መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ/ ም
ኢሳት ዜና:-ታዋቂው አለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ማርች 12 ፣2012 ባወጣው መግለጫ የመለስ መንግስት በሲቪል ማህበረሰብ ህግ መሰረት ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዳይንቀሳቀሱ በማድረጉ ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚታየውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ይፋ ለማድረግ አልተቻለም።
በዚህ ህግ የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ በጸጥታ ሀይሎች ዳፋውን እያየ መሆኑን ድርጅቱ ገልጧል።
አብዛኞቹ የሰብአዊ መብት ተማጓች ድርጅቶች በአዲሱ ህግ የተነሳ ስራቸውን እንዲያቆሙ፣ ወይም እንቅስቃሴያቸውን እንዲገቱ ተደርጓል።
የሲቪል ሶሳይቲው አዋጅ፣ ከጸረ ሽብረተኝነት አዋጅና ከሚዲያ ህግ ጋር ተጣምሮ ኢትዮጵያኖች ሀሳባቸውን በነጻነት እንዳይገልጡና መንግስትን እንዳይተቹ አድርጓቸዋል።
አምነስቲ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በማጋለጥ የሚታወቅ አለማቀፍ ተቋም ነው።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide