በምስራቅና በምዕራብ ጉጂ ዞኖች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲቀርብበት የነበረው የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ተጨማሪ የ10 አመት የኮንትራት ስምምነት ማግኘቱን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ስምምነቱን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በአዶላ ወዮ ተማሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ስምምነቱን ተቃውመዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች የሚድሮክ ወርቅ ላለፉት 20 አመታት ከፍተኛ መጠን ያለው የወርቅ ማእድን ሲያወጣ ቢቆይም፣ ...
Read More »Author Archives: Central
በሽንሌ ዞን እስርና ድብደባው እንደቀጠለ ነው
በሽንሌ ዞን እስርና ድብደባው እንደቀጠለ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮ-ሶማሊ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የክልሉ የልዩ ሃይል አባላት በርካታ ወጣቶችን እየያዙ አስረዋል። ብዙዎችም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ብዙዎቹ ወደ ጅግጅጋ ተወስደው የታሰሩ ሲሆን፣ በእስር ቤት ውስጥም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። በሽንሌ ከተማ በእስር ላይ የሚገኘው የወጣት አብዲ ሙሚን ሃሰን ቤተሰቦች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ካለፉት አርብ ጀምሮ ድሬደዋን ጨምሮ በተለያዩ የክልሎ ...
Read More »ኢንሳ አሁንም ትርምስ ላይ ነው
ኢንሳ አሁንም ትርምስ ላይ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢንሳን ለረጅም ጊዜ ሲመሩ የነበሩት ጄ/ል ተክለብርሃን ወ/አረጋዊ ከለቀቁ በሁዋላ ስልጣናቸውን በሚለቁ የህወሃት ባለስልጣናት ቦታ ሌሎች አዳዲስ ሰዎች እየተተኩ ነው። የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት አቶ ተመስገን ጥሩነህ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሰዎችን እየሾሙ መሆኑን የደረሱን የሹመት ደብዳቤዎች ያመለክታሉ። ህወሃቶች በርካታ የስለላ መሳሪያዎችን ወደ መቀሌ የወሰዱ ሲሆን፣ ከ10 ያላነሱ ...
Read More »በአማራ ክልል በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ንብረት መባከኑን ተጋለጠ፡፡
በአማራ ክልል በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ንብረት መባከኑን ተጋለጠ፡፡ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) የምክር ቤቱን አባላት ያነጋገረና ከፍተኛ ጥያቄ ያስነሣ የ2010 ዓ.ም የክዋኔ ኦዲት የስድስት የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የኦዲት ግኝት ይፋ ተደርጓል፡፡ ዋና ኦዲተሩ ረዳት ፕሮፌሠር ገረመው ወርቁ ለምክር ቤቱ ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት፣ በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ንብረት መባከኑን ተናግረዋል፡፡ ዋና ኦዲተር ...
Read More »ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ ሰላም አወረዱ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 19/2010)ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ በመካከላቸው ያለው ጦርነት ማክተሙን አወጁ። ከ63 አመታት በኋላም የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን የደቡብ ኮሪያን ድንበር ተሻግረው ከአቻቸው ሙን ጄ ኢን ጋር መገናኘታቸው ተሰምቷል። ሁለቱ መሪዎች በሰላጤው የነበረው ጦርነት ማክተሙን እውን ለማድረግም ለሰላም፣ለብልጽግናና ለአንድነት በጋራ ሊሰሩ የፓንሙንጆም ስምምነትን ተፈራርመዋል። ሰሜን ኮሪያና ደቡብ ኮሪያ በሰጣ ገባና በጠላትነት ሲፈላለጉ 63 አመታትን አስቆጥረዋል። በየጊዜው በድንበሮቻቸው አካባቢ በሚቀሰቀሱ ...
