ገዢው ፓርቲ በዋልድባ ከፍተኛ ሰራዊት በማሰማራት አካባቢውን ማረስ መጀመሩ ህዝቡን አስቆጣ

ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ዋልድባ አካባቢ የሚገኙ የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ባለፉት ስድስት ቀናት በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ አካባቢው በመሄድ የሰፈሩ ሲሆን፣ የመከላከያ ሰራዊቱን መስፈር ተከትሎ  አካባቢው መታረስ መጀመሩን ለማወቅ ተችሎአል። የአካባቢው ህዝብ መከላከያ ሰራዊቱ ጋር ተፋጦ የሚገኝ ቢሆንም እስካሁን ድረስ የተፈጠረ ግጭት የለም። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው  የአካባቢው ህዝብ በመንግስት ድርጊት በእጅጉ ማዘኑን ገልጠው፣ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን ተቃውመው እንዲነሱ ጠይቀዋል።

መንግስት በዋልድባ ገዳም አካባቢ የጀመረው የሸንኮራ አገዳ ተክል እንቅስቃሴ ኢትዮጵያውያንን እያስቆጣ መሆኑ ይታወቃል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide