ኢትዮጵያ የተመድ ሰራተኛን በሽብርተኝነት ወንጅላ አሰረች

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ብሉምበርግ አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጠቅሶ እንደዘገበው ግለሰቡ የታሰሩት ከኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ ነው።

የተመድ የደህንነት ሰራተኛ የሆኑት አብዱረህማን ሼክ ሀሰን ለእስር የተዳረጉት በኦጋዴን ክልል የተጠለፉትን ሁለት የሶማሊ ተወላጆችን ለማስለቀቅ ድርድር እንዲጀመር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

የመንግስት ቃል አቀባይ የሆነው ሽመልስ ከማል የተመድ ሰራተኛ ስለመታሰሩ እንደማያውቅ ተናግሯል። የአምነስቲ ኢንትርናሽናል የአፍሪካ ተመራማሪ የሆኑት ቤስተን ለብሉምበርግ እንደገለጡት በብዥታ የተሞላው የኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግ ጋዜጠኞችን  እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች የሽምግልና ስራ ለመስራት የሚሞክሩት ሳይቀር እንደሚያስር ገልጠዋል።

ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት የ11 አመታት እስር ተፈርዶባቸው ወይኒ ይገኛሉ። የተመድ ሰራተኛ የሆነው ዩሱፍ ሙሀመድ በሽብርተኝነት ሰበብ  የታሰረው ዴንማርክ የሚገኘው ወንድሙ የኦብነግ አባል ነው ተብሎ በመጠርጠሩ ነው። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና አንዱአለም አራጌን ጨምሮ በርካታ ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት ተከሰው በእስር በመሰቃየት ላይ ናቸው።

_________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide