ሚያዚያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንደዘገበው ተዋጊዎቹ ወደ ፑንትላንድ የተጓዙት ከኢትዮጵያ ፣ ከኬንያና ከአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሀይል የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት ለመከላከልና ራሳቸውን ለማደራጀት ነው። አልሸባብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእየ አቅጣጫው በሚሰነዘርበት ጥቃት እየተዳከመ መምጣቱ ይነገራል። የፑንትላንድ መንግስት የአልሸባብ ወደ ግዛቱ መግባት እንዳሳሰበው እየገለጠ ነው።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ታዋጊዎቹ ወደ ፑንትላንድ ማምራታቸው በየመን ከሚገኘው የአልቃይዳ ሀይል ጋር በቀላሉ ለመገናኘት ያስችላቸዋል ተብሎአል። የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ግን አልሸባብ በቅርቡ ከአልቃይዳ ጋር በጋራ ለመስራት ያሳለፈው ውሳኔ ለድርጅቱ መዳከም ከፍተኛውን አስተዋጽኦ አድርጓል። ለአልሸባብ አላማ ድጋፍ ያሳዩ የነበሩ ሀይሎች ሳይቀር ከአልሸባብ ውሳኔ በሁዋላ ራሳቸውን እያገለሉ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ ያለውን ቆይታ በዚህ ወር አጠናቆ እንደሚወጣ መንግስት ማስታወቁ ይታወቃል። ይሁን እንጅ አልሸባብ ቀጥተኛ የሆነ ጥቃት ባይፈጽምም አሁንም በሞቃዲሾና በባይዶዋ የተለያዩ ጥቃቶችን እየፈጸመ ነው። ከቀናት በፊት በባይዶዋ በፈጸመው ጥቃት ከ10 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በሞቃዲሾ ባካሄደው ጥቃት ደግሞ የመንግስት ባለስልጣናት መገደላቸው ይታወሳል።
___________________________________________________________________________________________________ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide