የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በፈጠራ የሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በአስከፊ እስርቤት ውስጥ ከሚማቅቁት መካከል የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው አንዱአለም አራጌ በደረሰበት ድብደባ የተነሳ በደንብ መቆም እንደማይችልና ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታትም እንዳለበት ለፍርድ ቤቱ ተናገረ
የእስረኞችን የመከላከያ ማስረጃ ለማየት የተሰየመው ችሎት፣ የብይን ግልባጭ ለጠበቆቹ ባለመሰጠቱ ችሎቱን ለማስተላለፍ ተገዷል።
አንዱአለም በድብደባው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት፣ የማረሚያ ቤቱ ሀኪሞች ሊረዱት ቢሞክሩም ከሀቅማቸው በላይ እንደሆነባቸውና ችሎቱ ውጪ ወጥቶ የሚታከምበትን ሁኔታ እንዲፈቅድለት ጠይቋል።
አንዱአለምን ተከትሎ ሌሎቹ እስረኞች ናትናኤል መኮንን እና ክንፈሚካኤል ደበበ በአንዱአለም ላይ ድብደባ የፈጸመው እስረኛ ወደ እነሱ ክፍል ተዛውሮ ተመሳሳይ ጥቃት ለመፈጸም እየዛተባቸው ነው። እስረኞቹ እንዳሉት በተኙበት እንዳይገድላቸው በመስጋት በእየተራ ነው ይተኛሉ፣ ምግባቸው እንዳይመረዝባቸውም ከፍተኛ ስጋት አላቸው።
ፍርድ ቤቱ የቃሊቲ እስር ቤት ሀላፊ ለመጋቢት 17 ቀን 2004 ዓም ቀርበው መልስ እንዲሰጡ ትእዛዝ ሰጥቷል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide