ሚያዚያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የፌስቱላ ሆስፒታል መስራችና ባለቤት ለሆኑት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የክብር ዜግነት ተሰጠ::
ዶክተር ካትሪን በኢትዮጵያ የፌስቱላ ሆስፒታሎችን በመመሰረት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የሕክምና እንዲሁም የሰብዓዊ አገልግሎት በመስጠት በመቶሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እናቶችን ሕይወት ታድገዋል።
የክብር ዜግነቱን የሰጡት አቶ መለስ ዜናዊ ናቸው። ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ የተወለዱ ናቸው። በአዲስ አበባ በቀድሞው የልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል በአሁኑ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ሆስፒታል የአዋላጅነት ትምህርት ቤት ለመምህርነት በኢትዮጵያ መንግሥት የወጣውን የሥራ ማስታወቂያ አልፈው እኤአ በ19 59 ስራ ጀምረዋል።
በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሰረት ሽልማቱ መሰጠት የነበረበት በአገሪቱ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ቢሆንም፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ፕሬዚዳንቱ ሳይገኙ በመቅረታቸው አቶ መለስ ሽልማቱን ሰጥተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመቶ አለቃ ግርማ ጤና ሁኔታ የተለያዩ ወሬዎች ይናፈሳሉ። የመንግስት መገናኛ ብዙሀን መቶ አለቃ ግርማ በህክምና እየተረዱ ናቸው፣ አልሞቱም ሲል መዘገቡ ይታወሳል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide