የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚሁ ስብሰባ ላይ የግንቦት7 ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ፣ የኦነግ የስራ አስፈጻሚ አባልና የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት አቶ አዴሳ ቦሩ እና ተዋቂው አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ታማኝ በየነ በእንግድነት ተገኝተዋል። የግንቦት 7 ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበበ ቦጋል ጥምረት ለነጻነት፤ ለፍትሃና ለእኩልነት በጄነራል ከማል ገልቹ ከሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጋር ባለፈው ሳምንት ...
Read More »Author Archives: Central
አስራ ሁለት ሺ ኢትዮጵያውያን በሱዳን ታሰሩ
የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዲያስ አዲስን በመግለጽ የዘገበው ደብረብርሀን ብሎግ ፣ በሰሜን ሱዳን ውስጥ በሚገኘው ኦምዱርማን እስር ቤት ውስጥ 12 ሺ ኢትዮጵያውያን ታስረው ይገኛሉ። ምንም እንኳ የታሰሩት ኢትዮጵያውያን ያለ ህጋዊ ሰነድ ወደ ሱዳን የገቡ ናቸው ቢባልም፣ ህጋዊ ወረቀት የያዙት ሳይቀር መታሰራቸው ተዘግቧል። በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያውያን ችግሩን በሱዳን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሲያመለክቱ ኢምባሲው “አያገባኝም ” የሚል መልስ መስጠቱ ታውቋል። ...
Read More »የአቶ ስብሀት ነጋ የሰጡት አስተያየት አነጋጋሪ ሆኗል
የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ስብሀት እርሳቸው የሚመሩት የሰላምና አለማቀፍ ተቋም ኢንሰቲቲዩት ባዘጋጀው ውይይት ላይ ነው፣ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ለምን በጥቃቅን የሙስና አይነቶች ላይ ብቻ ያተኩራል በማለት ጠይቀው፣ በኢትዮጵያ ሙስናን ለማጥፋት ፍላጎት እንጅ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ብሎ ነገር የለም። ይህ በሌለበት ተግባርም ውጤትም አይኖርም። ቁርጠኛ ሌባ አለ ቁርጠኛ ተዋጊ ግን የለም።” በማለት እርሳቸው በአምሳያቸው የቀረጹትን የመለስን መንግስት ነቅፈዋል። አቶ ...
Read More »አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በሙስና ከተጠየቅኩ ወይዘሮ አዜብ መጠየቅ አለባቸው አሉ
የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የውስጥ ምንጮቹን በመጥቀስ እንገለፀው፤ይህ የሆነው የክልሉ ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ-ደኢህዴግ ከየካቲት 5 እስከ የካቲት 11 ቀን 2004 ዓመተምህረት ድረስ ባካሄደው ግምገማ ላይ ነው። ቀደም ሲል በጋምቤላ በተደረገ ተመሣሳይ ግምገማ በ አኝዋኮች ጭፍጨፋ ተጠያቂ እንዲሆኑ ውሳኔ የተላለፈባቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ኦባንግ ኦሞድ፦” በ አኝዋኮች ግድያ እኔ የምጠየቅ ከሆነ፤ ድርጊቱ እንዲፈፀም ትዕዛዝ ያስተላለፈልኝ ...
Read More »በስዊድን የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ የተሳካ ዝግጅት አካሄደ
የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እኤአ ፌብሩዋሪ 25፣ 2012 በስቶክሆልም በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 6 ሰአት እስከ ምሽ ቱ 4 ሰአት በተከናወነው በዚህ ዝግጅት የኢሳት ጋዜጠኞች የሆኑት ገሊላ መኮንንና አፈወርቅ አግደው፣ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው መስፍን ነጋሽ፣ በእንግድነት ተገኝተዋል። ዝግጅቱ በክርስትናና እስልምና ሀይማኖት መሪዎች ጸሎት የተከፈተ ሲሆን በቅርቡ ለነጻነቱ ሲል ራሱን ያቃጠለውን የኔሰው ገብሬን በቅርብ የሚያውቁት መምህር ...
