Author Archives: Central

በፓርላማ አባላት ላይ የሚደረገው ማስፈራሪያ ተጠናክሮ ቀጥሏል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21 2010) የአስቸኳይ ገዜ አዋጁን እንዲያጸድቁ በፓርላማ አባላት ላይ የሚደረገው ማስፈራሪያ ተጠናክሮ መቀጠሉ ታውቀ። ከኦህዴድ አባላት በተጨማሪ በብአዴን እና ደኢህዴን አባላት ላይ ጭምር በተጠናከረው በዚሁ የማስፈራራት ርምጃ በዋናነት የሚሳተፉት ከመከላከያ ሚኒስቴር የተላኩ ጄኔራሎች እና የደህንነት  ሰራተኞች መሆናቸውን ለኢሳት የደረሰው መራጃ ያመለክታል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ደኢህዴን በአቶ ሃይለማርያም ምትክ ሊቀመንበር የመረጠውና በኋላም የቀየረው በሕወሃት መሪዎች ትዕዛዝ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ...

Read More »

ህወሃት የዶ/ር አብይ አህመድን መመረጥ አጥብቆ እየተቃወመ ነው

ህወሃት የዶ/ር አብይ አህመድን መመረጥ አጥብቆ እየተቃወመ ነው (ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን ለመተካት ኦህዴድ በእጩነት ለማቅረብ ያዘጋጃቸው ዶ/ር አብይ እንዳይመረጡ፣ ህወሃት ጠንካራ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ነው። የደረሱን ተጨባጭ መረጃዎች እንደሚያመለክቲት፣ህወሃቶች ዶ/ር አብይን “ትግሬን ይጠላል” የሚል ቅስቀሳ ከፍተውባቸዋል። የኦሮምያ ክልል መሪ አቶ ለማ መገርሳ ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ዶ/ር አብይ የድርጅቱ ...

Read More »

በደሴ የመጓጓዣ ዋጋ ተመን በእጥፍ ጭማሪ እንደተደረገበት ነዋሪዎች ተናገሩ

በደሴ የመጓጓዣ ዋጋ ተመን በእጥፍ ጭማሪ እንደተደረገበት ነዋሪዎች ተናገሩ (ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) በደሴ ከተማና በዙሪያዋ በሚገኙ የታክሲና የአውቶቡስ መጓጓዣ ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል።መረጃዎች እንዳሳዩት፣ በተለይ በከተማዋ የታክሲ ዋጋ ላይ ሃምሳ በመቶ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል። ‘’በዓለም ላይ የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ ባለበትና ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ ሳይኖር ለምን የዋጋ ጭማሪው ማድረግ አስፈለገ?’’ ሲሉ ነዋሪዎቹ ቢጠይቁም፣ ምላሽ የሚሰጣቸው አካል ...

Read More »

የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ ብስራት አቢ በእስር ቤት በደረሰባቸው ድብደባ የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ ብስራት አቢ በእስር ቤት በደረሰባቸው ድብደባ የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ እንደሚገኝ ተገለጸ። (ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) በአዲስ አበባ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ አደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ የበሩት አቶ ብስራት አቢ በእስር ቤት ውስጥ በደረሰባቸው ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች ምክንያት የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ምንጮቻችን ገልጸዋል። በማእከላዊ እስር ቤት ክፍል ውስጥ በመርማሪዎች በተፈጸመባቸው ከፍተኛ ድብደባ ...

Read More »

ለ 95 ክፍት የስራ ቦታ 13 ሺ ሰዎች አመለከቱ (ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) የአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን 95 ባለሙያዎችን ለመቅጠር ላወጣው ማስታወቂያ 13 ሺ ተወዳዳሪዎች ማመልከታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። ባለሥልጣኑ ታኅሳስ 15 ቀን 2010 ዓ.ም 95 ሰራተኞችን ለመቅጠር ያወጣውን ማስታወቂያ ተከትሎ ስራ ፈላጊዎች የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት አጥለቅለቀው ሰንብተዋል ብሎአል ጋዜጣው። መስሪያ ቤቱ እንዲህ አይነት ብዛት ...

