ መወሰዱ ውጥረቱን እንዳባባሰው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የውዝግቡ መነሻ ...
Read More »ወታደራዊ ምልመላ ተጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 11/2010) የመከላከያ ሚኒስቴር በመላ ኢትዮጵያ ወታደራዊ ምልመላ ጀመረ። በክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ ጭምር የተጀመረው ወታደራዊ ምልመላ አላማ ምን እንደሆነ ግን አልታወቀም። ይህ በመከላከያ ሰራዊቱ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጭምር የተሰራጨው ምልመላ እስከ ጥር መጨረሻ እንደሚዘልቅም ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል። እድሜያቸው 18 አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወጣቶች እንዲመዘገቡ ጥሪ የሚያቀርበው የመከላከያ ሚኒስቴር ማስታወቂያ በመላ ሀገሪቱ በየቀበሌ ጽሕፈት ቤቶች ...
Read More »በጀርመንና ኔዘርላንድ የአየርና የየብስ ትራንስፖርት ተቋረጠ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2010) በአውሮፓ ሃገራት ጀርመንና ኔዘርላንድ የተከሰተው ከፍተኛ አውሎ ነፋስ፣የአየርና የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎትን መግታቱ ተገለጸ። በአውሮፓ መንገደኞች ከሚበዙባቸው አውሮፕላን ማረፊያዎች አንዱ የሆነው የኔዘርላንዱ ሲኪፖል የአውሮፕላን ማርፊያ አገልርግሎቱ ተስተጓጉሏል። ከከባዱ አውሎ ንፋስ ጋር በተያያዘም የህንጻው ጣሪያዎች መነቃቀላቸው ታውቋል። በሰአት 140 ኪሎ ሜትር ወይንም 90 ማይል የሚጓዘው አውሎ ንፋስ ዛፎጭን እየገነዳደሰ የባቡር መስመሮች ላይ በመጣሉ የባቡር አገልግሎት ጭምር እንዲቋረጥ አድርጓል። ...
Read More »የውጭ ምንዛሪ እጥረት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ፈጥሯል
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2010) የወጭ ንግድ ሚዛን መዛባትና የውጭ ምንዛሪ እጥረት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ደንቃራና ቀውስ መፍጠሩን አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት/አይ ኤም ኤፍ/ አስታወቀ። የአይ ኤም ኤፍ የቦርድ ዳይሬክተሮች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያን በተመለከተ ባካሄዱት ምክክር የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ለአንድ አመት ከ8 ወራት ብቻ የሚበቃ ነው። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በመስቀለኛ መንገድ ላይ የቆመ እንዲሆን ያደረገውም ግሽበትን ...
Read More »ከጸረ ሽብር ሕጉ የሚሰረዝም ሆነ የሚሻሻል አንቀጽ የለም
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2010) ሕወሃት ኢህአዴግ ከጸረ ሽብር ሕጉ የሚሰረዝም ሆነ የሚሻሻል አንቀጽ እንደሌለ አስታወቀ። በአንድ አንቀጽ ላይ ብቻ ማብራሪያ የሚሰጥ ተጨማሪ ህግ ይወጣል ብሏል። ከጸረ ሽብር ሕጉ የሚሰረዝም ሆነ የሚሻሻል አንቀጽ እንደሌለ የተገለጸው ሕወሃት ኢሕአዴግ በጀት ከሚመድብላቸውና ታማኙ ከሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ነው። በዚህ ውይይት ገዢው ፓርቲ በስራ ላይ ያለው ጸረ ሽብር ህግ በምንም አይነት ከአለም አቀፍ ...
Read More »ሕወሃት እንደገና የማጥራት ስራ ይቀረዋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2010) ሕወሃት አመራሮቹን ግለሂስ እንዲያደርጉ በማድረግ እንደገና የማጥራት ስራ እንደሚቀረው የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ገለጹ። የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ድርጅታዊ ጉባኤ ሲጠናቀቅ በጥገኝነት ላይ የንበረውን አመራር ለማጥራት ከላይ እስከታች አሁንም ግምገማው ይቀጥላል ብለዋል ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል። የድርጅቱ ነባር ታጋይ አቶ ስዩም መስፍን በበኩላቸው ሕወሃት የታገለው ከድህነት ለመውጣት ሆኖ እያል አንዳንድ አመራሮች በጥርጣሬ እንዲታይ አድርገውታል ሲሉ ተናግረዋል። እናም ...
Read More »ሁከት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች አሉ ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2010) በኢትዮጵያ የሚከበረውን አመታዊ የጥምቀት በአልና የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች መኖራቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። በመንግስታዊና በፓርቲ መገናኛ ብዙሃን የተለቀቀው የፌደራል ፖሊስ መግለጫ አደጋውን ለመጣል እየተንቀሳቀሱ ያሉት ሃይሎች እነማን እንደሆኑ ግን ግልጽ አላደረገም። የፖለቲካ ምሁራን ይህን የፌደራል ፖሊስ መግለጫ ሕዝብን የማሸበር ርምጃ ሲሉ ተችተውታል። አንዳንዶቹ ስልጣን ላይ ያለውን ቡድን የቀደመ ተግባር እየጠቀሱ ራሱ አደጋ ለመጣል አስቦ ...
Read More »የከተራ በአል ተከበረ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2010) በመላው ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የከተራ በአል ተከብሮ ዋለ። የጥምቀት በአልም ነገ በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ይውላል። በከተራ በአሉ በየአድባራቱ የሚገኙች ታቦታት ከየቤተእምነቶቻቸው ወጥተው በክርስቲያናዊ መዝሙሮች በመታጀብ ወደ ማደሪያቸው ተሸኝተዋል። በአሉ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ ሃገሪቱ የተከበረ ሲሆን በተለይ በጎንደር 44ቱ ታቦታት ወተው በድምቀት መከበሩንም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የጥምቀት በአል ኢየሱስ ክርስቶስ በበእደ ዮርዳኖስ ...
Read More »