Author Archives: Central

አንዋር መስጊድ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ድርቅ ተመታ

ነሀሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 7 ወራት ከ50 ሺ ህዝብ በላይ ሲያስተናግድ የከረመው አንዋር መስኪድ በዛሬው የጁመአ ጸሎት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ100ዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ብቻ አስተናግዷል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ወደ አንዋር መስጊድ እንዳይሰባሰብ ተተኪ አመራሩ ውስጥ ለውስጥ ባሰራጨው መመሪያ መሰረት ፣ ህዝቡ ወደ መስጊዱ የሚያደርገውን ጉዞ እንደገታ ታውቋል። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተል አንድ ስሙ እንዳይገለጥ የፈለገ ሰው ለኢሳት ...

Read More »

ክቡር ገና የሚረገጥ ህዝብ ድንገት ይነሳል አሉ

“አንድ ህዝብ ዝም ብሎ ተኝቶ ሲረገጥ አይውልም፤ ድንገት ይነሳል፤ መተንፈሻ ያጣ ህዝብ ሌላ መንገድ በመፈለግ ለመተንፈስ ይሞክራል” ሲሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ክቡር ገና ተናገሩ። አንድነት “በዴሞክራሲአዊ ስርአት ግንባታ የሲቪክ ማህበራት ሚና” በሚል ርእስ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተናጋሪ እንግዳ ሆነው የቀረቡት፤ ዶ/ር ክቡር ገና ከፍኖት ነጻነት አዘጋጆች ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፤ “ፖለቲካ ችግርን በውይይት መፍቻ መንገድ ሆኖ ሳለ” በኛ ...

Read More »

የአሜሪካን ድምጽ ሬድዮ ፕሮግራም በመታወክ ላይ ነው

በኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚደረግ አፈና መቀጠሉን ከአዲስ አበባ የመጣው ዜና ያስረዳል። በዚህም መሰረት የአሜሪካን ድምጽ ሬድዮ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች በአጭር ሞገድ እንዲሁም በሳተላይት የሚያስተላልፍው ፕሮግራም በመታወክ ላይ ይገኛል። የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከህዝብ ዕይታ መሰወርን ተከትሎ የኤርትራ ቴሌቭዥን የሣተላይት ስርጭት መመታቱ ሲታወስ፤ በሐገሪቱ በሥርጭት ግንባር ቀደም የሆነው ፍትህ ጋዜጣ ሥለ አቶ መለስ ሁኔታ ዘገባ ይዞ በመውጣቱ በፍርድ ቤት ውሳኔ መቃጠሉ ...

Read More »

ሙስሊሞች ተቃውሞ ለመግለጽ መስኪድ ሳይሄዱ ቀሩ

(Aug. 17) በአዲስ አበባ የሙስሊሞች ተቃውሞ በዛሬው እለትም የቀጥለ ሲሆን፤ አንዋር መስጊድ በተቃውሞ ጭር ብሎ እንደዋለ ከአዲስ አበባ ለለማወቅ ችለናል። የአዲስ አበባ ምንጮቻች እንደገለጹልን፤ በዚህ አርብ ደህንነቶች ቀንደኛ ያሉዋቸውን የሙስሊሙን አስተባባሪዎች ለመያዝ ዝግጅት ላይ እንደሆኑ መረጃ በመውጣቱ የተነሳ፤ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ወደአንዋር መስጅድ ሳይሄድ እንደዋለና አንዋር በተቃውሞ ጭር ብሎ እንደዋለ ምንጮቻችን ጠቅሰዋል። በደሴም በትናንትናው እለት ከተደረገው በመንግስት የተቀነባበረ ሰልፍ በሁዋላ ውጥረቱ ...

Read More »

ዲፕሎማቶች እየኮበለሉ ነው ተባለ

(Aug. 17) ከአቶ መለስ ዜናዊ መሰወር ጋር ተያይዞ በውጭ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ወደአገር ቤት ቢጠሩም፤ ብዙዎቹ በነበሩበት አገር ወይንም ወደሌላ ሶስተኛ አገር በመኮብለል ጥገኝነት እየጠየቁ እንደሆነ የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በህንድ የወ/ሮ ገነት ዘውዴ ምክትል ሆነው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ደረጀ አስፋው ጄቶ ወደአሜሪካን እንደከዱና በአሜሪካን ጥገኝነት እንደጠየቁ ታማኝ ምንጮች ነግረውናል። በሌላ ዜናም በካርቱም ዲፕሎማት ሆነው ሲሰሩ የቆዩትና ከዚህ ቀደም በጃፓንና በዱባይ ለረጂም ...

