(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2011) ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሕመድ አዲስ አበባን ነዋሪዎቿን ብቻ ሳይሆን ሁሉን መሰብሰብ የምትችል ተደርጋ ልትገነባ ይገባል ሲሉ ገለጹ፡፡
ዶክተር አብይ አሕመድ የዓለም ዐቀፍ ሴቶች ቀንነ ለማበር በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ ባሰሙት ንግግር አዲስ አበባን ለመከፋፈልና የእኔ ለማለት ከመቸኮል ይልቅ የማያግባቡ ጉዳዮችን በመነጋገር መፍታትና መጓዝ ያስፈልጋል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ አዲስ አበባን ብተመለከተ የተናገሩት ሀሳብ የኦሮሚያ መንግስት የአዲስ አበባ ባለቤትነታችን ሳይረጋገጥ የኮንደሚኒየም እጣ መውጣቱ ትክክል አይደለም በሚል ካወጣው መግለጫ ጋር ይቃረናል።
ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተከብሯል
በዚህ በዓል ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ያለም ፀጋይ፣ ሚኒስትሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች ታድመዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ አዲስ አበባን ነዋሪዎቿን ብቻ ሳይሆን ሁሉን መሰብሰብ የምትችል ተደርጋ ልትገነባ ይገባል ሲሉ ገለጸዋል ፡፡
ዶክተር አብይ አሕመድ የዓለም ዐቀፍ ሴቶች ቀንነ ለማበር በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ ባሰሙት ንግግር አዲስ አበባን ለመከፋፈልና የእኔ ለማለት ከመቸኮል ይልቅ የማያግባቡ ጉዳዮችን በመነጋገር መፍታትና መጓዝ ያስፈልጋል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ አዲስ አበባን ብተመለከተ የተናገሩት ሀሳብ የኦሮሚያ መንግስት የአዲስ አበባ ባለቤትነታችን ሳይረጋገጥ የኮንደሚኒየም እጣ መውጣቱ ትክክል አይደለም በሚል ካወጣው መግለጫ ጋር ይቃረናል።
የሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ሚኒስትር ወይዘሮ ያለም ፀጋይ የዘንድሮው የሴቶች ቀን በመላ ሀገሪቱ የጀግኒት ሀገራዊ ንቅናቄ እየተከናወነ ባለበት ወቅት የሚከበር ነው ብለዋል፡፡
በጀግኒት ሀገራዊ ንቅናቄ የአስተሳሰብና የተግባር ተግዳሮቶችን ለማስተካከል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰው፥ በምሁራንና ተተኪ አመራሮች በዘርፉ ላይ መነቃቃትን መፍጠር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል።
አሁን ላይ በሀገሪቱ እየታየ ያለው ለውጥ ሴቶችን በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስክ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑንም ነው የገለጹት ። ለዚህም ሴቶች በሀገሪቱ ከፍተኛ የአመራር ቦታዎች ላይ ያላቸው ተሳትፎ መጨመሩን ጠቅሰዋል።
ለሴቶች የስራ እድል በመፍጠር፣ የኢንተርፕራይዝ ባለቤት በማድረግ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን የማረጋገጥ ስራዎች መስራት ይገባልም ነው ያሉት።
በተለይም ያለ እድሜ ጋብቻ፣ የሴት ልጅ ግርዛትና ሌሎች ባህላዊ ልማዶች ጋር በተያያዘ ለፌስቱላ የሚጋለጡ ሴቶችን ችግር ለመከላከልና በችግሩ ተጋላጮች ላይ የሚደርሰውን የማህበራዊ መገለል ለማስቀረት በትኩረት መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ43ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