ጥር 10 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ እንዳሉት፤በሀገሪቱ የነፃ ጋዜጣ ህትመት ስራ ዙሪያ ረጅም ጊዜ የወሰደ ምልከታና ጥናት በማካሄድ በቅርቡ‹‹ርግብ›› በሚል ስያሜ ሳምንታዊ ጋዜጣ ለማሳተም አስፈላጊ ዝግጅቶችን አጠናቅቀው እና አስፈላጊ ነገሮችን አሟልተው ከኢትዮጵያ ብሮድካስት
ባለስልጣን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ለማግኘትያቀረቡት ጥያቄ ከሁለት ወራት በላይ ምላሽ ሊያገኝ አልቻለም። ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት ፦” በቅድሚያ የድርጅቶቹን ባለቤቶች ማንነት ማጥናት አለብን”የሚል እንደሆነ ተመልክቷል።
የአማካሪ ድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ የሺዋስ አሰፋ ለባለስልጣኑ በላኩት ደብዳቤ፦ “የግል ሚዲያውን ማፈን ህገ-መንግስቱን መፃረር ነው›› በማለት ፈቃድ በመከልከላቸው የተሰማቸውን ቅሬታ ገልጸዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ፤ የፕሬስ ነፃነትን ለማስከበር የወጣውን አዋጅ 590/2000 በመተላለፍ ‹‹የድርጅቱን ባለቤቶች ማንነት ማጣራት አለብን፤ እስከዚያ ድረስም የምዝገባ ምስክር ወረቀት ላልተወሰነ ጊዜ አንሰጥም››ማለቱ፤ በአቶ የሺዋስ ደብዳቤ ላይ ተጠቅሷል።
በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና የኢሳት ባልደረባ ጋዜጠኛ ሢሳይ አጌና ምርጫ 97ትን ተከትሎ ለ 17 ወራት ታስረው በነፃ ከተሰናበቱ በሁዋላ ዳግም በፕሬስ ሥራ ለመሰማራት ያቀረቡት ተደጋጋሚ ጥያቄና ማመልከቻ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ይታወሳል።
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በመንግስት አግባብ ያልሆኑ አሠራሮች ዙሪያ ጠንከር ያለ ትችት የሚያቀርብ ገለልተኛና ነፃ የግል ጋዜጣ “ፍትህ” ብቻ እንደሆነ ይታወቃል።
ይሁንና፤ ከዚሁ ብቸኛ ጋዜጣ የሚሰነዘርባቸውንና ሊማሩበት የሚገባቸውን ትችት መስማትና መታገስ ያልቻሉት የአገዛዙ ቁንጮዎች፤በጋዜጣው አዘጋጆች ላይ ደህንነቶችንና አፋኝ ሀይሎችን በማሰማራት ጋዜጣውን ጨርሶ ለማጥፋት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል።
አስተያዬት ሰጪዎች፦ “ የአቶ በረከት አፋኝ ግብረ-ሀይል የቀረችውን አንዲት ጋዜጣ ለማጥፋት በተነሳበት ሰዓት፤ ክዋክብት አማካሪ ድርጅት ጋዜጣ ለማሳተም ፈቃድ ጠይቆ መከልከሉ የሚገርም አይደለም” ይላሉ።