Read More »

በዳላስ የተገደሉት ኢትዮጵያዊያን ተጠርጣሪ ገዳይ ታወቀ

በዳላስ የተገደሉት ሁለት ኢትዮጵያዊያን ተጠርጣሪ ገዳይ መታወቁን የዳላስ ፖሊስ አስታወቀ። ምክንያት ንቀውኛል በማለት። ተጠርጣሪው አብይ በለጠ ግርማ የተባለ ኢትዮጵያዊ ሲሆን፤ ተጠርጣሪው ሟቾቹን የደስታ ምግብ ቤት ባለቤቶች፤ አቶ ያየህ ይራድ ለማንና ወ/ሮ ኔነሽ ደስታን በተገደሉ እለት፤ ከምግብ ቤታቸው ጀምሮ ሲከተላቸው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ሁለቱ የደስታ ምግብ ቤታ ባለቤቶች፤ ባለፈው ረቡእ እኩለ ሌሊት ላይ ከስራ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ በራቸው ላይ በጥይት ተመተው ...

Read More »

የአቡነ ጳውሎስ ቀብር ነሀሴ 17 ቀን እንደሚካሄድ ታውቋል

(Aug. 17) በትናንትናው እለት ከዚህ አለም በሞት የተለዩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ ቀብር በመጪው ሀሙስ ነሀሴ 17 ቀን እንደሚካሄድ ተነገረ። ከስፍራው ባገኘነው መረጃ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ከየአገረስብከቶቻቸው ወደአዲስ አበባ እየገቡ እንደሆነም ታውቋል። በኢትዮጵያ የሚገኘው የአገር ቤቱ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ እንደተቀመጠ የታወቀ ሲሆን፤ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራአስኪያጅ የሆኑት፤ ብጹእ አቡነ ፊልጶስ በጊዜያዊነት የሲኖዶሱ ሰብሳቢ እንደሆኑ ታውቋል። በትናንትናው እለት ...

Read More »

የረሀብ አድማው አፈና እስር ትኩረት እንዲያገኝ ይረዳል ተባለ

ከነገ እኩለ ሌሊት እስከ ኦገስት 19 ወይም ነሐሴ 13 በዋይት ሀውስ ፊት ለፊት የሚደረገው የረሀብ አድማ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የመብት ረገጣ አጉልቶ ለማሳየት እንደሚረዳ የረሀብ አድማው አዘጋጅ  ቃል አቀባይ ለኢሳት ገለጹ:: ቃል አቀባይዋ ወይዘሪት ትርሲት ጌታቸው፤ ነጻ ሚዲያ ለኢትዮጵያ የሚባለው ቡድን የረሀብ አድማ እንዲደረግ የወሰነው በሀገራችን እየተባባሰ ያለውን የመብት ገፈፋ በተለይ ደግም  በጋዜጠኞች ላይ የተጣለውን አፈና እስርና እንግልት በመቃወም መሆኑን ...

Read More »

የግራዚያኒ ሀውልትና የመታሰቢያ ፓርክ ውስጥ ተቃውሞ ቀሰቀሰ

የጣልያን መንግስት ለፊልድ ማርሻል ግራዚያኒ ያቆመው ሀውልትና የመታሰቢያ ፓርክ በኢጣሊያ ውስጥ ተቃውሞ እንደቀሰቀሰ ቢቢሲ ዘገበ። የቤኔቶ ሙሶሎኒ የጦር መሪ በመሆን፤ በሊቢያና በኢትዮጵያ በፈጸመው ከፍተኛ ፍጅትና ግድያ የተፈረደበት ግራዚያኒ፤ የ160 ሺህ ዶላር መታሰቢያው የቆመለት፤ ከሮም ወጣ ብላ በምትገኝ መንደር ውስጥ ነው። የኢጣሊያ ዋንኛው ግራ-ዘመም ፓርቲ፤ ግራዚያኒ በ1930ዎቹ ውስጥ በኢትዮጵያ የፈጸመውን የዘር ማጥፋት በማስታወስ፤ በዚህ ዘመን ለግራዚያኒ ይህ መታሰቢያ መቆሙን አጥብቆ አውግዟል። ...

Read More »

ሙስሊም ጋዜጠኞች አገር ጥለው ተሰደዱ

(Aug. 16) የመንግስት ጥቃት በመፍራት ከሀገር መሰደዳቸውን ሁለት የሙስሊሞች ጉዳይ ጉዳይ ጋዜጠኞች ይፋ አደረጉ። መንግስት ሁለቱን ጋዜጤኞች በቁም እስር ላይ አስቀምጧቸው እንደነበር ይታወሳል። ጋዜጠኛ ይስሐቅ እሸቱ እና አክመል ነጋሽ የተባሉት፤ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ወቅታዊ ጥያቄ አጉልቶ በማሳየት የሚታወቀው የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሄት አዘጋጆች፤ መንግስት በሙስሊሙና በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርሰውን ግፍ በመፍራት ከሐገር መሰደዳቸውን የጋዜጠኞቹን የቅርብ ሰዎች በመጥቀስ ፍኖተ ነጻነት ዘግቧል። ጋዜጠኞቹ የሙስሊሞን እንቅስቃሴና ...

Read More »