በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በአል ዘንድሮም በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም

ት ዜና:-በየአመቱ ከጥር 10 እስከ  ጥር 11 በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በአል ዘንድሮም በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

ታቦታቱ በአዲስ አበባ በ16 ቦታዎች ያደሩ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ከቅዱስ ሚካኤል ታቦት በስተቀር ሁሉም ወደ መጡበት ተመልሰዋል።

በጎንደር በአሉ የካርኒባል በአል የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ለአንድ ሳምንት እንደሚከበር ታወቋል።