Author Archives: Central

በተለያዩ አካባቢዎች ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ተስፋፍቷል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 30/2010) በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በስፋት እየተካሄደ መሆኑን ሃገሪቱን እየገዛ ያለው ወታደራዊ እዝ/ኮማንድ ፖስት/አስታወቀ። በተጠናቀቀው ሚያዚያ ብቻ ከ2 መቶ በላይ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎች በድብቅ ሲዘዋወሩ መያዙን ኮማንድ ፖስቱ ገልጿል። ኮማንድ ፖስቱ በሞያሌ ከተማ የተከሰተውን ግጭትና በዚሁ ሰበብም በርካታ ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል። በኢትዮጵያ የተደነገገው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስፈጽመው ወታደራዊ እዝ/ኮማንድ ፖስት/በሞያሌ ግጭት ተፈጥሮ በርካታ ሰዎች ...

Read More »

በአዶላ ከተማ ሁለት ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 30/2010) በኦሮሚያ ክልል አዶላ ከተማ ሰላማዊ ተቃውሞ ካሰሙ ነዋሪዎች መካከል ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ። የከተማዋ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን ያሰሙት በአዶላ ከወርቅ ማውጣት ጋር በተያያዘ የሜድሮክ ኢትዮጵያ ፈቃድ ታደሰ መባሉን ተከትሎ ነው። ሜድሮክ ኢትዮጵያ በሻኪሶና በአዶላ ለ20 አመት የወርቅ ማዕድን ሲያወጣ የነበረው ስምምነት ተጠናቆ እንደገና ለ10 አመት መታደሱ በአካባቢው ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቷል። ዛሬ የምስራቅ ጉጂ ዞን አካባቢዎች በአብዛኛው በተቃውሞ ውስጥ ...

Read More »

በናይጄሪያ በተፈጸመ ጥቃት 45 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 29/2010) በናይጄሪያ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለው ጥቃት 45 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ። በሃገሪቱ ሰሜናዊ ግዛት ጉዋስካ በተባለችው መንደር ተፈጸመ የተባለው ይሄ ጥቃት ምክንያቱ ምን እንደሆነ አልታወቀም ብሏል ሮይተርስ በዘገባው። በሃገሪቱ ቦኮ ሃራምን ጨምሮ ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች በናጄሪያ የተለያዩ መንደሮች ጥቃት ሲፈጽሙ ቆይተዋል። እንደ አውሮፓውያኑ በ2015 ተመርጠው ሃገሪቱን በመምራት ላይ ያሉት መሃመድ ቡሃሪም በሃገሪቱ ሰላምና ደህንነትን አስከብራለሁ ሲሉ ቃል ቢገቡም ያንን ...

Read More »

ደራሲ አሰፋ ገብረማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

  (ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 29/2010) አንጋፋው ደራሲ አሰፋ ገብረማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በቀድሞ መንግስት “ኢትዮጵያ ቅደሚ’ የሚለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር የደረሱት  አቶ አሰፋ ገብረማርያም በ82 ዓመታቸው በስደት በሚኖሩባት የአሜሪካዋ ከተማ ላስቬጋስ ሕይወታቸው አልፏል። በ1928 አዲስ  አበባ ከተማ የተወለዱት አቶ አሰፋ ገብረማርያም የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርበኞች ት/ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን  ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት መከታተላቸውን የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል። ከፍተኛ ትምህርታቸውን በቀድሞው ...

Read More »

በአባይ ግድብ ዙሪያ በአዲስ አበባ የመከረው ስብሰባ ያለውጤት ተጠናቀቀ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 29/2010) በአባይ ግድብ ጉዳይ ላይ በአዲስ አበባ የመከሩት የ3ቱ ሀገራት የመስኖ ሚኒስትሮች ስብሰባ ያለውጤት ተጠናቀቀ። የኢትዮጵያ፣የግብጽና የሱዳን ሚኒስትሮች በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ቢያደርጉም ስብሰባው ያለውጤት ተጠናቋል። ስብሰባው ያለውጤት ቢጠናቀቅም ከአንድ ሳምንት በኋላ እያንዳንዱ ሀገር 3 ሚኒስትሮች የሚወከሉበት 9 አባላት ያሉት ውይይት እንደገና ለማካሄድ ቀጠሮ ይዘዋል። በአባይ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያና የሱዳን አቋም ተመሳሳይ እንደሆነ ይነገራል። በግብጽ በኩል ግን የግድቡ ...

Read More »

አንዳርጋቸው ጽጌ ይፈታ በሚል ዘመቻ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 29/2010) አንዳርጋቸውን ነፃ ማውጣት ኢትዮጵያዊነትን ማክበር ነው በሚል መሪ ቃል  ከዛሬ ጀምሮ እስከ ረቡዕ የሚቆይ  አንዳርጋቸው ፅጌ ይፈታ የሚል ዘመቻ በማህበራዊ ድረ ገፅ ተጀመረ። በፌስ ቡክና ቲውተር የተጀመረው ዘመቻ የአንዳርጋቸውን ፎቶ ፕሮፋይል ስዕል በማድረግ፣ የእሱንና  የቤተሰቡን ፎቶግራፎች ከተለያዩ መልዕክቶች ጋር በማሰራጨት፣ስለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፖለቲካዊ ስብዕና የሚያጎሉ መጣጥፎችን በማጋራት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል። ዘመቻውን በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን አክቲቪስቶች ...

Read More »

ለተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ድርጅት የተሰጠው ብድር 4 ቢሊየን ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 29/2010) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ድርጅት የሰጠው ብድር 4 ቢሊየን ብር መድረሱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። የመንግስት ኩባንያዎችም ሆነ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በድር ለማግኘት በተቸገሩበት በአሁኑ ወቅት አቶ ተክለብርሃን አምባዬ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በወሰዱት ገንዘብ አኪር የተባለውን የኮንስትራክሽን ድርጅት መግዛታቸውም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተበዳሪዎች ገንዘብ ለማቅረብ በከፍተኛ ደረጃ በተቸገረበት በአሁኑ ወቅት ለአቶ ተክለብርሃን ...

Read More »

በሻኪሶ ተቃውሞ አገረሸ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 29/2010) በሻኪሶ ዳግም ተቃውሞ አገረሸ። የሜድሮክ የወርቅ ኩባንያ ለተጨማሪ አስር ዓመት ኮንትራቱ መራዘሙን ተከትሎ ከአንድ ሳምንት በፊት የጀመረው ተቃውሞ ቀጥሏል። ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ የሻኪሶ ከተማ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ መቆሙ ታውቋል። ለገንደንቢ የሜድሮክ ወርቅ ማምረቻ ጠቅላላ ስራ ማቆሙንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ከሻኪሶ ወደ አዶላና እና ወደተለያዩ ቦታዎች የሚወስዱ መንገዶች በሙሉ ተዘግተዋል። የኢሳት ወኪል ካደረሰን መረጃ ለማወቅ ...

Read More »

በሞያሌ ግጭት ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 29/2010) በሞያሌ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ። በሶማሌ ክልል ልዩ ሃይልና በኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት የተነሳ ከሞያሌ ዙሪያ ካሉ አካባቢዎች በርካታ ሰዎች መሰደዳቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ትላንት እሁድ እንደ አዲስ ባገረሸው በዚሁ ግጭት ከሁለቱ ወገኖች የተገደሉ እንዳሉም ታውቋል። የህወሃት አገዛዝ ግጭቱን ለማስቆም እስካሁን የወሰደው ርምጃ እንደሌለ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ሞያሌ ከውጥረት መላቀቅ አልቻለችም። ግጭት የየዕለት መገለጫዋ እየሆነ ...

Read More »

በሞያሌ ግማሽ ቀን በፈጀ የተኩስ ለውውጥ በርካታ ሰዎች አለቁ

በሞያሌ ግማሽ ቀን በፈጀ የተኩስ ለውውጥ በርካታ ሰዎች አለቁ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ትናንት እሁድ ከቀኑ 5 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት በነበረው የተኩስ ለውውጥ ከኦሮምያና ከሶማሊ በኩል በርካታ ዜጎች ተገድለዋል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዛሬ ሞያሌ የሚገኙትን የኦሮምያ ፖሊሶች ትጥቅ አስፈትተዋቸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ተሰደዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገልጹት ትናንት ማንነቱን ያላወቁት አንድ እንግዳ ወደ ከተማዋ መግባቱን ...

Read More »