Read More »የገዛህኝ ነብሮ የስንብት ፕሮግራም ተካሄደ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ19/2010) ባለፈው ቅዳሜ በጆሀንስበርግ ለተገደለው አክቲቪስት ገዛህኝ ገብረመስቀል ነብሮ የስንብት ፕሮግራም ተካሄደ። የቀብር ስነስርዓቱ ነገ እንደሚፈጸም የደረሰን መረጃ ያመልክታል። የአክቲቪስት ገዛህኝ ወላጅ እናት ትላንት ምሽት ከአዲስ አበባ ደቡብ አፍሪካ መግባታቸውም ታውቋል። በሌላ በኩል የዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውያን ግብረሃይል ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ደጃፍ የሻማ ማብራት ስነስርዓት የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል። የዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውያን ግብረሃይል በአክቲቪስት ገዛህኝ ነብሮ የቀብር ስነስርዓት ላይ የሚገኝ ...
Read More »መዲናዋ በዳቦ ፈላጊዎች ወረፋ መጨናነቋ ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 19/2010) መዲናዋ አዲስ አበባ በዳቦ ፈላጊዎች ወረፋ መጨናነቋ ተሰማ። በከተማዋ የዳቦ ዋጋ ከሚገባው በላይ መናሩንና አንድ ብር ይሸጥ የነበረው የዳቦ ዋጋም አንድ ብር ከ75 ሳንቲም መግባቱ ታውቋል። የከተማዋ መስተዳደር ችግሩ የተከሰተው በውጭ ምንዛሪ እጦት ምክንያት መሆኑን አስታውቋል። ላለፉት አመታት ተባብሶ የቀጠለውና ስር የሰደደው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ወደ ሃገር ውስጥ ተገዝቶ የሚገባውን ስንዴ በመቀነሱ የአዲስ አበባ ዳቦ ቤቶች በወረፋ ...
Read More »ወደ መሃል ሐገር የጦር መሳሪያዎች በመግባት ላይ ናቸው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 19/2010)ወደ መሃል ሐገር በከፍተኛ ደረጃ የጦር መሳሪያዎች በመግባት ላይ መሆናቸው ተገለጸ። የመከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በዚህም ሳቢያ መሳሪያ ግዥና ሽያጭ ቀጥሏል። ይህንን ለመግታትና በተለያዩ ቦታዎች የተከማቹ መሳሪያዎችን ለመያዝ የቀጠና 5 ኮማንድ ፖስት በአማራ ክልል አሰሳ ላይ መሆኑም ተመልክቷል። በሕወሃቱ የጦር አዛዥ በሜጀር ጄኔራል ፍስሃ ኪዳኑ የሚመራው የቀጠና 5 ኮማንድ ፖስት በሕገወጥ መንገድ የሚገቡ መሳሪያዎችን ለማስቆም በሚል በአማራ ክልል ነዋሪዎችን ...
Read More »በጅጅጋ የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 19/2010) በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጂጂጋ የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ። በከተማዋ የንግድም ሆነ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ መቆሙን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። በተያያዘ ዜና በሽንሌ ከተማ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል። የአጋዚ ሰራዊት ከሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ጋር በመሆን በህዝቡ ላይ ርምጃ በመውሰድ ላይ መሆነ ተገለጿል። የአጋዚ ወታደሮች ባርባራት በሚል የሚታወቁትን የሶማሌ ክልል ወጣቶችን ድብደባ ሲፈጽሙባቸውና በርካቶችን አፍነው ...
Read More »የቅማንትን የመብት ጥያቄ ባነሱ ግለሰቦች ግጭት ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 19/2010) በህወሃት በተደራጁና የቅማንትን የመብት ጥያቄ ባነሱ ግለሰቦች ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ። በጭልጋ ሀሙስ ገበያ በተባለ አካባቢ ከትላንት ምሽት ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል። የአማራ ክልል ምክር ቤት በተያዘው ሳምንት 69 ቀበሌዎች በቅማንት አስተዳደር ስር ልዩ ወረዳ መዋቅር ይዘው እንዲካለሉ ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም የሚገባን የዞን መዋቅር ነው ባሉ ግለሰቦች ግጭቱ መቀስቀሱን የኢሳት የመረጃ ምንጮች ...
Read More »