Read More »

ቤተ እስራኤላዊያን በአዲስ አበባ የረሃብ አድማ አደረጉ

ቤተ እስራኤላዊያን በአዲስ አበባ የረሃብ አድማ አደረጉ (ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ነዋሪነታቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላዊያን ወደ እስራኤል ለመግባት በሚጠባበቁበት ወቅት የአገሪቱ መንግስት ድጎማ ለማቋረጥ የወሰነውን ውሳኔ በመቃወም ከዛሬ ረቡእ ጀምሮ በአዲስ በአበባ በሚገኙ ቤተመቅደሶች ሴናጎ ውስጥ በመገኘት የርሃብ አድማ አድርገዋል። ቤተ እስራኤላዊያኑ ከዘመዶቻቸው ጋር ለመገናኘት በጉጉት በሚጠብቁበት ሰዓት በጀት ለማቋረጥ መወሰኑ እንዳሳዘናቸው መግለጻቸውን፣ የረሃብ ...

Read More »

የቀድሞዋ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት የጥፋተኛነት ውሳኔ ተላለፈባቸው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20 2018) በሙስና ተወንጅለው ወህኒ የወረዱት የቀድሞዋ የደቡብ ኮርያ ፕሬዚዳንት በዛሬው ዕለት የጥፋተኛነት ውሳኔ ተላለፈባቸው። ውሳኔውን ተከትሎም በ30 ዓመታት እስራት እንዲቀጡ ኣቃቤ ህግ ጠይቋል። የቀድሞዋ የደቡብ ኮርያ  ፕሬዚዳንት ፓክ ሁን ሄ በሙስና ተወንጅለው ከስልጣናቸው የተባረሩት አምና በመጋቢት ወር ሲሆን ፣ወህኒ ከወረዱም አንድ ዓመት ያህል አስቆጥረዋል። የ66 ዓመቷ የቀድሞዋ የደቡብ ኮ ርያ ፕሬዚዳንት ፓክ ሁን ሄ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ያልተገባ ስጦታ ...

Read More »

የአገዛዙ ታጣቂዎች አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2010) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኋላም ቢሆን ሕዝቡ ተቃውሞውን በመቀጠሉ የአገዛዙ ታጣቂዎች አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ መታዘዙን የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያት ገለጸ። ኮማንድ ፖስቱ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴና ደምቢዶሎ የተካሄደውን የሕዝብ ተቃውሞ በመጥቀስ የአገዛዙ ታጣቂዎች የሕዝብ ሕይወት እንዳይጠፋ ጥንቃቄ ከማድረግ ይልቅ ርምጃ እንዲወስዱ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል። የፓርላማ አባላት አስቸኳይ ጊዜውን እንዳያጸድቁ በሕዝብ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑም ሕገ ወጥ ተግባር ነው ብሏል። የአስቸኳይ ...

Read More »

በሶማሌ ከእስር ቤት በይቅርታ የወጡ እስረኞች ተመልሰው ታሰሩ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2010) በሶማሌ ክልል ከሚገኘው ጄል ኦጋዴን እስር ቤት በይቅርታ ተፈቱ የተባሉ ከ1500 በላይ እስረኞች ተመልሰው ወደ እስር ቤት እንዲገቡ መደረጉ ተገለጸ። ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ሽፋን የሰጡት የፍቺ ዜና ሳምንት ሳይሞላው እስረኞቹ ወደ ጄል ኦጋዴን ገብተዋል ያለው የሶማሌ ክልል ተወላጆች የአክቲቪስቶች መረብ መገናኛ ብዙሃኑ በአስቸኳይ የሰሩትን ዜና እንዲያስተባብሉ ጠይቋል። እስረኞቹ መፈታታቸው ተገልጾ፣ ፎግራፍና ቪዲዮ ከተቀረጹና ዜና ከተሰራጨ በኋላ የዚያኑ ...

Read More »

ደኢህዴን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2010) የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን በሁለተኛ ዙር ምርጫ የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ። ይህ ዜና በዚህ መልኩ ተስተካክሎ ከመወጣቱ በፊት በድርጅቱ ፌስ ቡክ ገጽ ላይ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውይፋ ሆኖ ነበር። የደኢሕዴን ፌስ ቡክ ደረገጽ የመጀመሪያው መግለጫ የ1 ኛ ዙር ወጤት ሰለነበር ሰህተቱ መፈጸሙን አምኗል። የደኢሕዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫ በየጊዜው ሲቀያየር ቆይቶ ...

Read More »