የከተራ በአል ተከበረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2010)

በመላው ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የከተራ በአል ተከብሮ ዋለ።

የጥምቀት በአልም ነገ በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ይውላል።

በከተራ በአሉ በየአድባራቱ የሚገኙች ታቦታት ከየቤተእምነቶቻቸው ወጥተው በክርስቲያናዊ መዝሙሮች በመታጀብ ወደ ማደሪያቸው ተሸኝተዋል።

በአሉ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ ሃገሪቱ የተከበረ ሲሆን በተለይ በጎንደር 44ቱ ታቦታት ወተው በድምቀት መከበሩንም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የጥምቀት በአል ኢየሱስ ክርስቶስ በበእደ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ጊዜ የሚያስታወስ ሃይማኖታዊ በአል።

ኢሳት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የጥምቀት በአል ይሁንላችሁ ይላል።