ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ/ ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንደገለጠው የገናን በአል ተከትሎ የእርድ እንስሳት ዋጋና በከፍተኛ ደረጃ የጨመረ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የእርድ ከብት ከ12 ሺ ብር ጀምሮ በመሸጥ ላይ ነው።
በአዲስ አበባ ዶሮ ከ170 እስከ 200 ብር፣ በግ ከ1200 ብር እስከ 1700 ብር፣ ፍየል ከ1000 እስከ 1800 ብር በመሸት ላይ ነው።
ቅቤ በኪሎ በአማካኝ 130 ብር ዘይት 24 ብር ፣ አንድ ኪሎ ስጋ ደግሞ 90 ብር እየተሸጠ ነው።
ስኳር በኪሎ 14፣ ሽሮ ደግሞ 26 ብር በመሸጥ ላይ ነው።
በድሬዳዋ ደግሞ ፍየል ዝቅተኛው 1200 ብር፣ የበሬ ስጋ 90 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት በኪሎ 40 ብር ቀዩ ደግሞ 11 ብር ነው ። ዶሮ 100 ብር፣ ለጋ ቅቤ እስከ 160 ብር እንደሚሄድ ዘጋቢያችን ገልጧል።
“ኑሮን በጸጋ ከመቀበል ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ የለውም፣ አመት በአል የተወሰኑት ሰዎች ነው ሲሉ ” አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።