Read More »በጋምቤላ የሚገደሉት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
የካቲት 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአካባቢው መሬት በመውሰድ በእርሻ ሥራ ላይ የተሰማራ ወጣት ሰሞኑን ተገደለ። በሊዝ ኪራይ በጣም ሰፊ መሬት በመውሰድ በእርሻ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሦስት ወጣቶች ፤እርሻቸውን ጎብኝተው ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች የተኩስ እሩምታ በመክፈት አንድኛውን ገድለውና አንድኛውን ክፉኛ አቁስለው ከአካባቢው ተሰውረዋል። ከስፍራው የደረሰን ተጨባጭ መረጃ እንደሚያመለክተው፤መኪናው ውስጥ ከነበሩት ሶስት ወጣቶች መካከል አንድኛው ምንም ጉዳት ...
Read More »የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጅሊስ እኛን አይወክለንም፣ አህባሽን እና ኢህአዴግን ግን ሊወክል ይችላሉ አሉ
የካቲት 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአወሊያ መስጊድ ከቀኑ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለሰባት ሰዓታት በቆየው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ በመንግስትና በመጂሊስ ላይ ያነጣጠሩ ጠንካራ ተቃውሞዎች ተስተጋብተዋል። ይሁንና፤ በመስጊዱ ውስጥ “መጅሊስ አይወክለንም፣ ኮሚቴው የማያውቀውና ከእውቅናው ውጪ የሆነው “ኢህአዴግም አይወክለንም” የሚሉ በርካታ በኤ 4 መጠን የተባዙ ወረቀቶችለምዕመኑ መበተናቸውና በተለያዩ ቦታዎች ተለጥፈው መታየታቸው፤በተቃውሞው ማሰማቱ ሂደት ላይ እንቅፋት ፈጥሮ ነበር። የተቃውሞ ወረቀቱ ከ ...
Read More »ኢህአዴግ በሆላንድ የጠራው ስብሰባ ከኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ገጠመው
የካቲት 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአምስተርዳም ከተማ የተጠራው የኢህአዴግ ስብሰባ ከቀኑ 7፡ሰ ዓት ተኩል ላይ እንደሚጀመር መረጃ የደረሳቸው ኢትዮጵያውያን፤ ልዩ ልዩ መፈክሮችንና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ በስፍራው የተገኙት፤ ከስብሰባው መጀመር 30 ደቂቃ ቀድመው ነበር። “የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!ጋዜጠኞች ይፈቱ! የመሬት ንጥቂያ በአስቸኳይ ይቁም! ሞት ለዜናዊ! መለስና ግብረ አበሮቹ ለፍርድ ይቅረቡ! እና ምዕራባውያን መለስን መደገፍ አቁሙ!”የሚሉት፤ ፤በሰልፈኞቹ ከተስተጋቡት መፈክሮች ጥቂቶቹ ናቸው። ...
Read More »የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች ጋዜጣዊ መግለጫ
Ethiopian Orthodox religious leaders Press conference February 2012
Read More »ኢብሳ አስፋው ኦሮሞንና አማራን ለማጋጨት እየሞከረ ነው ተባለ
የካቲት 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቃሊቲ እስር ቤት የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነውን አንዱአለም አራጌን በመደብደብ ጉዳት ያደረሰው የእድሜ ልክ ፍርደኛው ኢብሳ አስፋው ፣ አንዱአለም ኦሮሞነቴን ጠቅሶ ስለሰደበኝ ነው የደበደብኩት በማለት የኦሮሞ ተወላጅ እስረኞችን ለማነሳሳት ሙከራ አድርጎ እንዳልተሳካለት የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ለኢሳት ገልጠዋል። ኢብሳ አንዱአለምን ከደበደበ በሁዋላ ሌላው የአንድነት የአመራር አባል ወደ ሆነው አቶ ናትናኤል መኮንን ...
Read More »