(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 4/2011)የማዕከላዊ አፍሪካ ሚኒስትር የነበሩ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን የኮሚቴ አባል በጦር ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ግለሰቡን የያዘችው ፈረንሳይ ስትሆንወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት ዘሔግ እንደሚወሰዱም ተመልክቱል።
ፓትሪስ ኤድዋርድ ናጊሶና የተባሉት የማዕከላዊ አፍሪካ የስፖርት ባለስልጣን በቁጥጥር ስር የዋሉት በሃገሪቱ ከ4 ዓመት በፊት በተካሄደ ሃይማኖት መሰረት ባደረገ ጥቃት ተዋናይ ሆነው በመገኘታቸው እንደሆነም ተዘግቧል።
እንደ አውሮፓውያኑ በ1958 ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የወጣችው የማዕከላዊ አፍሪካ እንዲሁም በሽምቅ ውጊያ ስትታመስ ቆይታለች።
ሃገሪቱ ነጻነቷን እንዳገኘች የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዴቪድ ዳኮ በጃንበዲል ቦካሳ በ5 ዓመት ግዜ ውስጥ ከተገለጠበት ግዜ ጀምሮ በየጊዜው በሚያገረሽ ቀውስ ስትናጥ የኖረች የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከ5 ዓመት በፊት በሃገሩ የተፈጠረው ሁኔታ ለኤድዋርዶ ናጊዋና መታሰር ምክንያት ሆኗል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2013 በማዕከላዊ አፍሪካ የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ በዋናነት በሙስሊሞች የሚመራ የሽምቅ ሴሌካ የተባለ ቡድን የሃገሪቱን ስልጣን ያዘ።
በአብዛኛው ክርስቲያኖች በሚኖሩበት ሀገር በሙስሊሞች የሚመራ የሃይል እንቅስቃሴ ወደ ስልጣን ሲወጣ ባላካ የተባለ የክርስቲያኖች እንቅስቃሴ በተቃውሞ ተንቀሳቀሰ።
በዚህም በተከሰተው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ተገደሉ።5 ሚሊየን ሕዝብ የማይኖርባት ሴንትራል አፍሪካ ከአንድ ሚሊየን የሚበልጥ ሕዝብ ተፈናቀለባት።
ለዚህ ግጭት መንስኤውም ክርስቲያኖቹን በማስተባበር የሚሊሺያ ቡድን በማደራጀት ሙስሊሞች ላይ ለተነጣጠረው ጥቃት ኤድዋርዶ ናጊዎና ተጠያቂ መሆናቸው ሲገለጽ ቆይቷል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015 በሃገሪቱ በተካሄደ ምርጫም ይህው መነሻ ሆኖ እንዳይሳተፉ ተከልክለዋል።
ስልጣን ላይ ካለው አካል ጋር በመደራደር የስፖርት ሚኒስትርነትን ያገኙት ኤድዋርዶ ናጊሶና የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኮሚቴ አባል ሲሆኑ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ከፍተኛ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
ናጊሶና ግን”የሚወራው ሃሰት ነው፣እውነት ቢሆን እኮ እኔን እዚህ ቦታ አታገኙኝም”ሲሉ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
“የሰራሁት ሁሉ ለሃገሬ የሚጠቅም ብቻ ነው”ሲሉም አክለዋል።
እኚህ ሰው ስልጣናቸውን አጥተው ወህኒ ወርደዋል።
እንደእሳቸው በጦር ወንጀል ከሚፈለጉት የሴንትራል አፍሪካ ባላስልጣናት ጋር ዘሔግ ኔዘርላንድስ ክስ ይቀርብባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።