ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወደ ተክለሀይማኖትና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በሚወሰድው መንገድ ላይ በርካታ ህጻናት ጎዳና ላይ ውለው ያድራሉ። ትናንት ከጧቱ 4 ሰአት ከ 30 ደቂቃ ላይ ነው። አንድ አዲስ አበባ ፖሊስ አባል አንድ በልመና የሚተዳደርን የጎዳና ተዳዳሪ ይደበድበዋል። የጎዳና ተዳዳሪውም በድብደባው ህይወቱ ያልፋል። ድብደባውን የፈጸመው ፖሊስና ጓደኞቹ በፍጥነት ከአካባቢው ይሰወራሉ። ትንሽ ቆይቶም ሌሎች ፖሊሶች በብዛት መጥተው አካባቢውን ...
Read More »Author Archives: Central
በአዲስ አበባ ስታዲየም ለድብድብ የተገባበዙትን ባለሥልጣናት ፤ የዕለቱ የክብር እንግዳ ተነስተው ገላገሉ
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ነገሩ የሆነው፤በብራዚል ለሚደረገው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያና -የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ግጥሚያ ሲያደርጉ ነው። ጠቡ የተፈጠረውም፤ ጨዋታውን ለመመልከት በክቡር ትሪቡን በታደሙ ሁለት ባለሥልጣናት መካከል ነው-በደደቢት ስፖርት ክለብ መስራች እና ፕሬዚዳንት በኮሎኔል አወል ኢብራሂም እና በስፖርት ኮሚሽነሩ በ አቶ አብዲሳ ያደታ መካከል። የሁለቱም ባለስልጣናት ጠባቂዎች ጠቡን ለማብረድ ያደረጉት ሙከራ በባለስልጣናቱ ...
Read More »በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን በመቃወም ሰልፍ አካሄዱ
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሳስካቺዋን፣ ማኒቶባ እና ከአልበርታ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በሳስካቺዋን ዩኒቨርስቲ ፊት ለፊት በመገኘት ፣ ዩኒቨርስቲው በሙስና እና ዜጎችን በህገወጥ መንገድ በማፈናቀል የሚወነጀሉትን የደቡብ ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን መጋበዙን ተቃውመዋል። ሰልፈኞቹ ዩኒቨርስቲው አቶ ሽፈራውን ወደ መጡበት እንዲመለሱ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። ዩኒቨርስቲው የውጭ ጉዳይ ልዩ አማካሪ የሆኑት ቶም ዊሻርት፣ በአቶ ሽፈራው ላይ የቀረበውን አቤቱታ እንዳልሰሙ ነገር ግን ...
Read More »በኢህአዴግ እና በመምህራን መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እየተካረረ ነው
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ተቃዋሚ ናቸው” የተባሉ መምህራንን ከሥራቸው ለማባረር ለየትምህርት ቤቶች የወረደን መመሪያ ለማስፈፀም ፈቃደኛ ያልሆኑ ርዕሳነ-መምህራን በፈቃዳቸው ከሃላፊነታቸው ለመነሳት መልቀቂያ እያስገቡ ነው። ኢህአዴግ፤ የመንግስት ተቀጣሪ መምህራንን ለማባረር አዲስ ስልት መቀየሱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች አጋለጡ፡፡ ቀደም ሲል መምህራን ፦“የሙያችን ክብር ተነክቷል፣ ዳቦ ለመብላት የሚያስችልና ከሁሉም ሙያዎች ጋር ትይዩ የሆነ የደሞዝ ማስተካከያ ስኬልና ጭማሪ ይደረግልን” የሚሉ ...
Read More »“ናሽናል ፕሬስ ክለብ” ፤ጋዜጠኛ አበበ ገላውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበውን ክስ ውድቅ እንዳደረገው አስታወቀ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የተባለው የገዥው ፓርቲ የፕሮፓጋንዳ አውታር አምባሳደር ብርሀነ ገብረክርስቶስን በማነጋገር ትናንት ባሰራጨው ቪዲዮ፤ ጋዜጠኛ አበበ ገላው በቡድን 8 አገሮች ስብሰባ ላይ በፈፀመው ተግባር፤ ከእንግዲህ የአሜሪካ መንግስት በሚያዘጋጃቸው ማናቸውም ስብሰባዎች ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ እንደተጣለበትና የፕሬስ ፈቃዱን እንደተነጠቀ አውጇል። ከአሜሪካ የጋዜጠኞች ማህበር የተገኙት መረጃዎች ግን፤ ይህ የአምባሳደር ብርሀነ ገብረክርስቶስ ቃለ-ምልልስ ስህተት መሆኑን የሚያመለክቱ ...
Read More »የብርሃንና ሠላም በጋዜጣ አሳታሚዎች ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ አጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ “ፊልም የለኝም” በሚል አሳታሚዎች ተጨማሪ ወጪ አውጥተው ሌላ ማተሚያ ቤት እንዲያሰሩ የሰጠውን ትዕዛዝ አላነሳም፡፡ድርጅቱ በተጨማሪም እሁድ ዕለት የሚታተሙትን ሪፖርተር፣ፎርቹን፣ካፒታል የተባሉ ጋዜጦች የቀለም ሕትመት ማሸን ተበላሸቶብኛል በሚል ሳያትም የቀረ ሲሆን ፎርቹንና ካፒታል በዛሬው ዕለት በሁለት ቀለም ብቻ ለገበያ ሲወጡ የእሁዱ ሪፖርተር በነገው ዕለት ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የእረቡ ሪፖርተር በዚህ ምክንያት ...
Read More »መኢአድ ሰኔ 1/1997 ዓ.ም በግፍ የተጨፈጨፉ ሰማእታትን ሰባተኛ ዓመት ዘከረ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 1/1997 ዓ.ም. ‹‹ድምፃችን ይከበር›› ብለው አደባባይ የወጡ ሰላማዊ ዜጎች በግፍ የተጨፈጨፉበትን ዕለት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሰኔ 3/2004 ዓ.ም. በጽ/ቤቱ ሻማ በማብራትና የተፈፀሙትን ዘግናኝ ድርጊቶች የሚያስታውሱና የሚያወግዙ ጽሁፎችን በማቅረብ አስቦ ውሏል፡፡ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ተቃውሞቸውን ለማሰማት ወደ አደባባይ በወጡ ዜጎች ...
Read More »ቀጣዩ በጀት ለመደበኛ ከተያዘው ጋር የሚስተካከል የ26.6 ቢሊየን ብር ጉድለት ያሳያል
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የ2005 ዓ.ም አገራዊ ረቂቅ በጀት በዛሬው ዕለት ለፓርላማ አቀረበ፡፡ የቀረበው አጠቃላይ በጀት 137 ቢሊየን 836 ሚሊየን 47 ሺህ 105 ብር ሲሆን ይህ ረቂቅ በጀት በገቢና ወጪው መካከል የ26 ቢሊየን 634 ሚሊየን 956 ሺህ 84 ብር ጉድለት ያሳያል፡፡ይህ ጉድለት በ2005 ዓ.ም ከተመደበው ጠቅላላ በጀት ውስጥ ለመደበኛ ወጪዎች ማለትም ለደመወዝና ሥራማስኬጃ ...
Read More »በማላዊ ሊካሄድ የነበረው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ወደ አዲስ አበባ እንዲዛወር ተወሰነ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ስብሰባው ወደ አዲስ አበባ እንዲዛወር የተደረገው፤ ማላዊ በ ዓለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የ እስር ማዘዣ የወጣባቸውን የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆኗ ነው። “አገራችን ስብሰባውን የምታዘጋጅ ከሆነ ኦማር ሀሰን አልበሽር እንዲሳተፉ አንፈቅድም፤ምክንያቱም በዓለማቀፉ ፍርድ ቤት በዘር ማጥፋት እና በጦር ወንጀለኝነት የሚፈለጉ ሰው ናቸው” ብለዋል- የማላዊ ፕሬዚዳንት። በ አዲስ አበባ የ አፍሪካ ህብረት አምባሳደር ...
Read More »የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መሪዎችን ለመምረጥ ዝግጅት እያደረጉ ነው
ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሙስሊሞቹ መንግስት በየቀበሌው ለማድረግ የሰበውን የመጅሊስ ምርጫ እንደማይቀበሉትና ምርጫውን በራሳቸው መንገድ በመስኪዶች ውስጥ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ሙስሊሞቹ በራሳቸው መንገድ ተጉዘው የመጅሊስ አባላትን የሚመርጡ ከሆነ፣ በመንግስት ተደግፈው ወደ ስልጣን ከሚመጡት የመጅሊስ አባላት ጋር ውዝግብ የሚፈጠር ይሆናል። መንግስት የመጅሊስ አባላትን ለማስመረጥ የሚያደርገው ጥረት ሙስሊሞችን እያስቆጣ መምጣቱንም ዘጋቢአችን ከአዲስ አበባ ገልጧል። በመንግስትና በሙስሊሞች መካከል ያለው ውዝግብ ...
Read More »