(Aug. 27) ጄኖሳይድ ወች በመባል የሚታወቀው ድርጅት ፕሬዚዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ግሪጎሪ ስታንተን፤ አቶ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ አደገኛ የሆነ የዘር መከፋፈልና፤ ጥቂት የአንድ ብሄረሰብ የበላይነትን አውርሰው ያለፉ አምባገነን መሪ ነበሩ ሲሉ ተናገሩ።
በአለማችን ላይ የዘር ፍጅትን ለመከላከል የሚሰራው የዚሁ ድርጅት ፕሬዚዳንትና በጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርሲቲ የግጭትና የዘር ፍጅት ጥናት የምርምር ፕሮፌሰር የሆኑት ፕሮፌሰር ስታንተን አቶ መለስ በኢትዮጵያዊያን ላይ ግፍና በደል ከመፈጸም አልፈው፤ እንደጋምቤላና ኦጋዴን ባሉ የሀገሪቱ ክልሎች የዘር ፍጅት ፈጽመዋልም ብለዋል።
ፕሮፌሰሩ በተሌይ ለኢሳት በሰጡት ቃለምልልስ እንደገለጹት፤ እንደ አቶ መለስ አይነት በአንድ ግለሰብ ተክለሰውነት ላይ የተገነባ ስርአት፤ አውራው መሪ ሲወድቅ የስልጣን ሽኩቻና የስርአት መናጋት ስለሚያስከትል፤ አደገኛ ሁኔታዎች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
ፕሮፌሰር ስታንተን አክለውም፤ የአቶ መለስን ሞት ድርጅታው ቀደም ብሎ ቢያውቅም፤ ጉዳዩ በይፋ እስከሚገለጥ መጠበቃቸውን ተናግረዋል።