(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011) የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት እየተደረገ ያለው ጥረት አመርቂ አይደለም ተባለ።
በሔሊኮፕተር የሚደረገው ጥረትም በቂ አይደለም ሲሉ የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ ገልጸዋል።
ውሃ በቅርበት አለመኖሩ በሄሊኮፕተር ጭምር እየተካሄደ ያለውን የማጥፋት ስራ አስቸጋሪ እንዳደረገው ተመልክቷል።
ከእስራዔል የእሳት አደጋ ባለሙያዎች በሰሜን ተራሮች ፓርክ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት በሚደረገው ርብርብ ቢሳተፉም እሳቱን መቆጣትጠር እንዳልተቻለ መረጃዎች አመልክተዋል።
እስከአሁን ከ700 ሄክታር በላይ የፓርኩ ይዞታ በእሳት መውደሙን ለማወቅ ተችሏል።
በአንዳንድ የፓርኩ ክፍሎች እሳት ይበልጥ እየተዛመተ መሆኑንም የአከባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።