በሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን የሃይል እርምጃ” ተቃወሙ

ሐምሌ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን “መንግስት በአዋልያና በአንዋር መስጊድ ተሰባስበው በሰላማዊ መንገድ ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ ባቀረቡ ነዋሪዎች ላይ የወሰደውን የሃይል እርምጃ” ተቃወሙ።

 

ከ300 በላይ ኢትዮጵያውያን በግል ተነሳስተው በቆንስሉ ግቢ በሚገኘው የኮሚኒቲ አዳራሽ ተሰባስበው “በንጹሃን ምዕመናን ላይ የተወሰደው እርምጃ አግባብነት እንደሌለው ለማሳዎቅ፤ የታሰሩት እንዲፈቱ፤ የሞቱት ሙሉ መረጃ እንዲሰጣቸውና መንግስት የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ ይፈታ ዘንድ አቤቱታ እንደሚያቀርቡ ” ወስነዋል፡፡፡

ተሰብሳቢዎች የመንግስት ሃላፊዎችን ለማነጋገር ጥረት ቢያደርጉም “ስብሰባው ህጋዊ ፈቃድ ሳይሰጠው የተከናዎነ ስለሆነ ማነጋገር አንችልም ” የሚል መልስ በቆንስል ሃላፊዎች መሰጠቱን ለማወቅ ተችሎአል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide